የሕገ መንግሥት ለውጥ – ለኢትዮጵያዊነት የሚያስፈልግ መሠረታዊ ጉዳይ – ኪዳኔ ዓለማየሁ

ራዕይ፤ ዓላማና እቅድ፤

ለኢትዮጵያ ተገቢ የሆነ ሕገ መንግሥት ማዘጋጀቱና ተግባራዊ የማድረጉ ራዕይ ውድ ሐገራችን ከጽንፈኛነት፤ ከዘረኛነትና ከጭቆና የተላቀቀ ኢትዮጵያዊነት፤ ሰላም፤ ጸጥታ፤ አንድነት፤ እውነተኛ ዲሞክራሲ፤ ሕብረት፤ መከባበር፤ ፈጣን ልማት፤ ወዘተ. የሰፈነባት ሐገር እንድትሆን ለማረጋገጥ ነው። ይህ ራዕይ ስኬታማ እንዲሆን፤ በአጭር ጊዜ (1 ዓመት)  ብቁ በሆኑ ባለሞያዎች የተሟላ ረቂቅ ሕገ መንግሥት እንዲዘጋጅና በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በጥልቀት እንዲመለከተው ማድረግ፤ ከዚያም፤ አስፈላጊው ማሻሻል ተከናውኖ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመላው ሕዝብና ለሚመለከታቸው ድርጅቶች ቀርቦ እንዲመረመር በመጨረሻም ተቀባይነት በሚኖረው ብሔራዊ ጉባኤ ሕገ መንግሥቱ እንዲጸድቅ ሆኖ በሚቀጥሉት ዓመታትም በሕገ መንግሥቱ መሠረት በሚመረጥ ምክር ቤት እንደ አስፈላጊነቱ ማሻሻል ይቻላል።

 

የአሁኑ ሕገ መንግሥት ሰቆቃዎች፤

እንደሚታወቀው፤ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ላይ ሰፍኖ የሚገኘው ሕገ መንግሥት ሕዝቡን በቋንቋና በጠባብ ዘረኛነት በተመሠረተ የክልል ሥርዓት ከፋፍሎ ባስከተለው የእርስ በርስ መናቆር፤ አለመተማመን፤ መከፋፈል፤ አለመተባበር እጅግ አሰቃቂ መጠነ ሰፊ ስቃይ እያስከተለ ነው። በዘረኛነት ምክንያት በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ብዙ ሺዎች ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተፈናቅለዋል። እጅግ ብዙ ሰዎች በተለይ ሴቶችና ሕጻናት እየተሰቃዩ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከሕገር ለመሰደድና በታሪክ ያስተናግዷቸው በነበሩ በዓረብ ሐገሮች ጭምር በዝቅተኛ ደረጃ ለመኖር ተገድደዋል። በጠባብ ጎሰኛነት መለያየት ምክንያት እጅግ ብዙ ንብረት ወድሟል። የዘረኛነቱ ጠንቅ፤ ፋሺሽት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ዘመን ከፈጸመችው አሰቃቂ የጦር ወንጀል ብሷል።

ኤርትራ ከእናት ሐገሯ ከኢትዮጵያ ተገንጥላለች። በአሁኑ እኩይ የሕገ መንግሥት አወቃቀርና ሥርዓት፤ “ክልል” የተሰኙ አንዳንድ አካባቢዎችም ለመገንጠል እያኮበኮቡ ነው። ደቡብ ክልል ውስጥ ከሚገኙ አካባቢዎች ውስጥም ወደ ክልልነትና የመገንጠል አባዜ ለመዝቀጥ አቅጣጫ እያንጸባረቁ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  "የህወሓትን ሕዝባዊ ጭፍጨፋና ከፋፋይነት እንኮንናለን፣" - በኮሎኝና አካባቢዋ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ/ኮሚኒቲ ኮሎኝ/ጀርመን

ያሁኑን ሕገ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ የጫኑት ተጠያቂዎች አንደኛው ዓላማቸው፤ ሕዝቡ በዘረኛነት እርስ በርስ እንዲናቆርና እንዲጨፋጨፍ ስለ ነበር ያለሙት ሁሉ እየተሳካላቸው ነው።

ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ልዩ የሚያደርጋት፤ ሕዝቧ በኢትዮጵያዊነት አንድነት የሚተባበርና የማይደፈር መሆኑን በነአጼ ካሌብ ዘመነ መንግሥት ከዚያም በአድዋ የጦርነት ድል ያስመሰከረች መሆኗ ነው። ያሁኑ ሕገ መንግሥት ግን ኢትዮጵያን በአሳፋሪና በውዳቂ ዘረኛነት ከፋፍሎ ሊያስደፍረን ነው። የባሰ ሊያጫርሰን ነው።

በዘረኛነት ሥርዓቱ ከባድ ድክመት ምክንያት ኢትዮጵያ በድህነትና በሙስና ታዋቂ ሆናለች። በተጨማሪም፤ በብዙ ዓለም-አቀፋዊ መስፈርቶች ኢትዮጵያ የዓለም ጭራ ሆናለች። ተመጽዋች ሆናለች። http://hdr.undp.org/sites/all/themes/hdr_theme/country-notes/ETH.pdf

ለበለጠ ዝርዝር ከዚህ በታች ያሉትን መመልከት ይጠቅማል፤

https://ecadforum.com/Amharic/archives/19630/

https://www.nytimes.com/2019/01/03/opinion/ethiopia-abiy-ahmed-reforms-ethnic-conflict-ethnic-federalism.html

 

ሥልት፤

ለኢትዮጵያ ተገቢ የሆነ ሕገ መንግሥት ለማርቀቅ የመጀመሪያ እርምጃ መሆን የሚገባው፤ ለተግባሩ ብቁ የሆኑ የሕግ፤ የኢኮኖሚ፤ የማሕበራዊ፤ ወዘተ. ባለሞያዎች በመምረጥ አንድ ግብረ ኃይል ማቋቋም ነው። ግብረ ኃይሉም በተቻለ ፍጥነት፤ ከተቻለ በ6 ወሮች ውስጥ ተግባሩን አከናውኖ በሚለጥቁት 6 ወሮች ውስጥ በሚከናወን አንድ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በጥልቀት እንዲመረመር ማድረግ ነው። ከዚያም ሌላ ተገቢ የሆነ ግብረ ኃይል በማቋቋም፤ በሚለጥቀው አንድ ዓመት ውስጥ፤ በኢትዮጵያ እስከ ወረዳ ድረስ በሚከናወን ምክክር፤ የሚመለከታቸውን ድርጅቶች በሙሉ በማሳተፍ ስለ ረቂቁ ሕገ መንግሥት የሚገኘውን ሀሳብ ማከማቸትና በሐገር ለሚከናወነው 2ኛ ጉባኤ በማቅረብ ጥልቀት ያለው ውይይት እንዲከናወንበትና እንዲወሰንበት ማድረግ ነው።

 

የአዲሱ ሕገ መንግሥት ባለቤት፤

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለራሱ የሚበጀውን ሕገ መንግሥት በጥልቀት መርምሮ የሚያጸድቀውና በሚያስፈልግበት ጊዜም እንደ አስፈላጊነቱ የሚሻሻልበትን ሥርዓት ይወስናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በትግራይ ክልል አንድ ባለስልጣን በጥይት ተገደለ

 

ህወሀት ኢትዮጵያን እንዲዘረፍ መንገድ የከፈተው ህገ መንግስት! – በሰዋለ በለው

 

የኢህአዴግ መንግስት በሚቃወሙትና በሚተቹት ላይ እየወሰደ ያለውን አፈና እና እስር የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲታገለው ጥሪ እናቀርባለን!!!

 

ሦስቱን መንግስታት በንጽጽር (ንጉሱ- ደርግ-ኢህአዴግ)

 

አገዛዙ አለኝ የሚለውን ህገ መንግስት በተግባር ቀዶ ጥሎታል!

 

የኢህአዴግ መንግስት ጨካኝ ወይስ ጨቋኝ?

በኢዜማ እምነት አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥት ባለበት እስከቀጠለ ድረስ እንኳን ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን መገንባት ይቅርና እንደ ሀገር የመቀጠል ህልውናችንም ቢሆን አደጋ ላይ የወደቀ ነው!!

 

የሕገ-መንግስት ትርጉም ጥያቄ አስተያዬት – ኢሳያስ ሃይለማሪያም

ህገ-ፓርቲ/ ኢህአዴግ  ህገ-ህዝብ አይደለም

 

የእኛ “መንግስት” – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

 

የኦህዴድን አፓርታይድ አገዛዝ በሰላማዊ ትግል በፍጥነት እናስወግድ!!! -አስፋው ረጋሳ

 

 

1 Comment

  1. የህገ-መንግስት ለውጥ የሚባለው ነገር የማይገባኝ ሎጂክ ነው። 30 ዓመታት የተፈጸሙት ግፎች፣ ፖሊቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና እንዲሁም የባህል ቀውሶች በሙሉ ሊከሰቱ የቻሉት በህገ-መንግስቱ ምክንያት ነው እንደማለት ነው። በሌላ ወገን ደግሞ በህገ-መንግስቱ ውስጥ አንዳችም ቦታ ሰው ግደሉ፣ አፈናቅሉ፣ የባህልና የማህበራዊ ቀውስ አድርጉ የሚል አልሰፈረም። እንደዚህ ተብሎ ቢጻፍ እንኳ ማሰብ የሚችል ሰው ካለ ይህንን ማድረግ የለብኝም በማለት እምቢተኝነቱን ማሰማት አለባት። በአገራችን የተካሄደው ከፍተኛ ቀውስ ከሌሎች አገሮች ጋር ሲነፃፀር ተወዳዳሪ ባይገኝለትም በብዙ አገሮች ውስጥ አገዛዝ ነን የሚሉ ሁሉ በህገ-መንግስት ውስጥ ያልተጻፈ ነገር ተግባራዊ ሲያደርጉ እንሰማለን፣ እናያለንም። በእኔ ዕምነትና ሳይንሳዊ ምርምር በአገራችን ምድር ያለው ትልቁ ችግር እንደዚህ ዐይነት ህገ-መንግስት መኖሩ ሳይሆን ከፍተኛ የአዕምሮ ችግር ነው። ከአብዮቱ ጀምሮ የተፈጠሩትን ሁኔታዎች ስንመረመር ስልጣን ላይ የወጡ ኃይሎች በሙሉ አረመኔዎች እየሆኑ የመጡ ናቸው። ይህም ማለት አረመኔያዊነት የአገዛዞች መለያ ለመሆን በቅቷል። ይህንን አረመኔያው ድርጊትም የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል ትክክል ነው ብሎ በመቁጠር ወይንም ደንታ ስለሌለው አስረሽ ምችው በማለት ላይ ይገኛል። ከዚህ ስንነሳ የህገ-መንግስትን መሻሻል አጥብቀው የሚያነሱ ብዙ ያልገባቸው ነገሮች አሉ። በአሁኑ ወቅት በአገራችን ምድር ከፍተኛ የስነ-ልቦና ቀውስ ይታያል። በመንግስትም ሆነ ሌላ በተደራጀና በግለሰብ ደረጃም የሚሰሩት ወንጀሎች በሙሉ በጣም ይዘገንናሉ። በዚህ ላይ ይህ ሁሉ ግፍ እየተፈጸመና ሰፊው ህዝብ ወደ ድህነት እየተገፈተረ ባለአምስት ኮከብ ትላልቅ ሆቴልቤቶች ይሰራሉ። ከዚህም በላይ በአፍሪካ ውስጥ ትልቁ የአውሮፕላን ጣቢያ በመሰራት ላይ ነው። ይህ ሁሉ ነገር የሚካሄደው እዚያው በዚያው ወለጋና አንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ መጠነ-ሰፊ ግድያዎች እየተፈጸሙ ነው። ሌላው የሚነሳው ነገር ህግ-መንግስቱ ቢቀየርስ የፖለቲካ ስርዓቱን እንዴት ማስተካከል ይቻላል? ከዚህ ጋር ተያይዞ የመጨቆኛ መሳሪያ እየሆነ የመጣው የመንግስት መኪናውንና የሚቆጣጠሩትን ሰዎች ምን ልናደርጋቸው ነው? ህገ-መንግስቱ ከተለወጠ እነሱም ሊለወጡ ይችላሉ ወይ? እስካሁንስ የፈጸሟቸው ወንጀሎችስ እንዴትይ ይታያሉ? ይህንንና ሌሎች አያሌ ጥያቄዎችንና በአገሪቱ ውስጥ አፍጠው አግጠው የሚታዩትን ችግሮች በሙሉ የህገ-መንግስት መለወጥ ሊፈታቸው በፍጹም አይችልም። ስለዚህም ውትወታው ሳይንሳዊ ያልሆነና ሎጂክ የጎደለው ነው።

    ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)
    http://www.fekadubekele.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.