የሐገርን ኢኮኖሚ እየገደለ ያለው አዲሱ የብሄራዊ ባንክ ገዢ – ሳሙኤል ብዙነህ

ጎረምሳው ለአራት አመታት ይህል የጠቅላዩ የኢኮኖሚ አማካሪ ሆኖ ሰርቷል፤በውጤቱ ግሽበቱ ሰማይ ነክቷል እነ ቴሌ ተገዳዳሪ እንዲገባባቸው ተደርጓል ቴሌ ራሱም ጆሮ ግንዱ እንዲባል ተወስኗል የውጭ ባንኮች እንዲገቡ ድግሱ ተጠናቋል….
ጎረምሳው በጠቅላዩ ቢሮ ከአዝማቾቹ የተሰጠውን ሚሽን አጠናቆ በመቶ ቢሊየን ካፒታል ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሚባል ተቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆኖ ላለፉት አስራ ሁለት ወራት ሲሰራ ከርሟል፤ተቋሙ የመንግስት የልማት ተቋማትን በአንድ ላይ ሰብስቦ ለችብቸባ ማዘጋጀት እንደሆነ ውስጥ ውስጡን ይወራል….
ሰሞኑን ጎረምሳው በሚመራው ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ኩንታል ስንዴ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ወደ ኬኒያ ኤክስፖርት ማድረግ አለበት ተብሎ በጎረምሳው በተሰጠ ቀጭን ትዕዛዝ የኮርፖሬሽኑ ባለስልጣናት ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ላይ ናቸው፤ገበሬው በኩንታል ለዮኒየኖች በ3200 እንዲያቀርብ ዩኒየኖች ደግሞ ለኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን በ3378 እንዲያቀርቡ አስገዳጅ ተመን ቢቀመጥም ገበሬው አያዋጣኝም ብሎ ምርቱን አፍኖ ይዟል….
ገበሬው ምርቱን በለሊት እያወጣ ያዋጣኛል ባለው ዋጋ መሸጥን ምርጫው አድርጓል፤ስንዴም ወግ ደርሷት በኮንትሮባንድነት ተሰይማ ኬላ ተበጅቶላታል….ጎረምሳው ወደ ኬኒያ የሚላከው ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ኩንታል ስንዴ ካልተሳካ እዚህ ወንበር ላይ አትቆዩም እያለ በንግድ ስራ ኮርፖሬሽን ሃላፊዎች ላይ መዛት ከጀመረ ሰነብብቷል፤ኮርፖሬሽኑ እስከ አሁን የገዛውና ወደ መጋዛኑ ያስገባው ሃያ ሺህ ኩንታል ገደማ ነው….የኮርፖሬሽኑ ሃላፊዎች መስሪያ ቤታቸውን ለኪሳራ የሚዳርግ ስራ መሆኑን በኬኒያ የአንድ ቶን የስንዴ ዋጋን ጠቅሰው ቢከራከሩም ላኩ ላኩ አያገባችሁም ተብለዋል፤ዋናው የሚፈለገው ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ኬኒያ ላከች የሚለውን ዜና መስራት ነው ……..
ጎረምሳው ዛሬ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ሆኗል ተብለናል፤አዝማቾቹ የብርና የዶላር ምጣኔ አሁንም ልክ አይደለም መስተካከል አለበት የሚሉ ናቸው….ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ አንድ የአሜሪካን ዶላር በሁሉም የንግድ ባንኮች ከዛሬ ጀምሮ በመቶ አስር ብር ይመነዛራል ተብሎ ቢነገርህ እንዳትበረግግ
ሳሙኤል ብዙነህ
ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ብልፅግና አመራሮች ስብሰባቸው ላይ ተናገሩ ከተባለው!

3 Comments

  1. “በአግቦ የሚመታኝ ባገኝ ብትር ባቀበልኩ” ይላሉ አበው፡፡ትክክለኛ ትችቶች ሀገርን ያጸናሉ ዜጎችን ይቀርጻሉ፡፡ሁሉንም ድርጊቶች በጅምላ መኮነን ግን ጽንፈኝነትን እንጅ ለሀገርና ለዜጎች መቆርቆርን አያሳዩም፡፡
    “ሳሙኤል ብዙነህ” ለአንተ እድሉ ቢሰጥህ ማነን የብሔራዊ ባንክ ገዥ እንዲሆን ትመርጥ ነበር?

  2. ውድ ወንድሜ አቶ ሳሙዔል ያቀርበከው ማስረጃ በጣም ጠቃሚ ነው። እንዳልከው ሰውየው የጠቅላይ ሚኒስተሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ ነበር። እሱ ግን ማክሮ ኢኮኖሚክስ የሚለውን ትልቅ ጽነስ-ሃሳብ፣ አብዛኛውን ጊዜ በአገራችን የተሳሳተ ግንዛቤ ውስጥ የገባውን የሚጠቀሙበት የአገርን ኢኮኖሚ ከማሻሻልና ህዝቡን ከድህነት ከማላቀቅ ይልቅ የአገርን ሀብት ለውጭ ከበርቴዎች በመሸጥ የባስ ድሀነትን መፈልፈል ሆኗል ስራው። የዛሬ አንድ ዓመት ተኩል ገደማ Home Growth Economy የሚል “ፍቱን ዕቅድ” አወጣን ብለው ነበር። እሱም ቢሆን የውሃ ሽታ ነው ለመሆን የበቃው። አሁን ደግሞ የማዕከላዊ ባንኩ ዋና አለቃ በመሆን የእነ IMF ን ትዕዛዝ በመቀበል የኢትዮጵያን ብር ከዶላር ጋር ሲወዳደር የባሰውኑ በጣም ዝቅ እንዲል ያደርጋል ማለት ነው። ይህ በራሱ ደግሞ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ያስከትላል።
    ለማንኛውም ሰው እንዲገባው አጠር መጠን ባለመልክ ስላቀረብክልን ሳላመሰግንህ አላልፍም።

    ፈቃዱ በቀለ
    http://www.fekadubekele.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.