እነ ሲያልቅ አያምር! – ተዘራ አሰጉ ከምድረ እንግሊዝ

እንደሚታወቀው በአስተውሎት ፣ ታሪክን ተመርኩዞ ፣ እውነትን ሰድሮ፣ በቅንነት ፣ አማክሮና ተመክሮ የተጀመረና የተጓዙበት ነገር አዋጭ ከመሆኑ ባሻገር ይከበሩበታል ፣ ይመሰገኑበታልና አንፃራዊ ሰላምንም ያጎናፅፋል።

በተቃርኖ በሸር ፣ በተንኮል ፣ በመሰሬነት ፣ “ከኔ ወዲያ ላሳር”ና “ እኔ አውቅልሃለሁ” በሚል ህሳቤ የተጀመረና እያደር ሸሩ ፣ ተንኮሉና ሻጥሩ ዐይን አውጥቶ ሊተገበር ሲሞከር ጣጣው ብዙ ፣ ውርደትን የሚያላብስ ፣ የሕዝብ እምቢተኝነትን የሚያስነሳና ሰላም መውጫ ቀዳዳ አጥታ ምድሪቱ በጣርና በሰቆቃ ጊዜዋን እድታሳልፍ ምክንያት ይሆናል።

በኢትዮጵያ የሶስት ሺህ ዓመት ታሪክ ነገሥታት መጥተዋል ፣ ወደ ማይቀርበት ዓለምም ተሸኝተዋል ፣ ቋሚ ሁነው አልኖሩም ፣ ሰዎች ናቸውና።
አንዳንዶቹ መሪዎች በሰሩት መልካም ምግባር በትውልድ ልብ የታተሙ ፣ ሐውልት ታንፆላቸውና የታሪክ መነባንብ ተከትቦላቸው ለዘመናት ስማቸው ከመቃብር በላይ ህያው ሆኖ የሚዘልቁ አሉ።

በሃገራችን ታሪክ ከቀደምቶቹ በእግዚአብሔር ከተቀቡ ነገስታት መካከል ጥቂቶችን ለመጥቀስ ንጉስ ላሊበላ፣ ዐፄ ፋሲል ፣ ዐፄ ቴዌድሮስ ፣ ዐፄ ዮሃንስ ፣ ዐፄ ሚኒሊክ ፣ አሊ ሚራ ፣ ጅማ አባ ጁፋር ፣ ንጉስ ጦና ወዘተ ይገኙበታል ።

ከዚህ በተፃራሪ አንዳንዶቹ መሪዎች ሥልጣን ላይ ቁብ ሲሉ በስልጣኑ ላይ ለዘለዓለም ተሰይመው የሚኖሩ ይመስል በሕዝብ ላይ ግፍ ሲሰሩ ፣ የወጡበትን ማህበረሰብ ሲንቁ ፣ ሃገርን በጋራ ያቆሙ ተቋማትን እሴቶች ሲሸረሽሩ ፣ ሲያንጓጥጡ ፣ ሲከፋፍሉ ፣ ወገንተኛነት ሲያስፋፉ ፣ የብሄርን ፅንፍ የሚያቀነቅኑና ከሰሩት መልካም ስራ ይለቅ እፀፃቸው ሚዛን የደፋ ፣ በክፉ እንደ ተነሱ የዘለቁ መሪዎች ነበሩን፣ ብቅ ብቅ ብለው የታዮም አሉ ፣ አሁንም በእውን እያየ ናቸው ነው።እየታዮም ያሉም አሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ደመቀ መኮንንና ተመስገን ጥሩነህ፤ ያማራ ሕልውና ዋና ጠላቶች

ከሃያኛው ክፍለ ዘመን ወደ ኋላ ባሉት ዘመናት የነገሱትን ነግስታቶች በክፉ ለማንሳት የሚያስቸግር ከመሆኑ ባሻገር የአሁኑ ትውልድ ውጤት የሆኑት የሃገራችን መሪዎች የእግዚአብሔር ኃያልነትን የሚዳፈሩ ፣ ለሃገር አንድነት ደንታ ቢስ በመሆናቸው ፣ ከአፋቸው የሚወጣው ቃል ፃያፍ ፣ ንቀት የተሞላበት ፣ የሰው ደም ካልፈሰሱ መንቀሳቀስ የተሳናቸው “ የደም ሱስ” ያለባቸው፣ ውሸት ፣ ሸረኝነት ፣ ክህደት ፣ ድፍረት ወዘተ የተላበሱ በመሆናቸው የኒያን የደጋግ ያለፉትን ዘመናት መሪዎችን ወደ ኋላ ተመልሰን ለመተቸት አይዳዳምን ። ከኢምንት ስህተታቸው የሰሩት መልካም የአንድነት ፣ የሰላም ፣ የመከባበር መንፈስ ፣ የፍሪሃ እግዚአብሔር ድማሜያቸው ፣ ለሃገር ባንዴራ ሟችነታቸው ፣ ለዳር ደንበር ዘብ መቆማቸው ፣ ለሕዝብ የሚሰጡት ከበሬታና የሃይማኖት ቀናይነታቸው አጃየብ የሚያሰኝ ስለነበር።

እንግዲህ የዘመኑ የብልፅግና መሪዎች “እኛ ያልጋገርነው አይቦካም ፣ ያልባርክነው አያፀድቅም” በሚል እጓጉልና ኋላ ቀር ህሳቤ ከላይ ከአናቱ ጀምሮ በተዋረድ በየመዋቅሩ እንደ “እርጎ ዝንብ” ጥልቅ ከማለት ባሻገር አምባገነን ሁነው እየታዮ ነው ። የፉረንጆችን አባባላዊ ጥቅስ መጥቀስ ባይመችም ማወቁ መልካም ነውና እንንገራቸው

Autocratic leadership known as autocratic leadership, is a management style in which an individual has total decision-making power and absolute control over his subordinates. An authoritarian leader makes decisions on policies, procedures and group objectives with little or no input from his or her team members or followers”

ከላይ የሰፈረው ማጣቀሻ የሚያስተምረንና በዚህ ሰሞን የምናየው የሃገራችን ምስቅልቅል መነሻ ምክንያቶች ቁንጮ ያሉ የኢትዮጵያ መሪዎች የሕዝብን ፍላጎት ሳያማክሉ ፣ የተለያዩ ተቋማትን ሙያዊ ምክር ሳያሰባስቡ ፣ ሊመጣ የሚችለውን ጉዳት ወዘተ ሳያመዛዝኑ እራሳቸውን ጻጻስ ፣ ምሁር ፣ ወታደር አድርገው ቀብተውና ሹመው “_የእኛ ቃል የፈጣሪ ቃል” ነው በሚል የወረደ ህሳቤ “ከድጡ ወደ ማጡ” እንዲሉ ሃገረ ኢትዮጵያን ልትወጣው ወደ ማትችለው አዝቅት ሊከቷት እየሞከሩ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Health Care Customer Service Representative

ገዳይና እስገዳይም በግለሰብ ፣ በመሪና በቡድን ደረጃ የሕዝብን የደማ ልብ በይቅርታ ሳያለሳልሱ ፣ በጦርነት ያለቀውን ወጣት ለወላጆቻቸው መርዶ ሳይነግሩ፣ ደምር ሳይደምሩ፣ ፍትሃት ሳያስፈቱና ካሳ ለሚገባው ካሳ ሳይሰጡ ሕዝብን በመናቅ እየተሳሳሙ ፣ እየተሳለቁና የውስኪ ብርጭቆ በማን እለብኝነት እያጋጩ ነው። “እምላክ ወይ ውረድ ፣ ወይ ፍረድ” እንላለን።

እንግዲህ “ሲያልቅ አያምር” እንዲሉ ያለፉት የቅርብ ጊዜ የዚህ ጥቅስ ሰለባ የሆኑትን መሪዎቻችን ግጥምጥሞሽ ስንዳስስ ጓድ መንግስቱ ኃይለማሪያም ምንም በሃገር አንድነት ፣ ባንዴራና ደንበር ባይደራደሩም የስልጣን ወንበራቸው ሲንገጫገጭ “ ይህ ወርቅ ቢያነጥፉለት ፋንዲያ የሚል ህዝብ“ ብለው ስንኝ በአፍ ወለምታ ደርድረውና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ተሳልቀው እንደነበር ይታወሳል ፣ የኢትዮጵያ አምላክ ሰማ ከዚያ የሰሩት መልካም ምግባር አመዝኖ ይሆን አይታወቅም ነብሳቸው ተርፋ የውርደት ካባ ተከናንበው ለስደት ተዳረጉ ፣ አብረዋቸው ሲያሸረግዱ የነበሩትም ጓዶቻቸው እጃቸው ተጠርንፎ ወደ ከርሸሌ ተወረወሩ።

ታጋይ መለስ ዜናዊ “ሳይንካካ ተቦካ” እንዲሉ ገና ከበርሃ መጥተው በዕድል የስልጣን ኮረቻ ላይ ቁብ ሲሉ የኢትዮጵያ የአንድነት ምልክት ፣ ከአምላክ የተበረከተላትን መለያና የቅድስት ማሪያምን መቀነት አምሳያ የሆነውን አረንጓዴ ፣ብጫና ቀይ ባንዴራ “ጨርቅ ነው” አሉ የድንግል ማሪያም ልጅና የኢትዮጵያ ጠበቃ የሆነው አምላክ ግን ይህ ንግግራቸው ስላላስደሰተው “የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም” እንዲሉ በቁማቸው እንደቃዡ ፣ በስህተታቸው እንደባነኑና እየመነመኑ የሕዝብን ክብር አጥተው ወደማይቀርበት ዓለም ተጓዘ ፣ ታጋይ ጓዶቻቸውም በማይሆን መልኩ ለክብር ቀብር ሳይበቁ በርሃ ላይ ቀሩ ።እንዲያውም በአንድ ወቅት “ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን እዳትነሳ እርገን ቀብረናታል” ብለው ቀባዥረው ነበር ነገር ግን ማን እንደተቀበረ አምላከ እግዚአብሔር በቁም አሳይቶናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኦባማን እምባ ለእነዚህ በኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ የተነሳ በአጋዚ ሰራዊት ለተገደሉት ሕጻናት እንዋሰው | ቪዲዮ

እንግዲህ ወደ አሁኖቹ ዘመነኛና በቅብ / በአስመሳይነት/ ክርስቲያን የሚመስሉ በግብር ግን አልቦ የሆኑ መሪዎቻችንን ስንቃኝ ፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን ከኩነቶች ጋር አገናዝበን የምናጣቅስላቸው ማጣቀሻዎች አሉን እነሱም “ የማይነካውን ነካቺሁ ፣ ማኖ ነካችሁ፣ ሲያልቅ አያምር” ወዘተ እያልን እንሸረድዳቸዋለን “ለንጉስ ዐፄ ሤስኒዮስ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ አይማኖታዊ ቀኖናንና መሰረት ለመለወጥ የሞከሩትን አይነት ተጋፋጭ፣ ለእምነቱ ቀናይ የሆነ የንግሥና ውርስ ልጅ አይነት እንደ ዐፄ ፋሲል ያለ ንጉስ አምላክ ቀብቶ ለኢትዮጵያ እስኪሾም ድረስ” ታላቅዋን፣ አለምአቀፋዊዋን ፣ በጌታ ፍቃድ ተመስርታ ለኢትዮጵያውያን ፊደል ቀርፃ ፣ ቀናቶችን ቀምራ ፣ በአምላክ ስም አጥምቃና ቃለ እግዚአብሔርን አስተምራ ከሺህ ዓመታት በላይ የዘለቀችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እነሱ የተናገሩትን ፀያፍ አባባልና ድፍረት የተሞላ ቃል መከተቡ ስለሚሰቀጥጥ ለኢትዮጵያና ለአማኙ ህዝብ የህሊና ፍርድ ትቸ የሚሆነውን እየጠብቅን በንፅህና እየፀለይን የአምላክን ፍርድ እንጠብቅ እንላለን።

በመጨረሻም “ፍርድ ሰጭ አምላክ እንጂ ሕዝብም ሰውም ስላልሆነ” የአምላክን ፈቃድ ፣ በጎነትን ፣ ፍርድና አስተምህሮትን እንጠብቃለን። “ልብ ያለው ልብ ይበል “ ና “ ካለፈው የሚማር ይማር” እንላለን። “እነ ሲያልቅ አያምር” አይነት ፍርድ እንዳያጋጥማችሁ እንመክራለን።

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.