ከታሪክ ማህደር: ከፍተኛ 15 (ካዛንችስ/ባንቢስ) አድማ ግድያ 45ኛ ሙት ዓመት መታሰቢያ – ያ ትውልድ

ያ ትውልድ ቅጽ 10 ቁጥር 2
የካቲት 04 ቀን 2015 ዓ.ም.

በድምጽ ለማድመጥ እዚህ ይጠቁሙ ( www.yatewlid.org/images/mp3/H15Adma.mp3) ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ነው። ልክ የዛሬ 45 ዓመት ቀኑ የካቲት 4 ቀን የዋለው ቅዳሜ ነበር።ይህ ቀን ለእኛ በተለይ በደርግ ቀይ ሽብር ዘመን ከፍተኛ 15 እስር ቤት ለነበርነው እጅግ መሪር ትዝታ አለው። ቀኑን እንደያ ትውልድ ወገንተኛነታችን ማሰብና ነፍስ ይማር ማለት እንገደዳለን። ሁኔታው በአቶ ነሲቡ ስብሐት መስከረም 2007 ዓ.ም. ተጽፎ ለንባብ ከበቃው “ፍጹም ነው እምነቴ ቀይ ሽብር የከፍተኛ 15 እውነተኛ ታሪክ” ግጽ 227 “2.14 የከፍተኛ 15 አድማ ተብሎ ግድያ” በሚል ርዕስ ሥር የቀረበውን ከነድምጽ ቅጂው ለማስታወስና ሰማዕታቱን ለመዘከር አቅርበንላችኋል። —[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]-

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ወራሪው ማን ነው? ተወራሪዎቹስ? (ፈለገ-አሥራት)

3 Comments

  1. የከፍተኛ 15 የቀይ ሽብር አረመኔ ነፍሰገዳዮች ታሪክ ሲወሳ ራሴ የታሰርኩበት የከፍተኛ 23 ነፍሰገዳዮች ታወሱኝ:: በተለይ በርሄ የሚባለው የከተማ ልማት ተጠሪ ቀን አመሻሽ ላይ መጥቶ ዛሬ ማታ ድራማ ይኖራል ብሎ በትንሽ ወረቀት ላይ እየዞረ የሚገደሉትን ወጣቶች ስም ይጽፋል ግማሾቻችን በቶርቸር ግርፋት በቆሰለ እግራችን ላይ በጭካኔ ይራመዳል:: በዚያን ጊዜ መርማሪ ከነበሩት ድሮ ከፍተኛ 3 ይኖር የነበረው መስፍን በዙ ክፉኛ የገረፋቸው የኤርትራ ታጋዮችና የከፈተኛ 2 ደረጃ ተማሪዎች አይቀርልንም ብለው በስጋት ይጠብቁ ነበር::
    ምሽት ላይ ገዳዮቹ እነበርሄ ሃምሳ አለቃ ሺፈራው ሌሎቹም ወጣቶችን ለመግደል ድፍረት ያገኙ ዘንድ የጠጡት ኡዞና ጂን አልኮል እየሸተተን በላንድ ክሩሰር ከታሳሪ በተዘረፈ ሲመጡ ከፈተኛ የሃብታም ነጋዴ የቡና መጋዘን የነበረው በሩ በስፋት ይከፈትና ዘምሩ ይሉናል::” መራራው ትግል” እያልን ስንዘመር በርሄ ከወረቀቱ ላይ ሲጠራ- ይጥና አብሬ ግርማ ወልደአብ አባተ ይርዳው እያለ ሲጣራ አባተ እንዳይታሰር ጠፍቶ የነበረ ሲጠራ ዲጎ አላልኩሽም አልቀረልኝም ቻዎ ብሎኝ ሲሄድ እምባ ከአይኔም ከአፍንጫዬም ፈሰሰ:: ጌቱ የተባለ የቄራ ልጅ ደግሞ አዲስ ነጠላ ጫማውን ይህን ለእማዬ ስጡልን ብሎ በርሄ እየደበደበ በኡዚው ሰደፍ እየደበደበ ወሰዳቸው:: ብሩክ ፈይሳ በተለይ ከግርማ ወልደአብ ጋር ለእናት ሃገር ጨረታ በከፍተኛው እስር ቤት በጣም የተሳተፉ ተወስደው ተገደሉ:: ጠዋት ድረስ ደማቸው ፈስ ሶ ሌሊት ተቀስቅሰን ፊታችኝ ስንታጠብ እንድናየው ተደረገ:: በዚህ ወቅት ጭንቅላቱን ብዙ የተደበደበ ፈዋዱ የሚባል የሞዝቮልድ ሰራተኛ የሚጥል በሽታ ተይዞ ምንም የኢህአፓ ተሳትፎ የሌላቸው ጌቱ ጆሮ የሚባል የቄራ ልጅ”” ሆጃዬ ሆጃ” የማኖ ዲማንጎን ዘፈን የሚጫወትልን በኢህአፓ የማጋለጥ ሂደት በመዋቀሩ ውስጥ የሌለ ክፉኛ ሲገረፍ አሰር ሃያ ገደልኩ የሚለውን ወስደው አረዱት::
    ዛሬ በህይወት ያሉ እነመስፍን በዙ የወያኔ አፈቀላጤ የሆኑ ሳያፍሩ በአሜሪካ ሲኖሩ ቀልቤሳና ከፈለኝ ከርቸሌ አብረውን የታሰሩ ለፍርድ በቅተዋል:: ያልታሰሩትን በውጭም በሃገር ውስጥም ያሉትን ከናዚ ወንጀለኛ ያላነሰ ግፍ የፈጸሙትን ማጋለጡ ለፍርድ ማቅረቡ ይቀጥል::
    እኒያ ወጣቶች ያለምንም የዘር ልዩነት ያደረጉት የፍ ት ህ ትግል ዛሬ በተረኛ ግፈኛች ሰው በዘሩ መጠኣቱ መታረዱ መፈናቀሉ ይባስ ብሎ በቤተሃይማኖት ሴራው መግባቱ ሊወገዝ ሊቆም ይገባዋል:: ሃቀኛ ሚዛናዊ የእርቅና የሰላም ጉባኤ ልባቸው የተነካ ለሚናዘዙት ይቅርታ የሚያሰጥ በሃገራችን ይጀመር:: ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው የዚያ ትውልድ ተራፊ ከሚድ ዌስት አሜሪካ

  2. ጊዜው የደርግ ዘመን ነው፡፡ ጉዳዪ የሆነው በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎች ከዚህም ከዚያም ተለቅመው ታጉረዋል፡፡ በጧቱ የደርግ ባለስልጣን ወደ ከተማው ገብቷል እየተባለ ይወራ ጀመር፡፡ ቀኑ ላይ ያ የተወራለት ሰው በገጠር ታጣቂዎችና በስፔሻል ፎርሶች ታጅቦ እስረኞቹ ባሉበት ግቢ ይገኛል፡፡ ስሙ ሻለቃ ገብረህይወት ይባላል፡፡ አይኑ ሁሉን እሰረኛ እያየ ቆዪ ዋጋቹሁን እሰጣችኋለሁ በማለት አጠገቡ የቆመውን መርማሪ ወደ ጅሮው ጠጋ ብሎ ሲያናገር እሺ እሺ ይላል እያዳመጠ፡፡ ማታ በድንገት መኪና ግቢው ውስጥ ይገባል፡፡ የእስር ቤቱ በር ተከፍቶ ስማችሁ ሲጠራ ውጡ በማለት ስም መጥራት ጀመረ፡፡ ልክ የተጠራው ሲወጣ ድው የሚል ነገር ይሰማል፡፡ ግን የጥይት አይደለም፡፡ የስም መጥራቱና የሚሰማው ነገር ቀጥሎ ትንሽ ከቆየ በህዋላ ቆመ፡፡ የእስር ቤቱም በር ተመልሶ ተዘጋ፡፡ ስማቸው የተጠራው ሰዎችም ሳይመለሱ ቀሩ፡፡ በጧቱ አንድን የሌሊት ጥበቃ ፓሊስ የእስረኞች አለቃ (ራሱም እስረኛ የሆነ) ጠጋ አለና ማታ ምንድን ነው የሆነው? ያ ይሰማ የነበረው ነገር ከየት የመጣ ነው? ተው ሃገር አለኝ አትበል፤ የሆነው ይህ ነው፡፡ እስረኞችን ከመገደላቸው በፊት እጃቸውን የምናስርበት ፌሮ ባለመኖሩ ልክ እንደ ወጡ በመዶሻ ጭንቅላትና ደረታቸውን የሚመቱ ሰዎች ከመቷቸው በህዋላ አራት ፓሊሶች እግርና ጭንቅላታቸውን ይዘው የፓሊሱ ማርሰዲስ ላይ ይጫናሉ፡፡ ከዚያ አንድ ገደል አፋፍ ላይ ተወስደው ተደፉ፡፡ ጥይት አናባክንም ተብሎ በዚሁ ሰዎቹ ተሸኙ፡፡ የተረፋችሁትን ፈጣሪ ያድናችሁ፡፡ እኔ ወደ ሱዳን መጥፋቴ ነው በማለት ያ ወታደር እንደገና ወደ ጥበቃው ሳይመለስ ቀረ፡፡
    ሻለቃ ገ/ህይወትም ከደም አፍሳሹ መላኩ ተፈራ ጋር ወደ ሁመራ በወታደራዊ ሄሊኮፕተር ሂደው ገ/ህይወት ሳይመለስ ቀረ፡፡ በደረሰው የአየር አደጋ ሻለቃው ሞተ ተብሎ ታንቡርም ባይመታም እንደ ማርሽ ነገር እያሰሙ በራዲዮ ተደሰኮረ፡፡ ይሁን እንጂ በሁለቱ ሻለቆች መካከል መናናቅ ስለነበር አንድ ሌላውን እንደበላው ይወራል፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ግፈኞች ያኔም አሁንም አሉ ወደፊትም ይኖራሉ፡፡ በደርግ ዘመን ስለሆነው ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ ስለ ድብደባው፤ ስለ ህክምናው፤ ስለ ልዪ ምርመራው፤ ስለ ሴት መድፈሩ፤ የፓርቲ ሚስጢር አናወጣም ብለው እግራቸውና መላ አከላታቸው ከድብደባው ብዛት የተነሳ ጨርቅ ሆኖ በጥይት ጭንቅላታቸው ተቦዳድሶ በየመንገድ የተጣሉ ቁጥራቸው ብዙ ነው፡፡ ግን ዛሬስ ቢሆን እርስ በእርስ መጨካከናችን መቼ ካለፈው ሰቆቃ ተምሮ ሰውን በሰውነቱ ያከብራል? ኦ ስንት ግፍ ያኔም ዛሬም ተሰራ፤ ይሰራል? ይቆም ይሆን? አላውቅም፡፡

  3. ሞረቴው ጥሩ ዘግበህልናል አንድ አምድ ይዘህ በዛን ሰው ባበደበት ጊዜ የሆነውን ወደፊት እንዳይደገም ብትዘግብልን ትውልድ ትምህርት ያገኛል ግን ሁለታችሁ ከጻፋችሁት ላይ ሞረቴው ከጻፈው በርሄ ተስፋ ከጻፈው ገ/ህይወት የተባሉት ትግሬዎች ናቸው ኤርትራኖች፡፡ የሞረቴው ግልጽ ያለ ሲሆን የተስፋው ለመረዳት ምርምርና ማብራሪያን ይጠይቃል፡፡ ሞረቴውም ሆነ ተስፋ በዛ ደረጃ ከታሰራችሁ እንዴት ተረፋችሁ ብሎ መጠየቅም አግባብ ይሆናል ለማንኛውም በህይወት መቆየታችሁ መልካም ሁኖ አሁንም መልካምን ስበኩ ፡፡ተስፋ ባየው ነገር ተነክቶ ይሁን ወይም ትግሬ ይሁን አላውቅም ሃሳብ ሲሰጥ የሚጎትተው ነገር አለው ቁጣም ያበዛል ሰው በዘመኑ ሲጎዳ ስላየ ቴራፒ ነገር ቢያገኝ መልካም ነው፡፡ ተስፋ “ሻለቃ ገ/ህይወትም ከደም አፍሳሹ ሻለቃ ተፈራ ስትል” ሻለቃ ገ/ህይወት ጥሩ ትግሬ ነበር ማለት ነው? ይሄ ነገር ድፍን ያለ ነገር ሁኖ መረዳት ከብዶኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.