የእሁድ እንጉርጉሮዬ – የእሁድ እንጉርጉሮዬ

የእሁድ እንጉርጉሮዬ

ጨለማው ረዘመ~ ምንም አልታየን፣
ጀንበር ብልጭ ብላ~ቀን በወጣልን።
በረጅም ሩጫ ~ ኖረን ስናሸንፍ፣
ወደ ሁዋላ ሆነ ~ላጭሩ ስንከንፍ ።
በጊዜ ውንበዳ~ መላ የለው ዘንድሮ፣
ቤተሰላም ሆነ~ጉልት ላምባጉሮ።
ስንበሌጥ ከመርን~ በጊዜ ገለባ፣
ድንጋይ ቤት አፍርሰን~ጎጆ ልንገነባ ::
ጸጥተኛ ቦታ ~ የነበረ ብቻ፣
በድንገት ሆነብን ~ አመጽ መዶለቻ።
ምን ይለው ነበረ~ ዋናው አስተማሪ፣
ትምህርቱ ሲጠፋ ~ ሳይቀር ፍርፋሪ?
ከመቶዎች በፊት ~ታሪክ መዝገቦታል፣
ጠብ መንጃና መስቀል~አንድ ላይ አይቶታል።
ማነው ተው የሚለው~ ሰላምን መካሪ፣
ሽማግሌ ሆኖ ~ዋናው ጸቡን ጫሪ ?
እንዴት ይጸለያል~ወዴት እንባ ይረጫል?
አስታራቂ የነበር~ ቀን በቀን ያጋጫል።
መለዮውን ጥለው~ ሥልጣን ላይ ሲወጡ፣
እልቂትን ነው እንጂ~ሰላም መቼ አመጡ?

አሸናፊ ዋቀቶላ፣ ሕ/ዶ – ፌብሩዋሪ 11፣ 2023

 

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  አሳማ! - በላይነህ አባተ

1 Comment

  1. Wonderful poem. My message to the messenger of evil is this:

    ለጨረታ አቅርበህ ያገር ሃብት አንጡራ
    በለውጡ ሸምተህ የብረት አሞራ
    ዲሽቃና ቆንጨራ
    ከንቱ ብትኩራራ
    ጽዋው አያልፍህም ኑክሌር ብትሠራ
    የእንባ የደም ጎርፉ
    አልፎ ከገደሉ ዘልቆ ከገደቡ
    የፈጣሪ ጣቶች
    ማኔ ቴቄል ፋሬስ ጽፈዋል በግንቡ
    ካምናም በላይ ዛሬ ፈርዖን ደንድነሃል
    በጌታ ደጆች ላይ ሰይፍህን መዝዘሃል
    እውነትም ጠርቶሃል የነሂትለር ቢጋር
    እዚያው ሲዖል ወርደህ ትጫወታላችሁ ከሙሶሎኒ ጋር

Leave a Reply

Your email address will not be published.