ይድረስ ለኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት/ፓርላማ/

አሸባሪውን ትህነግ/ወያኔ በአሁኑ ሰአት ከአሸባሪነት መዝገብ ማንሳት ታሪካዊ ስህተት ነው!

ትህነግ/ወያኔ ከፍጥረቱ ጀምሮ ፀረ-ኢትዮጵያ ሆኖ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡ በተለይም የአማራን ህዝብ እንደ ቀዳሚ ጠላት ፈርጆ መነሳቱ በታሪክ የተመዘገበ እውነታ ነው፡፡ ሴረኝነት፣ ጸረ-አማራነት፣ ተስፋፊና፣ ተገንጣይነት የዚህ ድርጅት መገለጫ ባህሪያት ናቸው፡፡ ይሄን እውነታ ከትህነግ ማንፌስቶ ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ ኢትዮጵያን በበላይነት በገዛባቸው ሃያ ሰባት ዓመታት የአገዛዝ ባህሪው፣ የተጠኑ ሴራዎቹና በሕዝብ ደም ፖለቲካ የመስራት ደመ-ቀዝቃዛ ድርጊቶቹ መረዳት ይቻላል፡፡

የዚህ እኩይ ባህሪው ጥቅል መገለጫ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች ውህድ ማንነት የሆነውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከጀርባ የወጋበት፣ በኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች ልጆች ላይ በከፈተው ጦርነት የውጭ ኃይሎች ረዥም እጃቸውን ሰደው ኢትዮጵያውያን እረፍት እንዲነሱ ያደረገበት ሁኔትና የሄደበት እርቀት የኢትዮጵያና ሕዝቦቿ የክፍለ ዘመኑ ትልቁ የመከራ ምንጭ ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል፡፡ ይህ የባንዳነት ወንጀል ከታሪክ፣ ከሞራል፣ ከሕግ፣ ከፖለቲካ፣ ከብሔራዊ ጥቅም፣…ወዘተ አንፃር በኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች ዘንድ ይቅርታ የማያሰጥ የክፍለ ዘመኑ ታላቅ ወንጀል ነው ብለን እናምናለን፡፡

አሸባሪው ትህነግ/ወያኔ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የሰሜን ዕዝ አባላትን በተኙበት በመጨፋጨፍ የጀመረውን የሽብር ጥቃት በተከታታይ 3 ዙር ጦርነቶች በ2 አመት ውስጥ በማካሄድ በሀገራችንና በህዝባችን ላይ አይተነውና ሰምተነው የማናውቀውን አይነት ሰቆቃና እልቂት ፈፅሟል። በሚሊዮን የሚቆጠር ሰላማዊ ህዝባችን ለሞት፣ ለአካል ጉዳትና፣ ለመፈናቀል ተዳርጓል። ህለቆ መሳፍርት የሌለው የሀገርና የህዝብ ሀብት ወድሟል።

ልሳነ ግፉዓን ድርጅት ጥቅምት 23/ 2015 ዓ.ም ፕሪቶሪያ ላይ የተፈረመው የሰላም ስምምነት ከእነ እንከኑም ቢሆን ሙሉ በሙሉ ተግባር ላይ ከዋለ ሀገራችንን ወደ ሰላም ጎዳና ሊወስድ ይችላል የሚል እምነት ስላደረበት በወቅቱ “ኢትዮጵያችን ዳግም
በአሸናፊነት፣ በታላቅ ድልና፣ በግሩም ልዕልና በጠላቶቿ መቃብር ላይ ከፍ ብላ ቆማለች!” በማለት ድጋፉን መስጠቱ
ይታወቃል(መግለጫውን እዚህ ይመልከቱ)።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ታሪክ ይፋረደናል! - አንዱዓለም ተፈራ - የእስከመቼ አዘጋጅ

በተለይም በሰላም ስምምነቱ የተካተቱ አብዛኛው አንቀፆች በግልፅና በማያሻማ ሁኔታ የተቀመጡና ተግባር ላይ ሲውሉም በማንኛውም አካል ሊታዩና ሊዳሰሱ የሚችሉ እርምጃዎች የተካተቱበት ሰነድ ነው ብሎ በመቀበል ለተግባራዊነቱ ግልፅ ድጋፉን ሲሰጥና ሂደቱንም በቅርበት ሲከታተል ቆይቷል።

በአንፃሩ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ አሸባሪው ትህነግ/ወያኔ ከሰላም ስምምነቱ ውጭ በመሄድ የሚያደርጓቸውን ከመርህና ከህግ ውጭ የሆኑ እንቅስቃሴዎችንና ግንኙነቶችን በመቃወምና የሰላም ስምምነቱ በተደጋጋሚ መጣሱን በሚመለከት “መርህና ሕግ ያልተከተለው የብልፅግና መንግስትና የትህነግ/ወያኔ ግንኙነት በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል!” በማለት የተቃውሞ ድምፃችንን ስናሰማ መቆየታችን ይታወቃል (መግለጫውን እዚህ ይመልከቱ)።

ይሁን እንጂ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ጀምሮ ተግባር ላይ በማዋልም ሆነ አሸባሪው ትህነግ ለፈረመው ዓለም ዓቀፍ የሰላም ስምምነት ተገዥ እንዲሆንና ለሀገሪቱ ህግና ስርዓት ተገዥ እንዲሆን ከማድረግ አንፃር በመንግስት በኩል ምንም አይነት መሻሻሎችም ሆነ ተሰፋ ሰጭ እርምጃዎች የማይወሰዱ መሆናቸው በእጅጉ አሳስቦናል። ይልቁንም አሸባሪው ትህነግ/ወያኔ፦

1ኛ. የስምምነቱ አንቀፅ 6 “Disarmament, Demobilization, and Reintegration (DDR)” የሚለው ክፍል በግልፅና ሙሉ በሙሉ በተጣሰበት፤ ትህነግ/ወያኔ ትጥቅ ባልፈታበትና ተዋጊዎቹን በሙሉ ወደ ተሃድሶ/ማሰልጠኛ ማዕከላት ባላስገባበት ሁኔታ፣

2ኛ. የስምምነቱ አንቀፅ 10 “Transitional Measures” የሚለው ክፍል ሙሉ በሙሉ በተጣሰበትና በትግራይ ሁሉን ባለድርሻ አካላት ያካተተ አዲስ የሽግግር አስተዳደር ባልተቋቋመበትና በሂደቱም ላይ ሁሉን አቀፍ ተቃውሞ በነገሰበት ሁኔታ፣

3ኛ. የስምምነቱ አንቀፅ 7 /Confidence-building measures/ የሚለው ክፍል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ትግራይን ተረክቦ ሰላም እንዲያስከብርና ከሁሉም የተወጣጣ የአካባቢ ሚሊሻና የክልል ፖሊስ እንደሚዋቀር በፕሪቶሪያው ላይ በግልፅ ተደንግጓል። ይሁንና ከስምምነት ውጭ በሆነና ምክንያቱ ለህዝብ ባልተገለጠበት ሁኔታ በአሁኑ ሰአት ትግራይ ውስጥ የነበረው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አካባቢውን ለትህነግ/ወያኔ አስረክቦ በከፍተኛ ቁጥር ከትግራይ በወጣበት ሁኔታ፣

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሬየን አልሸጥም - አጭር ወግ - በሄኖክ የሺጥላ*

4ኛ. በተከታታይ በተደረጉ 3 ዙር ጦርነቶች ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱት የአፋርና የአማራ ክልሎች ከጦርነቱ ጉዳት ባላገገሙበት፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ባልተመለሱበትና፣ ትህነግ/ወያኔ የአማራ መሬቶችን በወረራ ይዞ በሚገኝበት ሁኔታ፣

5ኛ. ትህነግ/ወያኔ አሁንም የአማራ ክልልን፣ አፋርንና፣ ኤርትራን ለመውረር የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመና ቅስቀሳ እያደረገ በሚገኝበት ሁኔታ፣

6ኛ. ከሁሉም በላይ የሰሜን ዕዝ አባላትን በግፍ የጨፈጨፉ ወንጀለኞች ተጠያቂ ባልሆኑበትና የሰማዕታቱ ደም ፍትህ ባላገኘበት ሁኔታ፣

7ኛ. የሀገር አንድነትና ሰላም ለማስከበር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበለትን ሀገራዊ የክተት ጥሪ ተቀብሎ የዘመተውና የተሰዋው የኢትዮጵያ ጥምር ጦር አባላት ክቡር ደም ባልደረቀበትና ከሀዘናችን ባልተፅናናንበት ሁኔታና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ህልውና አደጋ ዋነኛው ምንጩ ትህነግ/ወያኔ መሆኑ እየታወቀና ዛሬም በአንድ አገር ሁለት የታጠቀ ኃይል ባለበት ሁኔታ!

በአጠቃላይ ትህነግ/ወያኔ በዓለም ዓቀፍ መድረክ የፈረመውን የሰላም ስምምነት ባለከበረበትና ለሰላም ያለውን ፍላጎትና

ቁርጠኝነት ባላሳየበትና ባለስመሰከረበት ሁኔታ የብልፅግና መንግስት በተለይም የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሽብርተኝነት መዝገብ ለመሰረዝ በነገው እለት ማለትም መጋቢት 13/2015 ዓ.ም በፓርላማ ውይይት እንደ ሚደረግበትና

ድምፅ እንደሚሰጥበት በተጨባጭ መረጃዎች አረጋግጠናል።

ስለሆነም በዚህ ታሪካዊ ወቅት ሰፊውን የኢትዮጵያ ህዝብ ወክላችሁ በተከበረው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆናችሁ የህዝብ ልጆች!

ከላይ በዝርዝር ያቀረብናቸውን ምክንያታዊና ተጨባጭ የህግ፣ የመርህና፣ የሞራል ሁኔታዎቸን ግምት ውስጥ በማስገባትና

ከፓርቲ አባልነትም ሆነ ውክልና በላይ የሆነውን ሀገራዊ ግዴታችሁና ሃላፊነታችሁ በማክበር ፣

ፀሃይና ቁር ሳይበግረው ረዥም ሰዓተት ተሰልፎ ድምፁን ለሰጣችሁ ለጀግና ህዝባችሁ ታማኝ በመሆን፣

ለታላቋ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ሰላምና፣ ደህንነት መረጋገጥ ዘብ በመቆም፣

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጭንቀላት ሥጋ መብሰሉ ለማይቀረው እንጨት ይፈጃል - ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ከሁሉም በላይ የተከበረውን ምክር ቤት ሀገራዊ ጥሪ ተቀብሎ በደሙና በአጥንቱ ሀገሩን ከአሸባሪው የትህነግ/ወያኔ ወረራና ጥቃት የታደገውን የኢትዮጵያ ጥምር ጦር አባላትን ክቡር መስዋዕትነት ዋጋ በመስጠት፣

የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር /TPLF/ ከአሸባሪነት መዝገብ እንዲሰረዝ የሚቀርበውን የውሳኔ ሀሳብ በመቃወም ትህነግ/ወያኔ ለሰላምና ለፍትህ እጅ እስኪሰጥና ፍትህ በተጨባጭ እስኪረጋገጥ ድረስ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር /TPLF/ በኢትዮጵያ መንግስት የአሸባሪዎች መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ እንዲቆይ ታደርጉ ዘንድ ከታላቅ አደራ ጋር እናሳስባለን።

Lisane Gfuan 1 1

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም በክብር ትኑር!

ልሳነ ግፉዓን ድርጅት

መጋቢት 12/ 2015 ዓ.ም

2 Comments

  1. አሁንስ ዘቀጡ ትንሽ እፍረት የላቸውም እንዴ 100 000 የትግሬን ወጣት ያለ እግር ያስቀረው አማራ የተባለውን አካባቢ ተመላልሶ እንዳልነበረ ያደረገውን የኢትዮጵያ መከላከያን በተኛበት ያረደውን የአማራ ሴትና መነኩሴ ሳይቀር የደፈረውንና ለመናገር ዘግናኝ የሆኑ የዲያብሎስ ስራውን የሰራውን ህወአት አሸባሪ ሳይሆን ማን አሸባሪ ሊሆን ይችላል? አረ የኢትዮጵያ ፓርላሜንታሪያን ስለ ክብራችሁ እንጅ ስለ ሆዳችሁ አትኑሩ፡፡ ጊዜው የኦሮሙማ ቢሆንም የኦሮሞ ወጣቶች ላይ የተሰራውን ግፍ አስታውሱ ኢሬቻ በአል ላይ የሆነውን አስታውሱ ልጆቻችሁም ያፍሩባችኋል ምንም እንኳን ሆዳችሁ ባያፍርባችሁም፡፡

  2. The Ethiopian parlemen members don’t have normal mind. They sack the poor Ethiopian blood and eat flush as mosquitos for nothing.

Leave a Reply

Your email address will not be published.