ቦ ጊዜ ለኩሉ – በ-ሙሉዓለም ገ/መድኀን

ብራዊያኑ ሰለሞን ከሺሕ ዓመታት በፊት “ቦ ጊዜ ለኩሉ” ማለቱን ከታላቁ መጽሐፍ አንብበናል። የጠቢቡ አባባልን የግእዝ ሊቃውንት እንደነገሩን “ለሁሉም ጊዜ አለው” የሚል ነው። በእኔ ግንዛቤ፣ በሕይወት ዘመኔ እንዲህ ዓይነት ደረቅ እውነት ገጥሞኝ አያቅም።

FB IMG 1679563704288 1 1 1

ይኸው የልእለ ኃያሏ አሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበረው ትራምፕ እንኳ ሰሞኑን “እንዳታስሩኝ” እያለ እያለቃቀሰ ነው:: መቼም ይሄንን ያየ ሰው ትራምፕ በጉብዝና የወንበር ወራቱ “ሙስሊም ሃገሬን እንዳይረግጣት” የሚል አዋጅ አስነግሮ ነበር ቢሉት አያምንም። እውነታ ግን ይህ ነው።

የትግሬም ነገር እንዲህ ነው። አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ። ይኸው ትላንት “አደይ ትግራይ ሲንጋፖር ትሆናለች” እንዳላሉን፤ ዛሬ “አዲግራት የእኔ ነች” ከሚለው የኢሮብ ሕዝብ ጋር ተፋጥጠዋል::

ትላንት አማራን በመልክዓምድር፣ በዲሞግራፊ፣ በማህበረ-ኢኮኖሚ እንዲያንስ፣ ትርጉም አልባ እንዲሆን ተግቶ የሠራው ኃይል ዛሬ ‘የእጅህ አልፎ ይጠብቅሃል’ የተባለው ደርሶበታል።

የዶላር ሚሊየነሩ ስብሃት ነጋስ “ለህክምና የምከፍለው አጥቼ ትላንት የተወለዱ የወንድሜ ልጆች ከፈሉልኝ” እያለ ያማርራል ብሎ ማነው ያሰበው? (ባናምነውም ቅሉ)

የጥንት የጠዋቱ የፋሲል ደሞዝን የትግል ቀስቃሽ ሙዚቃዎችንስ ሪትም ቀይረው፦

“አረሱት ሁመራን ዘቅዝቀው እንደ ቦይ ያውም
የእኛን ዕጣ
እነሱ ምን ያደርጉ ከዓድዋ ሰው ሲታጣ”

እያሉ መዝፈንን እንደ ትግል ስልት ይይዙታል ብሎ ማን አስቦ ነበር?

መቼም ይሄ ለዓድዋ የተገባ ቢሆንም ደርሶ ሲያዩት የሚያስቅ ነገር አለው። ከፈገግታው ባሻገር የጊዜን ጉልበት ግን ያስረግጣል።

ርግጥ ይሄ ሁሉ መአት እብሪት ያመጣው ነው።

ከፍ ሲል እንደአፍሪካ ቀንድ በኢኮኖሚያዊ ውህደት፤ ዝቅ ሲልእንደ ሀገርና ጉርብትና ተካፍሎ መብላት ሲቻል፤ በጠርዘኛ ስግብግብነት ሁሉን ለመጠቅለል ቋመጡ::

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: ጌታቸው ረዳ በአባይ ግድብ ዙሪያ የሰጡት ያልተገራ አስተያየት የካይሮ ባልስልጣናትን አስቆጣ * ከጋምቤላ የታፈኑት ህጻናት በደ/ሱዳን ለሽያጭ ሳይቀርቡ እንዳልቀረ ተሰግቷል

በመጨረሻም በዓሉ ግርማ እንዳለው “ሁሉን ትፈልጋለህ፣ ግን ሁሉ ታጣለህ” ሆነ።

መቀሌን ይዞ እንድርታ፣ ድፍን ደቡብ ትግራይን ወጅራት የብቻዬ ነው እያለ ነው።

መቼም ዛሬ እነ ክፍሌ ሙላት “ትግራይ እስከትለማ ሌላው አገር ይደማ” ያሉት ተቀይሯል።

የዛሬቱ ትግራይ ሰበር ዜናዎቿ፦

➻በትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት ሊቋቋም ነው፣

➻የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊከፈቱ
ነው፣

➻ፖሊስ ጣቢያዎች አገልግሎት ሊሰጡ ነው፣

➻ ፍርድ ቤቶች ሥራ ሊጀምሩ ነው (እስከአሁን
የነበረው ጥንታዊው ሃሞራቢ ሎ “eye for
an eye” ዓይን ላጠፋ አይን፣ ጥርስ ለሰበረ
ጥርስ ነው) አይነት እያሉን ነው

‘የጉድ አገር ቃሪያ እያደር ይፋጃል’ እንዲሉ ስለትግራይ የምንሰማቸው ዜናዎች ሁሉ አሳፋሪም፣ አሳዛኝም፣ … አሸባሪም ናቸው።

በሦስቱም ተከታታይ ዙር ጦርነት የተሰለፈው በተለይም በሁለተኛውና በሦስተኛው ዙር የተዋጋው ታጣቂ በዋናነት ወጣቶች የትግራይን አገር መሆን እያሰቡ ነበር። በጦርነቱ ማግስት ግን ከሞት የተረፉት አንድ ሚሊየን ወገኖቻቸውን ከጎናቸው ከማጣታቸው ባሻገር ብዙዎቹ ያለሟትን አገር ሳይሆን የታቀፉት፣ ያልገጠበቁትን ሰው ሰራሽ እግርና እጅ ሆኖ አገኙት።

በትግራይ፥ “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” የሚለው በግነት የተሞላ ትርክት ከራሱ ከትርክቱ መነሻ ጋር ሦስት ትውልድ በልቷል።

አያት፣ አባትና ልጅን የሕይወት ዘመን የአካል ጉዳተኛ አድርጓቸዋል።

በትጥቅ ትግሉ፣ በባድመ ጦርነት እና በአሁኑ ጦርነት አያት፣ አባትና ልጅ አካለ ጎደሎ የሆኑበት የትግራይ ፖለቲካ ሙሉ ትራጀዲ ለኢትዮጵያም የተረፈ መሆኑ ይሰመርበት።

ዛሬ በትግራይ ያለ አካለ ጎደሎ ‘የጉዳት መቼት’ ለማወቅ ‘የደርጉ ነው ወይስ የብልጽግናው?’ እንዲህ ያደረገህ ብሎ መጠየቅ ግድ የሚልበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

አያት፣ አባትና ልጅ አካለ ጎደሎ ለመሆን ያበቃቸውን፤ ከአማራ፣ አፋርና ኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አፋሳሽ ቅራኔ ውስጥ የከተታቸውን የእብደት ፖለቲካቸውን መርምሮ ለመከለስ/ለማረም ከመነሳሳት ይልቅ ዛሬም ለአራተኛ ዙር ጦርነት ምልመላ፣ ልምምድና ስልጠና ላይ ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት ተማሪዎች በግድ ዩኒቨርሲቲው እንዲለቁ ተደረገ

ዛሬም በገደል ላይ ሩጫ በሚመሰለው ስሌታቸው አዲስ አሰላለፍ ፈልገው ቀሪውን ከመማገድ የሚታቀቡ አይደሉም። “አመል ካልገደለ አይለቅም” የሚባለው ለዚህ አይነቱ ልክፍት ነው።

ለሁሉም “ቦ ጊዜ ለኩሉ” የሚለው የዕብራዊያኑ ጠቢብ አባባል፥ ለዘመኑ ተረኞችም በአያሌው ይሰራል❗️

በ-ሙሉዓለም ገ/መድኀን

1 Comment

  1. is sad the previous generation fought to sussed Eritrea, this generation fought to destroy Ethiopia, in both cases the tegreas are the losers. what do tegrea say this time, are they still complaining Ethiopians or started to look inside?

Leave a Reply

Your email address will not be published.