የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የእያንዳንዳቸው “ውሳኔ” እንዲታወቅ – ሽፈራው

በአሜሪካ የሕዝብ መብቶች (Civil Rights) ትግል ወቅት በአሜሪካ የኮንግረስ አባላት መካከል በ1960ዎች ከፍተኛ ትግል ተካሂዷል፡፡ ሲቪል ራይትስ ቢል በተደጋጋሚ ለውሳኔ ቢቀርብም ተቀባይነት አላገኘም ነበር፡፡ እጅ በማውጣት ብቻ ይወስኑ ነበር፡፡ ከውጭ ከፍተኛ የሕዝብ ግፊት ነገር ግን ዘረኛ ነጭ የምክር ቤት አባላት የጥቁር ሰዎችን መብት፣ ፀረ አድልዎ ሕጎችን በዘፈቀደ እጅ በማውጣት ያንቀበልም ውሳኔ ይወስኑ ነበር፡፡ በመጨረሻ እያንዳንቸው የምክር አባላት በእያንዳንዱ አንቀጽ ላይ ምን እንደወሰኑ በጽሁፍ እንዲቀመጥ ተወሰነ፡፡ ሕጉ ጸደቀ፡፡ የሕዝብ ጥላት ማን ነው? የሕዝብ መብት እንዳይፀድቅ የሕዝብ መብቶች እንዲነፈጉ የሚያደርጉ አባላት እነማን ናቸው? መታወቅ አለባቸው፡፡

ወያኔን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰኑ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እንደዚያ ያለ አሰራር ቢኖር ያን ውሳኔ ይወስኑ ነበር?

ያ ቢሆን ለእኛም ይቀለን ነበር፡፡ ማንን ከኃላፊነት እና ከተወካይነት እንደምናነሳ እናውቅ ነበር፡፡ ወደፊት ማን በውሳኔው ተጠያቂ መሆን እንዳለበት እናውቅ ነበር፡፡ ማንም ለውሳኔው ኃላፊነት መውሰድ አለበት፡፡ ማንም ሊቀልድ አይገባም፡፡

ሰዎች እኮ ወያኔ ከሽብርተኝነት ይሰረዝ ያሉት ቁጥራቸው ስንት እንደሆነ እንኳ አልነገሩንም፡፡ ይህ ቀልድ ማብቃት አለበት፡፡ በሀገር እና በሕዝብ ላይ መቀለድ ማብቃት አለበት፡፡ እነርሱ ባይነግሩንም ማን ምን እንደወሰነ ማወቃችን አይቀርም፡፡ እናም እያንዳንዱ ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ሶስት ዓመት አለኝ የሚለው ዋስትና ከሆነው እናያለን፡፡

ይህ ውሳኔ ዳግም ለምክር ቤቱ መቅረብ አለበት፡፡ እያንዳንዱ አባል ምን እንደወሰነ በጽሁፍ መቀመጥ አለበት፡፡ በምክር ቤቱ ጉባዔ ያልተገኘ ሰው እንኳ ካለ በስልክ ተጠይቆ ውሳኔው መቀመጥ አለበት፡፡ ይህም ለሕዝብ ይፋ መደረግ አለበት፡፡ ውሳኔው እንደገና መታየት አለበት፡፡ ጉዳዩ እንደገና ለምክር ቤቱ መቅረብ አለበት፡፡ ግልፀኝነት ይጎድለዋል፡፡ ኃላፊነት ይጎድለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የፌደራል ስርዓት መርሆዎች በ ገለታው ዘለቀ

ወያኔ ከሽብርተኝነት ዝርዝር መሰረዝ የለበትም

ጉዳዩ እንደገና መታየት አለበት፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.