ወታደሩ ራሱን፣ ሕዝቡን እና ሀገሩን ይታደግ

Ethiopia Troops 1 1

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ጦር ላይ እየተጫወተ ነው፡፡ እጅግ በተሳሳቱ ውሳኔዎች ከአንዴም ሁለቴ ሶስቴ  መከላክያ ሰራዊት እንዲጠቃ እያደረገ ነው፡፡ መጀመሪያ ወያኔ መከላክያው ላይ እርምጃ እንደሚወስድ እየታወቀ ችግር ከመፈጠሩ እና ጦርነት ከመነሳቱ በፊት ቀድመህ ሕጋዊ እርምጃ ውሰድ ቢባልም በጆሮ ዳባ አልፎ በአንድ ቀን አስር ሺህ የኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት አባላት እንዲያልቁ አደረገ፡፡

ከዚያም ወያኔ ዱቄት ሆኗል እያለ ሰራዊቱን ሲያስጠቃ ነበር፡፡ ይህም አልበቃው ብሎ ከእንግዲህ ትግራይ ወታደራዊ ጠቀሜታ የላትም በማለት ወታደሩን ከትግራይ አስወጥቶ ወያኔ እንደ አሻው እንዲዘጋጅ አደረገው፡፡ ከዚያም ሰራዊቱን እያስደመሰሰ ከዚያም የአማራን እና የአፋርን ሕዝብ እያወደመ ወደፊት እንዲቀጥል አደረገው፡፡ በሕዝብ ልጆች ደም እና ተሳትፎ ወደነበረበት እንዲመለስ አደረገው፡፡ አብይ ግን ጦርነቱን ገታው ሰራዊቱ ወደ ትግራይ እንዳይገባ አደረገ፡፡ ይህም አልበቃው ብሎ ሰራዊቱ በስንት ተጋድሎ የያዛቸውን የህወሓት መሪዎች ስብሃት ነጋንም ጭምሮ ከእስር ቤት ፈትቶ በነጻ ለቀቃቸው፡፡

እንዲሁም ወያኔ በጦርነት እንደማይሸነፍ ለማረጋገጥ ወያኔ ለበርካታ ወራት የጦርነት ዝግጅት እንዲያደርግ ፈቀደለት፡፡ ከዚያም ወያኔ እንደገና ለሶስተኛ ጊዜ መከላክያን ማጥቃት ጀመረ፡፡ የሕዝብ ልጅ መከላክያም ወያኔን መደዳውን መት እየጠረገ ሲሄድ አካሄዱ ያልጣመው አብይ የፕሩቶሪያ ስምምነት ብሎ ላይ ላዩን የኢትዮጵያ መከላክያ እንዳሸነፈ የሚያስመስል በውስጥ ግን ወያኔን በጦርነትም እና በፖለቲካም አሸናፊ የሚያደርግ ስምምነት አመጣ፡፡ አሁን ደግሞ ወያኔን ከአሸባሪነት ዝርዝር ፋቀው፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ወያኔ በጦርነትም፣ በፖለቲካም፣ በዲፕሎማሲም እንደማይሸነፍ የማይሸነፍ ሃይል እንደሆነ እያረጋገጠልን ነው፡፡ አሁን ጠላታችን ማን እንደሆነ አውቀናል፡፡ ከእንግዲህ ወደ ወያኔ የምንሄደው በመጀመሪያ በደማችን በሚቀልዱት ላይ አፈሙዛችንን ካዞርን በኋላ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ በአብይ እጅ እየወደቀች ወይስ የሻለቃ ዳዊት ማስጠንቀቂያ ብቻ? | Hiber Radio

 

                                     አስር አለቃ ክበበው ደምስ

2 Comments

  1. አስር አለቃ መከላከያ ሚንስትሩም ህወአት ነው አብረሀም በላይ ይባላል የትግሬ አገረ ገዥ አድርጎት ህወአትን አጠናክሮ ነው የወጣው አማካሪውም አርከበ እቁባይ ነው የዚህ ነገር ምስጢር ወደፊት ይወጣል። ለጊዜው ግን የመከላከያ ሀይላችን ላይ ባይ ቀልድ መልካም ነበር። በእርግጥ የራሱ የወደፊት እጣው ያሳስባል የሚያምር አይመስልም ከሩቅ ሳይሆን የቅርቦቹ ይበሉታል።

  2. መከላከያ የአማራን ከሌሎች ብሄሮች መሬት የመንጠቅና የማስፋፋት ሕልም ለማሳካት ሞት ይብቃ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.