ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ በጀግንነት የተዋጋው ጄ/ል ተፈራ ማሞ ከሃገር ወጥቶ መታከም ሲችል ሆነብሎ መከልከል የሞት ፍርድ እንደመፍረድ ይቆጠራል

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: አርሰን ቬንገር ለአርሰናል የሚፈልጓቸው 10 ከዋክብት

2 Comments

  1. ወታደሩ በዚህ ነገር ዝም ይላል እንዴ? የወጋውን ስብሀት ነጋን በክብር ሲሸኘው ጓዱን ሲገድልበት? እዚህ ላይ ያላመጸ ወታደር ይህንን ያልተቃወመ ፖለቲከኛ አሳማ እንጅ ምን ሊሆን ይችላል?

  2. በወያኔና በኦሮሞ ድላ ተወቅጦ አሁን ዝም ያለው እውቁ ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ “አልነጋም” በተሰኘው ጥልቅ ግጥሙ እንዲህ ብሎን ነበር።
    ፀሐይ ስትወጣ- ‹‹ነግቷል›› ለምትሉ
    ንጋት ላልገባችሁ- ጨለማዎች ሁሉ
    አልነጋም ነው መልሴ- ለናንተ እኩኩሉ፡፡
    አልነጋም
    አልነጋም
    አልነጋም
    አልነጋም
    እንደኔ ላለ ሰው
    በረሀ ተወልዶ-በረሀ ላደገ
    ፀሐይ ጠላቱ ነች
    ሰርክ የሚደበቃት- ጥላ እየፈለገ፡፡
    ከላይ በአስተያየቱ – “የበላይን አንገት ለገመድ ፣ ባንዳን ለሽልማት ስታበቃ የኖረች ሀገር ናት – ኢትዮጵያ የዛሬው እድል ፈንታዋ ካለፈው ጨልሞባታል። በእውነት የወያኔን ገዳይ ሃይሎች ከሥር የፈታውና ለህክምናም ሆነ ለጉብኝትም በየስፍራው እንደልባቸው እንዲዘዋወሩ ያደረገ የድህነቱ መንግስት ብልጽግና ማንን ነው የሚያታልለው? በሰሜን ጦር ላይ በተኙበት ወታደርና ሲቪል ጦርነት ከፍቶ ስንቶችን ያረገፈውን የወያኔ ቁንጮ አቶ ስብሃት ነጋን ከገደል ተሸክሞ ያወጣ እንዴት ባለ ሂሳብ ነው ለዘመናት በወያኔ ሰቆቃ ስንት ግፍ የተሰራበትን ጄ/ተፈራ ማሞን ውጭ ሂዶ እንዳይታከም መከልከል፡፡ ለዚህ ነው ውጊያው በወያኔና በኦሮሞ ፓለቲከኞች ጥምረት በአማራ ህልውና ላይ ነው ብዬ የማምነው። በወሎ፤ በጎንደር፤ በሰሜን ሽዋ፤ በአፋር የተደረገው ተደጋጋሚ ጦርነት ሆን ተብሎ የተደረገ ለመሆኑ አሁን በፕሪቶሪያና በናይሮቢ ተደረገ የተባለው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም በግልጽ ያመላክታል። አማራው መስሎት እንጂ ውጊያ በይፋ ከታወጀበት ቆይቷል። ጥቃቅን አጀንዳዎችን መንግስት ተብዬው እየሰጠ እርስ በእርሱ ሲያናክሰው የኦነግ መሪዎች በተጠና መልኩ በኢትዮጵያ አንድነትና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ላይ ጠንካራ አቋምና ተሰሚነት ያላቸውን ሰዎች በስውርና በይፋ ይገላል፤ ያፍናል፤ ያፈናቅላል፤ ያሳድዳል። የጄ/ተፈራ ህክምና መከልከልም ከዚሁ ከወያኔ የክፋት ኮሮጆ ኦነግ የገለበጠው ከጭፍን የዘር ጥላቻ የመነጨ ክልከላ ነው።
    የሰላም ተሸላሚው ጠ/ሚ ሥራው ሁሉ እየቆየ የሚያማታ፤ ሰው በዘሩና በቋንቋው ብቻ የጎላ ሚና እንዲኖረው የሚያደርግ፤ አሰራሩ ሁሉ ሽምድምድና ወልጋዳ ለመሆኑ በየቀኑ ከሚያደርጋቸው የማያባራ ንግግር መረዳት ይቻላል። በቅርቡ በጉራጌ ህብረተሰብ መካከል ተገኝቶ የደሰኮረው ዲስኩር አማችና ጭራሽ እውነትነት የሌለበት ፊት ማሳያ ጉብኝት እንደነበረ በሥፍራው የነበሩ ይረዳሉ። ባጭሩ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ኦሮሞ ሆነህ ኦሮምኛ ካልተናገርክ ሥፍራ የለህም። ምድሪቱ በዘርና በጎሳ እንዲሁም በቋንቋ ከተሳከረች የቆየ ቢሆንም እንደዚህ እንደ አሁኑ የጦዘበት ጊዜ ትውስ አይለኝም። በይፋ ኦሮምኛ ካልተናገርክ የሥራ ማመልከቻህን አልቀበልም የሚባልበት ጊዜ ላይ ቆመን ጠቅላዪ ምንም ችግር እንደሌለ ዝም ብሎ በማር የተለወሰ ቃሉን በየስፍራው ይዘራል። ወለጋ ላይ ክትባት እንስጥ በማለት ሰብስቦ ኦነግ የረሸናቸው ሰዎች ደም ይጮሃል። ሰው ዘሩን መርጦ እንደተወለደ ሁሉ ሰውን በዘሩና በቋንቋው እያሳደደ ከሚገድል የኦነግ ሸኔ ስብስብ የኦሮሞ ነጻነት ይመጣል ብሎ መገመት ያለፈ ታሪክን አለመረዳት ነው። ደም አፍሳሾች ነጻነትን አምጥተው አያውቁም። ከበፊቱ የከፋ ባርነትን እንጂ። ግን መቼ ነው ይህች የሃበሻ ምድር የሚገድሏትንና የሞቱላትን ለይታ ፍትህ የምትሰጠው? አላውቅም። ሌላው እውቁ ገጣሚና አሁን በህይወት የሌለው አያ ሙሌ (ሙሉጌታ ተስፋዬ) እውነትም በመንበርህ የለህማ ያለው ወዶ አይደለም። ስለዚህ ፈጣሪ ሃገራችን ጠብቅ፤ ሰላም አድርግልን ወዘተ ማለቱን ትተን በምድር ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ግፈኞችንና ደም አፍሳሾችን በምንችለው ሁሉ ለመፋለም ከዘር፤ ከቋንቋ፤ ከክልል ፓለቲካና ከሃይማኖት ራሳችን ነጻ አድርገን ሰውን በሰውኛ ሚዛን በማየት ታጥቀን እንነሳ። ደጋግሜ እንዳልኩት ፈጣሪ ሰው የክፋትና የመከራ ቋት ሆኖ ይህን አድርግ ያን ሥራ ማለቱ በራሱ ላይ ማሾፍ ይሆናል። የችግሩ ምንጭ እኛው ነን። የችግሩ መፍትሄም ከእኛ ነው። ሌላው ሁሉ ማቆሚያ ከለሌው የዶፍ ዝናብ መጠለያ ፍለጋ እንጂ እውነትነት የለውም። የጄ/ተፈራ ማሞም ወደ ውጭ ሂዶ ህክምና እንዳያገኝ መከልከሉ ምን አልባትም ህክምናው የሚያጋልጠው በጄኔራሉ ላይ የተደረገ ሰውር ደባ ይኖራል። ሰው እንደ አውሬ በመርዝ የሚገደልባት ሃገር። አይጣል! በቃኝ

Leave a Reply

Your email address will not be published.