ጥበብ በቴዲ አፍሮ ቤት አደርባይ አይደለችም ( ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን )

እውነትን ትናገራለች። ፍትህን ትሰብካለች። ነጻነትን ታዜማለች። ስለቴዲ የጥበብ ተአምራዊ ብቃት ለመግለጽ አቅም ያለው ቃል አላገኘሁም። ትላንትም በዜማዎችህ ኢትዮጵያን አየናት። ዛሬም በልዩ ስጦታህ ለለሀገራችን፣ ስለወገኖቻችን አልቅሰህ፣ አስለቀስከን። ነገም ባንተ የጥበብ ምናብ ውስጥ ታላቋን ኢትዮጵያ እናያታለን። አንተ ትለያለህ። እነዚህን ስንኞች ያፈለቀው አእምሮህን እንዴት አለማድነቅ ይቻላል?!
ዘውግ ያወረው ድንበር ማላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በእልፍ አእላፍ ሬሳ
የተረገጠ እውነት በጊዜ ውስጥ እግር
ታፍኖ የቆየ በሆታ ግርግር
ትንሽ ጋብ እንዳለ የጭብጨባው ጩኸት
እረጭ ሲል ውሸት ይናገራል እውነት
እያመመው መጣ
ቂምን ሻረውና ወይ ፍቅርን አንግሰው
ሁለት ሆኖ አያውቅም አንድ ነው አንድ ሰው
ከሐገርም ይሰፋል ያ የፍቅር ገዳም
መጠሪያው ሰው እንጂ ዘር አይደለም አዳም
ቴዲ፣ አለቀስኩ። ደግሞም ልቤን ተስፋ ሞላት። እድሜ ይስጥህ!
ተጨማሪ ያንብቡ:  ካራማራ ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርጎ ያውለበለበው ጀግናው ብ/ጀኔራል ደሣለኝ አበበ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.