ኢትዮጵያዊነት ወንጀል: ኢትዮጵያዉያን አገራቸዉ እና መዳረሻቸዉ የት ይሆን?

Ethhiopiawinetኢትዮጵያዊነት ወንጀል እና በደለኛነት ሆኖ የሚታየዉ አስከ መቸ እንደሆነ ባይታወቅም የኢትዮጵያን ዕዉነተኛ ታሪክ በመካድ የኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያን አንድነት በማናጋት እና የመኖር ዋስትና ማሳጣት ማማ ሻ ጊዜ ለመግዛት ካልሆነ በቀር መጨረሻዉ ሞት ነዉ ፡፡

የህዝብን ቁስል እና ህመም ከማስታመም ይልቅ ነህዝብ ስም ጥላቻ እና በቀል መዝራት ከህዝባዊነት ማዕቀፍ ያስተፋል እንጂ አያሳቅፍም እና እንዲያዉ ህዝብን በንቀት እና በማጥላላት ኢትዮጵያዊነት የለም ፡፡

በመላዉ አገሪቱ በፀረ -ኢትዮጵያዉያን ለዘመናት አገር በማፍረስ ሴራ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከዉጭ እና ከዉስጥ  ኢትዮጵያ ጠል ታሪካዊ ጠላቶች ድር እና ማግ በማድረግ ለግማሽ ክ/ዘመን እየሰሩ እና እያሴሩ ባለበት አንጻራዊ ሠላም የሚገኝበትን መሀል ኢትዮጵያ (ጎጃም) ላይ የህዝብ ልጂ እና የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ህዝብ ልጂ በሆነዉ ፍኖ ላይ በህግ ማስከበር ስም ዘመቻ መካሄዱን  በቀጥታም በወሬም  እንረዳለን ፡፡

ለመሆኑ ሠላም የራቃቸዉ ፤ኢትዮጵያዊነት ወዘና ካጡ አመታት ያስቆጠሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች ቢያንስ 1/3ኛዉ የአገሪቷ ክፍል ለአፍራሽ ሃይሎች  ደም፣ ህይወት እና  ስደት በሚገብሩት ጊዜ ሠላሙን አስጠብቆ እና ከሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች ከሚሳደዱት እና ከሚሞቱት የኢትዮጵያን ህዝቦች በተለይም የ ዓማራ ህዝብ መጠጊያ የሆነዉን የጎጅም ምድር ሠላም ለማደፍረስ የሚደረገዉ በቀል ተኮር  “ፋኖን ”የማሳደድ ስራ ለአገር ቀርቶ ለግለሰብ የሚበጂ አይደለም ፡፡

ኢትዮጵያን የግል የእጂ ስራቸዉ እና በነሱ ቸርነት የተፈጠረች እና የኖረች አገር አድርገዉ የሚያስቡ እነርሱ ቀንደኛ ታሪካዊ የህዝብ እና የአገር ጠላቶች እና ስስታሞች እና ግለኞች መሆናቸዉን “ተቀምጦ የሚያከብረዉን እና ቆሞ የሚንቀዉን ” የሚያዉቀዉ በርቱ እና አርቆ ተመለረካች ኢትዮጵያዊ አሳምሮ ከጥንት አስከ ጥዋት የሚያዉቀዉ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ደጋፊዎችን ልፋት፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አፈር ድሜ አስጋጠው

እናም የኢትዮጵያ ዋስ ጠበቃ እኛ ለሚሉት እኛን ኢትዮጵያዉያን አምርረዉ የሚጠሉን እኛን እያሳደዱ ስለ አገር እና ህዝብ  ዘብነት መናገር ሹፈት ሳይሆን ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ  ከፍተኛ ታሪካዊ ስህተት እና ክህደት ነዉ ፡፡

በቅርቡ የሆነዉ  ሠላም እና ህግ በማስከበር ሽፋን የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ  በተለይም ዓማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለዉ ማሳደድ እና ማዋረድ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የህዝቦችን አንድነት የመናድ ጉዞ ቢሆንም ነፃነት እና ለህልዉና መረጋገጥ የሚደረገዉን ብሄራዊ ህብረት እና አንድነት እንደሚያጠናክረዉ ጥርጥር የለዉም ፡፡

አገር ሲፈርስ የሚጠቀመዉ ጠላት እንጂ ባላገር የሆነዉ ኢትዮጵያዊ ሊሆን እንደማይችል በመረዳት ሁሉም“ ጨዉ  ለረስህ …..” እንዲሉ ለራሱ እና ለአገሩ ዘብ ይቁም ፡፡

እዚህ ጋ የፋኖን  ስርዎ ታሪክ ፣አመጣጥ እና ክስተት ልክ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን የግል ንብረት እና ስሪት አድርገዉ እንደሚያዩት ዕቡያን እና ግብረ አበሮች ከታሪካዊ እና አገራዊ መረጃወች በተጨማሪ ኢትዮጵያ እንደ አገር ከመፈጠሯ ጋር  የፋኖ የነፃነት ታግድሎ እና ብሄራዊ አልኝተኝነት ምልዕክትነት ቀድሞ በኢትዮጵያ ግዛት እና ዕምብርት በሆነዉ ክ/ሀገር በቦታ መጠሪያዉ “ፋኖ ” የሆነ መኖሩን የምናዉቅ ስንቶቻችን ናቸዉ ፡፡

ይህም ፋኖነት “ፋኖ ”ተብሎ ከሚጠራዉ ልዩ ቦታ ጋር ብንመለከተዉ የሶስት ዓመታት  ዕድሜ ማስቆጠሩን ስናይ ለኢትዮጵያዉያን ፋኖ ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ዉልደት ጋር የማይነጠል በመሆኑ ፋኖ ኢትዮጵያ ፤ ኢትዮጵያ  ኢትዮጵያዉያን ፤ ኢትዮጵያዊነትም ዓማራን የሚያቅፍ  እንደመሆኑ  ዓማራን እና ፋኖን መለያየት ኢትዮጵያን ማደናቀፍ መሆኑን ለመረዳት የኋላ ታሪክን ማወቅ ከበቂ በላይ ተጠባቂ ይሆናል፡፡

እናም ኢትዮጵያዉያንን በአገራቸዉ ማሳደድ ፣ ማስወገድ እና ማዋረድ  በይፋ በሚካሄድበት አገር ስለ ባዕድ አገር ኗሪ ዜጎች ስቃይ እና መመለስ የአዞ ዕንባ ማንባት ምን ይባላል፡፡ ለመሆኑ በአገር ዉስጥ የዘመናት የሞት እና ስደት  ፣ጥቃት ፣ ፍጂት ባልቆመበት የዉጭ ስደተኞችን ጉዳይ ማጮህ እንዴት ይሆን የኢትዮጵያዉያን አገራቸዉ እና የመጨረሻ ዕጣ ፋንታ መዳረሻ የት እንደሚሆን እንደ ሠዉ የሚያሳስበን መቸ ይሆን ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊያን - ከያህያ ይልማ

 

“ነፃነት ወይም ሞት ”

NEILOSS –Amber

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.