ጋዜጠኛ ተመስገን “የመከላከያ ሰራዊትን ሚስጥር በማውጣት” የሚል አዲስ ክስ

temesgenጋዜጠኛ ተመስገን ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርቧል
መንግስት ከ33 ቀን በኋላ ለተመስገ “የመከላከያ ሰራዊትን ሚስጥር በማውጣት” የሚል አዲስ ክስ አዋልዷ
የመንግስት የክስ አደማመር ሂደት እንመልከት
↘️ በመጀመሪያ ጋዜጠኛ ተመስገን ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት በዩትዩቦች ይጠቀማል አለ፤
+ ሲደመር
↘️ ከአስር ቀን ቀጠሮ በኋላ በዩትዩብ ሳይሆን በፍትሕ መፅሔት ይጠቀማል አለ፤
+ ሲደመር
↘️ ፍርድ ቤቱ ይሄን ተከትሎ በዋስ እንዲወጣ ወሰነ፤
+ ሲደመር
↘️ይሄን ተከትሎ የፖሊስ መርማሪዎችና አቃቤ ህጎች ይግባኝ ብለው ወንጀሉ ውስብስብና ሌሎች አባሬዎች አሉ አለ፤
+ ሲደመር
↘️ፍርድ ቤቱም ሰኔ 2/2014 በዋለው ችሎት ደግሞ ፖሊስ 8 ቀን ወስዷ ምርምሮ ለሰኔ 10/2014 በድጋሚ ያቅርባቸው ብሎ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ወሰነ::
+ (ሲደመር)
↘️የሰኔ 10/2014 ቀጥሮ ቀርቶ ለሰኔ 7/2014 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳልኝ ከ5 ቀናት በኋላ ፍርድ ቤት ቀርቦ አቃቤ ህጎቹም የተመስገን ፁሁፍ ወታደራዊ ሚስጥሯች ፅፏል:: ፁሁፍን ተከትሎ ሞትም ተከስቶ ሊሆን ይችላል የሚል አዲስ ክስ አምጥተዋል::
+ ሲደመር
የዛሬን ሰኔ 22/2014 ዓ.ም ክስ አዋልደዋል::
ሦስት የተለያዩ ክሶችን አነባብረው አዋልደዋል::
1ኛ. በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 44(1) (2) እና 336(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ፤ 2ኛ. በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 44(1) (2) እና 337(1) ፤ 3ኛ. በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 44 (1) 2) እና 257 (ሠ) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ፡፡
ወንጀል ክስ የቀረበበት ሲሆን ፤ አጠቃላይ ክሶቹ ” ምስጢራዊ ወታደራዊ መረጃዎችን በማውጣት ፣ የሐሰት ወይም የሚያደናግራ ወታደራዊ መረጃ በማውጣት እንዲሁም ህዝብ ያለውን አቋም የሚያፈርስ መረጃ በተከታታይ እትሞች ለህዝብ እንዲሰራጭ በማድረጉ በፈፀመው መገፋፋት እና ግዙፍ ያልሆነ ማሰናዳት ተግባር ወንጀል ተከሷል” የሚል ነው።
በጋዜጠኛ ተመስገን ዳሳለኝ ላይ የቀረበውን ክስ ተከትሎ ፤በዋስትና ጉዳይ በግራና ቀኝ ክርክር ተካሂዷል ።ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ፤ የደንበኛቸው የዋስትና መብታቸው ተከብሮ በተከሰሱበት ወንጅል ጉዳያቸውን ከእስር ቤት ውጪ ሆነው እንዲከታተሉ ለፍ/ቤቱ ጠይቋል።
ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ በሰጠው ምላሽ ፤ የዋስትና መብት ውድቅ እንዲሆን እና ጋዜጠኛ ተመስገን ጉዳዩን በእስር ቤት ሆኖ እንዲከታተል የጠየቀ ሲሆን ፤ በምክንያትነት የዘረዘረው ” የክሱ ብዛት ፣ ተደራራቢነት እና የወንጅሉ ሁኔታ እንዲሁም 1ኛ እና 3ኛ ክሱ እስከ 10 ዓመት የሚያስቀጣ በመሆኑ ፣ በተጨማሪ 2ኛ ክስ እስከ ዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ” በመሆኑ የዋስትና መብት ሊጠበቅ አይገባም በማለት ዐቃቤ ሕግ ተከራክሯል።
ለዐቃቤ ሕግ ክርክር ምላሽ የሰጡት ጠበቃ ሔኖክ ፤ ” ጋዜጠኛ ተመስገን ሀሳብን ከመግለጽና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ለማድረግ ከመጻፍ ባለፈ ምንም ወንጀል ፈጽሞ እንደማያውቅ ለችሎቱ” አስረድቷል፡፡ ከዚህ በፊት በነበረው የመንግስት ሥርዓት ታስሮ ዋስትና ተፈቅዶለት፤ ለሶስት ዓመታት ሕግን አክብሮ እየተመላለሰ ፍርድ ቤት ይቀርብ እንደነበርም ጠበቃው አቶ ሄኖክ አንስተዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ፤ በወንጀለኛ መቅጫ ስነስርዓት ሕግ አንቀጽ 67/ሀ እና በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 6 መሰረት የዋስትና መብቱ እንዲጠበቅለት ጠይቀዋል፡፡
ባለፉት ጊዜያት ጋዜጠኛው ሕግን አክብሮ ወደ ፍርድ ቤት ይመጣ እንደነበርም ጠበቃው ጠቅሰዋል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ከሀገር እንዲወጣ በተለያዩ አካላትና መንግስታት ሳይቀር ግፊት ቢደረግበትም ጋዜጠኛው ግን “ስራዬና ሞቴ በሀገሬ ላይ ነው” ብሎ ከሀገር ሳይወጣ መቅረቱን ጠበቃው ተናግረዋል፡፡
ጋዜጠኛ ተመስገን ቋሚ አድራሻ ያለውና ህግን የሚያከብር በመሆኑፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቱን እንዲፈቅድለት ጠበቃው ጠይቀዋል፡፡ ዐቃቢህግ ግን ጋዜጠኛው በተደራራቢ ክስ በመከሰሱና በልዩ ሁኔታ ዋስትና ሊያስከለክል እንደሚችልና የሰበር ውሳኔ ድንጋጌዎች ዋስትናን ሊያስከለክል እንደሚችል ጠቅሶ ዋስትና ሊሰጥ አይገባም ብሏል፡፡
ፍርድ ቤቱ በዋስትናው ላይ ብይን ለመስጠት ለአርብ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓም ቀጥሯል

Tariku Desalegn Miki

ተጨማሪ ያንብቡ:  በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጸመው ሰውን የማቃጠል ድርጊት፤ የመንግስት የጸጥታ አባላት መሳተፋቸውን ማረጋገጡን ኢሰመኮ አስታወቀ

Leave a Reply

Your email address will not be published.