የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በየሰብአዊ እርዳታ በጫኑ ተሽከርካሪዎች ያልተፈቀደ ጥሬ ገንዘብ እና ቁሳቁሶችን የማስተላለፍ ተግባርን በጽኑ አወገዘ

በአፋር ክልል ሰርዶ ኬላ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ ወደ ትግራይ ክልል አስቸኳይ ድጋፍ እና የሕክምና ግብአቶችን በጫነ ተሽከርካሪ ውስጥ ገንዘብ እና ፈቃድ ያላገኙ እቃዎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ሊዘዋወር ሲል መያዙን ገልጿል።
296391382 3256164031292720 9019281170708453046 nድርጊቱን የፈጸመው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋሉንና ተሽከርካሪው ኮሚቴው ከአንድ የንግድ ኩባንያ ለአጭር ጊዜ በኪራይ የወሰደው መሆኑን አመልክቷል።
የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ “ከተገኘው ገንዘብ እና እቃዎች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም ድርጊቱን አጥብቄ አወግዛለሁ” ብሏል በመግለጫው።
ኮሚቴው “በመላው ኢትዮጵያ በትጥቅ ግጭት እና ሌሎች ሁከቶች” የተጎዱ ሰዎችን ብቻ መርዳት የሚፈልግ የሰብአዊ ድርጅት እንደሆነና በኪራይ ያመጣው ከባድ የመኪና አሽከርካሪ ያጋጠመው ሁኔታ በስራው ላይ ተጽእኖ እንዳያሳድር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
በአፋር ክልል ጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ቅርንጫፍ ዱብቲ ወረዳ ሰርዶ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ8 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ እና የተለያዩ ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶችን መያዙ ይታወቃል።
296016421 3256163787959411 8904182988002450630 n
ኢዜአ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራና አፋር ተጎራባች ወንድማማቾች የሰላም መድረክ በቀወት ወረዳ ኩሬ በረት ቀበሌ በመካሄድ ላይ ነው!

1 Comment

  1. በርቱ ወገኖች እንዲህ በርትታችሁ ስትሰሩ እንደግፋለን ዳግም ወገኖቻችንን በትግሬዎች እንዲታረዱ አንፈቅድም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.