ስለ ለገሰ ቱሉ እውነታዎች !!

አያሌው መንበር

  1. የትውልድ ቦታ: ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን። ማለትም የአማራ ሕዝብ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ በኦሮሙማ ዘረኛ ኃይል ቁምስቅሉን ከሚያይበት ማገቻ ቦታ ነው።
  2. ብሔር፡ ኦሮሞ
  3. ወደአማራ ክልል የመጣበት ምክንያት: በ1980ዎቹ መጀመሪያ በዲፕሎማ ከተመረቀ በኋላ የ1ኛ ደረጃ የBiology መምህር በመሆን ተቀጥሮ የሰራና በሹመት ላይ እያለ በክረምት የመጀመሪያ ድግሪውን በBiology ይዞ ክልል ብአዴን ጽ/ቤት በኃላፊነት እያለ ከነብናልፍ አንዷለም ጋር በ2011 ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ MA in Educational psychology ያገኘ ነው። በአካዳሚክ አቅሙ ጎበዝ የሆነና የዕውቀት ችግር የሌለበትም ነው።
  4. ወደአመራር የመጣው : አማራ ክልል ኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን የሚተዳደረው በቋንቋ ምክንያት ከኦሮሚያ ክልል በመጡ ምስለኔዎች ስለነበረ በዚህ መሠረት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪም ሆኖ ነበር
  5. ከዞን አስተዳዳሪነት የተነሳበት ምክንያት : በኬሚሴ ተወላጆች በተነሳው ቅሬታ
  6. ከዚያ የት ተመደበ: በ1998 በብአዴን ማ/ኮ ጽ/ቤት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የድርጅቱ የአስ/ፋይናንስ ኃላፊ ሆኖ ተመደበ

ቀጠለና የብአዴን ጽ/ኃለፊ ሆኖ ለተወሰነ ጊዜ ሰርቷል።

  1. ሌሎች ኃላፊነቶች: የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበረና የአሜራ ክልል ም/ቤት አባል የነበረ ነው።
  2. መታወቂያ ባህሪው: ሐቀኛ ታጋይ በመምሰል አማራ ጠልነቱ በድፍረት በየአደባባዩ የሚያሳይ መሰሪ ሰው ነው:: የአዲሱ ለገሰ፣ የበረከትና ታደሰ ጥንቅሹ ዋነኛ ጉዳይ አስፈጻሚ እንደነበረ አስታውሳለሁ።
  3. ከዚያስ?

የመለስ አካዳሚ ፕሬዚደንት ሆኖ ተመደበ ከዚህ ኃላፊነት በለውጡ ወቅት እያለ ወደቻይና ለትምህርት ተላከ።

10.ከዚያስ?

ከትምህርት እንደተመለሰም ንጉሱን በማባረር ቀድሞ በአብይ በተመቻቸለት ቁልፍ ስልጣን የኮሚዩኒኬሽን ሚኒስተር ሆኖ በአብይ ተሾመ

  1. ቀጥሎስ?

የአማራን ኮታ በመያዝ የብልጽግና ፓርቲ ማዕ/ኮሚቴ አባልና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆኖ በአብይ ቡድን ተሰየመ

  1. አሁን ምን እየሰራ ነው?
ተጨማሪ ያንብቡ:  የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ ድጋሚ ሊጓዙ ነው

የኦሮሙማ ዋና ጠበቃና ሽፋን ሰጪ ከመሆኑም በላይ አሚኮን በጸረ-ኦሮሞነት እየወነጀለ ያለና ለማዘጋት እየተሯሯጠ ያለ ነው።

በአጭሩ በአማራ ሕዝብ ሰም ስልጣን ላይ ተቆናጦ አማራን ለማጥፋት የአብይና የሽመልስ ቀኝ እጅ ሆኖ በፊታውራሪነት እየሰራ ያለ ነው።

ማሳሰቢያ፡ የአማራ ብልጽግና ውስጡን በቆራጥነት ካላጠራ ፈተናው ማለቂያም የለው

——————

Leave a Reply

Your email address will not be published.