እንደ ጺላጦስ እጅን ታጥቦ ከወንጀል ንፁህ ለመሆን መሞከር ያስተዛዝባል ! – ተዘራ አሰጉ ከምድረ እንግሊዝ

የዲያስፓራ የብልፅግና ተለጣፊዎችና የለገሰ ቱሉ ተብየ የማናለብኝነት የንቀትና የይስሙላ የቁራ ጩህት መግለጫዎች ገዳዮች ፣ አፈናቃዮች እና ግፈኞች ከደሙ ንፁህ መስለው በስልጣን ይዘልቁ ዘንድ ማህበረሰቡን የሚያዘናጉበት ስልት ብልፅግናዎች ከሕውሃት አባታቸው የወረሱትና የኮረጀት ባህሪና እካሄድ መሆኑ ግልፅና ግልፅ ነው።

ሕውሃት በ997ቱ ምርጫ ወቅት በመላ ሃገረቱ በተለይ በመዲናዋ አዲስ አበባ በአብላጫ ድምፅ ሲሸነፍ “የመራጮች የሕዝብ ድምፅ የይከበር የአደባባይ ነውጥን ለማፈን ያደረገው ጭፍጨፋና የአሮሞ ብልፅግና በአሁኑ ስዓት እያከናወነ ያለው የኢትዮጵያና የአማራ ጠል ገዳይኑቱ ፣ ወደ እስር ማጋዙና የመሰሬነት ባህሪዎች በአብዛኛው ተመሳሳይነት አላቸው።

አምላክ በአምሳሉ የፈጠረውን የሰው ልጅ ሞት ፣ ስቃይ ፣ መከራ ፣ መፈናቀል ወ.ዘ.ተ. በይቅርታ ፣ በካሳ ፣ በገንዘብና በንዋይ ተምኖ ለማወራረድ መሞከር ለአንዳንዶቹ እሽርጋጅ ባንዳዎች ፣ ተከፋዮችና ወጭት ሰባሪዎች የሚመስላቸው ከአለቆቻቸው ድግስ ቤት ታድሞ ውስኪ እና ቁርጥ እንደማወራረድ ነው።

ትዝ ይለኛል ህወሃት በ1997 ምርጫ ከሁለት መቶ በላይ ንፁሃንን በአዲስ አበባ ከተማ ሲጨፈጭፍ የአሁኖቹ “የተግባር ምክር ቤት ፣ Defend Ethiopia ፣ በእየ ኢምባሲው ተሰግስገው እሁን የሚያነፈንፉ ውሻ ደም ላሾች ፣ የብልፅግና መንግስት ጋሻጃግሬዎችና ተከፋዮች የአምናዎቹ ቅንጅቶችና ግንቦቴዎች ” የያኔውን ዐይን ያወጣ ግድያና ጭካኔ “ተመጣጣኝ ነው ወይስ ተመጣጣኝ አይደለም” እያሉ በህውሃት ደባዊ ትርክት ጀሮአችን ያደነቀሩና አጀንዳ ተቀብለው ያራግቡ እንደነበር የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ያኔ በውይይቱ የታደሙ ወገኖች “በሃገራችን ፍትሃ ነገስት ፣ ዘመናዊ ሕግና ቱፊት” መሰረት” አንድ መርፌ የሰረቀና እንድ በሬ ሰርቆ የነዳ ያው ወንጀለኛ ነው ” የሚል የሕግን ጠርዝን ተከትለው ለማስረዳት ሞክረው ነበር ፣ ግን ማን ሰምቶ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር 8 - ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ይዛ ቀርባለች

የሕግን አግባቦት የማይረዳ ፣ በትምህርት ቤት ደጅ ያላለፈ የመንደር አውደልዳይ ሲናገርም ፣ ሲዳፈርም ፣ ሲከትብም በሌላ ጠርዝ ያለውን የተጎዳ ወገን ስሜት አይረዳም።

ምክንያቱም “ውሻ በበላበት ይጮሃል” እንዲሉ የአዛዦቻቸሁንና የጌቶቻችሁን መዳኛ መንገድ ፣ የስልጣን ዘመን ማረዘሚያና መሰንበቻ ስለምትናፍቁና ስለምትሹ የማወናበጃ ፣ የመሸንገያ ፣ መንግስት መልካም ተናገራችሁ እንዲላቸሁ ፣ ድጋፋዊ መግለጫ ሰጡ ተብላችሁ መንግስት ነጥብ እንዲቆጥረላችሁ በሚል መናኛ የሽንገላ ስራ መስራታችሁ አመላቸሁና የለመዳችሁ አባዚያቸው ስለሆነ “ኧረ ተው ፣ ይበቃል” ከማለት በቀር ምን እንበላቸሁ ፣ ማፈሪያዎች።

ለኢትዮጵያ ህዝብ ባህዳን የሆኑት የተባበሩት መንግስታት ፣ አለም አቀፍ የፍትህና ፍርድ ፅህፈት ቤት /International court of justice”፣ የአውሮፓ ህብረት ና አለም አቀፍ ተቋማት ወ.ዘ.ተ. የብልፅግና መንግስት ያደረሳቸውን ዘር የማጥፋት ክዋኔዎች በአግባቡ ተጣርተው ፍርድ ይሰጥ ዘንድ እየተከራከሩ ባሉበት ወቅት “የእናት ልጅ ዥንጉርጉር” እንዲሉ ከእኛው አብራክ የተፈራችሁ የህንግዲህ ልጆችና ልወደድ ባዮች ፍሬፈርሲኪ የሆነ ደብዳቤ በመፃፍና መግለጫ በመስጠት እምቢ ባዮን ሕዝብ ሊታደናግሩና ግራ ሊታጋቡ በየፊናቸው በመሯሯጥ መሆናችሁ ትንሽነታችሁን ያሳያል።

ሌላው ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የተጎዱትን ማቋቋም ፣ መርዳትና መደገፍ እንጂ ፖለቲካ ውስጥ ገብቶ መዘንቆልና መዳከር ምን የሚሉት ነው።

የረቀቀውን የመንግስት ደባ በጎረሱት ድጎማ ፣ ጉርሻና ፍርፋሪ ተገፋፍተው የተገፋውን ሕዝብ የደምና የሙት ገላን ሽጠው ሌላ ተጨማሪ መሃያ ለማወራረድ መኳተናቸው ያሳዝናል ፣ እነደዚህ ሆኖ ከሰውነት ጎዳና መውጣት ያንገሸግሻል።

በተጎዳ ጎን ፣ ነፍስ ፣ ስጋ ፣ ሞራልና መንፈስ እሳት ፣ እረመጥና ስይፍ መሸንቆር ምን የሚሉት ነው ፣ ኧረ እፈሩ ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ህወሓት በአፅቢ (እንዳስላሴ) ረብሻ ለመቀስቀስ እየሞከረ ነው፤ ነገ እሁድ አረና ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳውን ቀጥሏል

እነዚህ የሃሳብ ፣ የአመለካከት ፣ የእውቀትና የጥበብ ድውያን የሆኑ “እዛኝ ቅቤ አንጓቾች ” ሊገነዘቡት የሚገባው አንኳር ገዳይ ወንጀል የፈፀመው የመንግስት አካልና ለወንጀሉ መፈፀም የገንዘብ ፣ የሃሳብ ግፊት እና ድጋፍ በማከናወን የመንግስት ጀሮና ዐይን ለአለፉት አምስት ዓመታት እንዲደፈን ፣ እንዲደናበርና መንግስት ተብየው እንደልቡ ሕዝብን ፣ የሃይማኖት ተቋማትንና መሰሎችን በግፍ እንዲገል ፣ እንዲያሰቃይ ፣ ወደ እስር ቤት እንዲያግዝ፣ እንዲያዋርድ ወ.ዘ.ተ. የራሳቸሁን ሚና ስለተጫወታችሁና አስተዋፅኦ በማበርከታቸው እንዲሀም በወገኖቻችን ላይ በተለይ በወለጋ ፣ በአጣየ ፣ በቤንሻንጉል ፣ በደቡብና በመላ ኢትዮጵያ ለተፈፀመው ወንጀል እጃቸው እንዳለበት ስለሚታወቅ ጊዜ ሲመጣና ነፃነት ሲታወጅ ዋጋ እንደምትከፍሉ ልትገነዘቡ ይገባል እንላለን።

ሕዝብ ነቅቶ ፣ በቃ ብሎና ታግሎ መከራና ሞቱን እንዳያስቆም የማዘናጋት ስራ ስለሰራችሁ “እንደጺላጦስ” እጃቸውን ታጠባችሁ ከወንጅሉ ነፃ ነን ልትሉ አንደማይቻላችሁ ልትገነዘቡ ይገባል እንላችዋለን።

ህሊናቸው እያርበተበታቸው ፣ እየሸነቆጣቸው ፣ ቅር ቅር እያላቸሁና ቁራሽ የጣለላችሁ መንግስት እንዳይነካ ፣ እድሜው እንዲራዘም በሚል ፈሊጣዊ ዘይቤ እንደዚህ አይነት በደም የተቀላ የሚያንገሸግሽ “የቁራ ጨኅት” የመሰለ የሽንገላ ፅሁፍ መፃፋችሁና መልእክት በዚህ የመከራ ወቅት ማስተላለፋቸሁ ባይገርመንም አካሄዳቸው በጣም ያስተዛዝባል።

ምን አለበት በሰለጠነው ዓለም እየኖራችሁ ስራቸውን እየሰራችሀ ሕይወታሁን ቢትገፉ ፣ ካልሆነ የትግሉን ስልት ስላላወቃችሁት ” ራስ ሳይጠና ጉተና” እንዱሉ ዝም ማለትን ማንን ገደለ ።

ቢያንስ ቢያንስ በዚህ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ “የሎሄ የሎሄ” እያለ ” ወይ ውረድ ወይ ፍረድ” እያለ ወደ አምላኩ እያንጋጠጠ ባለበት ሰዓት የተሰጣችሁን የአቃጣሪነት መንዳ እየቆረጠማችሁ በመኖር ፋንታ መዘላበድና መዘላበድና “እንደ እከካም አህያ” በገዳይ ትክሻ ጎን መታከክ ምን ይፈይዳል። ታዘብናችሁ እናንተ ከሞቱት በላይ ፣ ካሉት በታች ናችሁ እንላለን ደጋግመን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዓረና-መድረክ በመቀሌ የጠራው ሰለማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በህወሓት መሪዎች ታገደ

በየስርዓቱ “አለን ፣ አለን እና እኛ ያላቦካነው ሊጥ አይጋገርም አላችሁሳ” ጃል ፣ በቃችሁ። ትግሉን ለፋኖ ፣ ለዘርማና ለተተኪው ወጣት ትውልድ ስጡት እንላለን። እነ “እምቢ አላረጅም” ሙሽርናና ፖለቲከኛነት እኮ የዕድሜ ገደብ አለው።

በቃ ፣ በቃ ፣ በቃ ” ሲበዛ እኮ ማርም ይገለማል ። ሞት እኮ የገበጣ ጭዋታ አይደለም ። ወይ ነዶ ዘንድሮ ፣ በስንቱ እርር ፣ ድብን እንበል ፣ ቁስላችን እስኪ ሽርና ለበደላችን አግባብ ያለው ፍትህና መልስ እስክናገኝ ድረስ ከፊታችን ዞር በሉልን እባካችሁ እንላለን።

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ

1 Comment

  1. ተዘራ እነዚህ አንተ አገር ያሉ ዲያስፖራዎች እንደ ብአዴን ስንቴ ይለዋወጣሉ? በነገራችን ላይ ተረቱ ተለውጦ አሁን ሰው እስስት አትሁን አይልም ብአዴን አትሁን ነው የሚለው። መንጃ ፍቃድ አንተ አውጣላቸው እኔ አሮጌ መኪና ገዝቼ እሰጣለሁ ከዛ ሰርተው መኖር ይጀምሩ ይሆናል እኛም እረፍት እናገኛለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published.