የአስራ አምስት ቀን ህፃን! – በላይነህ አባተ

289659386 10159901026834393 7717595044600991369 n 1ንፁህ የአማራ ደም ወለጋ ተንጣሎ፣
ጠራርጎ ሊወስደው ዓባይ መጣ ደሞ፣
የተከሉት ችግኝ ስላልዋጠው መጦ፡፡

የደም ጅረት ሲፈስ ፀጥና እረጭ ያሉ፣
የዓባይ ጎርፍ ሲባል መብረቅ ይሆናሉ፡፡

የአስከሬን ተራራን ተመጤፍ ያልጣፉ፣
ምሁር ተብዮዎች ግድብ ይዘክራሉ፡፡

የአስራ አምስት ቀን ህፃን ተደፍታ ስታለቅስ፣
ተናቶች ታያቶች የሬሳ ክምር ውስጥ፣
ምኑን ሰው ሆንና ቆመን የምንሄድ፡፡

ኧረ ተው የሰው ልጅ በሰውነት ቀጥል፣
ተበግ መንጋ አትውረድ በአባይ በመደለል፡፡

በላይነህ አባተ ([email protected])
ሰኔ ሁለት ሺ አስራ አራት ዓ.ም.

WEB ETHIOPIA OROMIA 1000X562

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሀቢባ መሐመድን ጨምሮ የ32ቱ ሰዎች ክስ ለሕዝብ ክፍት እንዲሆን ጠበቆቹ ጠየቁ

Leave a Reply

Your email address will not be published.