ጠ/ሚኒስትሩ ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ፣ የሰላም ሚኒስትሩና ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የመንግሥት ሹማምንት ሥልጣናቸውን ይልቀቁ።

Killersዶክተር_ቴዎድሮስ
ሰላምን እየገደሉ በሰላም መኖር አይቻልም
================
1. ገዥዉ ፓርቲና መንግሥት የችግሩ እንጂ የመፍትሔው አካል ሊሆኑና ኃላፊነታቸውን ሊወጡ አልቻሉም። ጠ/ሚኒስትሩ ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ፣ የሰላም ሚኒስትሩና ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የመንግሥት ሹማምንት ሥልጣናቸውን ይልቀቁ። የፌዴራል ፓርላማው ፣ የአማራና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤቶች የአፈና መሣሪያ በመሆናቸው ይበተኑ። ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያካተተ የብሔራዊ መድህን የሽግግር መንግሥት ይቋቋም።
2.የዘር ማጥፋት ድርጊቱ የብሔራዊ ደህንነት አደጋ በመሆኑ በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይታወጅ። በአሸባሪ ኃይሎች ላይ ሀገር አቀፍ ዘመቻ ይከፈት። የሀገር መከላከያና የየአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች በአንድ ሀገራዊ ዕዝ ሥር ይዋሉ። በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ ጥቃት የሚደርስባቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ ነዋሪዎቹን በሚወክል በተቀናጀ የሲቪልና ወታደራዊ
አመራር ስር ይዋሉ።
3. በየደረጃው ያሉ የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ፣ የኦሮሞ የፀጥታና ደህንነት አካላት ፣ ባለፉት አራት ዓመታት በሚመሩት ክልል ውስጥ በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን የዘር ማጥፋት ድርጊት ማስቆም ባለመቻላቸው ፣ ለአሸባሪዎች መዋቅራዊና ፖለቲካዊ ከለላ በመስጠታቸውና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በዘር ጭፍጨፋና ሰብአዊ ወንጀሎች ተሳታፊ መሆናቸው በአስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ።
4. በአማራ ስም በፌዴራልም በክልልም የተሰየሙ ባለሥልጣናት ፣ በፌዴራልና በክልል ምክር ቤቶች ያሉ እንደራሴዎች የህዝባቸውን አደራ በአግባቡ ሊያስከብሩ ባለመቻላቸው የአማራ ህዝብን ይቅርታ ጠይቀው ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ይልቀቁ። የራሳቸውን ሥልጣንና ጥቅም ከህዝብ ህልውና ያስቀደሙና አልፎም ለገዳዮች የፖለቲካ ሽፋን የሰጡ ባለሥልጣናት ከመንበራቸው ወርደው በህግ ይጠየቁ።
5. የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለይም የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና ሌሎችም እግራቸውን በሰላምና በአመፅ መካከል ያንፈራጠጡ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ በተደጋጋሚ የጥቃት ሰለባዎችን በመወንጀል ፣ የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ በማድረግ ተግባር በመሳተፋቸው ከሰላማዊ ፓርቲነት ይታገዱ አመራሮቹም በህግ ይጠየቁ። ለአሸባሪ የዘር ጨፍጫፊዎች ሽፋን በመስጠት የተሰማሩ የኦሮሞ መገናኛ ብዙሃን ፈቃዳቸው ይሰረዝ ፣ በህግ ይጠየቁ።
6. የአማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የሲቪክ ማህበራት ፣ የአማራ ፋኖ ፣ ሚሊሻ ፣ ምሁራንና ለህዝባችን የማያባራ ውርደትና ሞት ከተጠያቂነት አናመልጥም። በተለይም የፖለቲካ ፓርቲዎች ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ ትግሉን ለመምራት ካልቻልን ፣ የገዳዮች መሣሪያ እንዳንሆን ህዝባችንን ይቅርታ ጠይቀን ችቦውን እናስረክብ። በሀገር ውስጥና ባህር ማዶ የምንገኝ የአማራ ማህበረሰብ ክፍሎች በሙሉ ህዝባችንን ከጥቃት ለመከላከልና እጣፋንታችንን ለመወሰን በአጭር ታጥቀን እንነሳ።
7. መላዉ ኢትዮጵያውያን ወገኖች የመጣንበት የተረኝነትና የዘረኝነትመንገድ እንደማያዛልቅ አይተናል። ከእንግዲህ ሀገራችን አንዱ እየገደለና ሌላው እየሞተ ፣ የቀረው ዳር ቆሞ እያየና የሞት ወረፋ እየጠበቀ ልትቀጥል አትችልም። ወይ በጋራ ሰላማችንን አስከብረን በአንድነት እንኖራለን ፣ አለያም በማያባራ የደም መፋሰስ እንበታተናለን። ሰላምንራሱን እየገደሉ መኖር አይቻልም
292119430 5235186876571276 2936118020736292885 n
1) የሰሞኑ የአማራ ህፃናት እና እናቶች ጭፍጨፋና መታረድ እራሱ አብይ በደም ፍላት እልቂት ቀስቃሽ የአማራ የጥላቻ ንግግር በማድረግ ነበር::
2) ከዚህ በፊት OBN ብቻ እንዲዘግብ ተደርጎ መተከል ላይ አንድ የአካባቢ “ሽማግሌ” የተባሉ ነገር ግን የክልሉ ም/መሪ የነበረ በኦነግና ህወሃት የአማራ ጥላቻ የተጠመቀ ካድሬ ከ30 ደቂቃ በላይ እልቂት ቀስቃሽ የጥላቻ ንግግር እንዲያደርግ (ቀድሞ በተዘጋጀ መልኩ) አብይ ዝም ብሎ መርዙ እንዲረጭ አደረገ:: ማታውኑ 250 አማራዎች ተጨፈጨፉ:: በጅምላ በዶዘር ተቀበሩ:: አስገዳዩ አብይ አህመድ ነበር::
3) ፓርላማ ላይ ከወሎ-ከሚሴ የተወከሉ ከበቀለ ገሪባና ኃይሉ ጎንፋ የባሱ ኦነጎች የአማራ ፖሊስ ከአማራ ክልል ይውጣልን ብለው በጥላቻ የደም ስራቸው ተወጥሮ እልቂት ቀስቃሽ ንግግር ሲያደርጉ–አብይ እንደፈለጉ እንዲናገሩ አደረገ:: “አማራ ለምን ይጨፈጨፋል” ብለው ያለቀሱ የፓርላማ አባላትን ግን ለፍተኝ ተግሳፅ (ያው ለኡዙ ፓርላማ ትእዛዝ) ሰጠ::
ለ99 ጊዜ:- የአማራ የዘር እልቂት የሚፈፀመው በአብይ አህመድ መሪነት: በኦህዴድና ኦነግ አስፈፃሚነት ነው::
ተጨማሪ ያንብቡ:  በምዕራብ ወለጋው ጥቃት ወቅት ታግተው የተወሰዱ ሰዎች እንዳሉ ተገለጸ

Leave a Reply

Your email address will not be published.