ሶስት ለ ፩ ኢትዮጵያ “በሬ ካራጂ  ”

ዘመን  ሂዶ ዘመን በተተካ ቁጥር  ኢትዮጵያ እና ጠላቶቿ አመች የሚሉትን አጋጣሚ እየጠበቁ ሲፈልጉ አንድ ሲላቸዉ ሶስት እየሆኑ ኢትዮጵያን ማዋረድ እና የቁርጥ ቀን ልጆቿን ማሳደድ የዉርስ ባህሪ አድርገዉታል ፡፡

የዉጭ እና የዉስጥ ዕናት ጡት ነካሾች ዛሬም እንዳለፉት ጊዜያት አንድም ሶስትም ሆነዉ በዘመን መለዋወጥ ሂደት ቅርፅ እና መልክ እየቀያየሩ አገሪቷን እና ህዝቧን እንደ መዥገር በመላ አካላቸዉ በመለጠፍ ፣በማድማት እና በመጠጣት እያገረጧት እና እያደሟት ይገኛሉ ፡፡

ከቅርብ የክህደት እና ክፋት ጊዜ ስንነሳ ከ፪ኛዉ የኢጣሊያ ወረራ መባቂያ ማግስት በአምስት ዓመት የነፃነት ተግል ዘመናት የህይወት እና የደም ዋጋ የከፈሉትን ጀግኖች አገሪቷን እና ህዝቡን በትኖ ስደትን የመረጠዉ የስርዓቱ አቀንቃኞች ከስደት መልስ ከታሪካዊ የዉጭ ጠላት ጋር በማበር የዘዉድ ስርዓቱን በይስሙላ ለመመለስ በህቡዕ የእጂ አዙር ግዛቱን ዕዉን ለማድረግ ምኞት የነበረዉ የወቅቱን ቅኝ ገዥዎች  ከዉስጥ ከኃዲዎች ጋር በመሆን የኢትዮጵያዉያንን የነፃነት ፋና ወጊዎች በግፍ እንዲሳደዱ ፣ እንዲወገዱ እና እንዲዋረዱ በማድረግ ተባብረዋል ፡፡

ለዚህም የማይረሳዉ የወቅቱን ፈርጣኝ የስርዓቱ ግሳግሶች ከአገራቸዉ እና ከህዝባቸዉ በላይ ለስልጣን እና ሀብት ይጓጉ የነበሩት  እንደ በላይ ዘለቀ ላቀዉ የመሳሰሉትን ጀግኖችን  በእነኝ የዘመናችን ከኃዲዎች ቀደምት አያቶች እና የስርዓቱ አምላኪዎች ለሞት ዳርጓል ፡፡

ጊዜዉን ጠብቆ ከሰላሳ ዓመት የኢትዮጵያ የትግል በኋላ በ1960ዎች መባቻ ጀምሮ በነበረዉ ህዝባዊ ንቅናቄ ግንባር ቀደም የህዝብ ድምፅ እና ክንድ የነበሩትን በተለይም እንደ ዓምላክ ይፈራ የነበረዉን የዘዉድ ስርዓት ፊት ለፊት የተጋፈጠዉ የዓማራ ህዝብ እና ልጆች መሆኑን የሚረሳ አይደለም ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ግንቦት 7 አድባር ትከተልህ!

ነገር ግን  በክህደት እና በስልጣን ስስት የኢትዮጵያን ህዝብ የዘመናት ትግል እና የትግል ዉጤት ከኋላ እንደ አይጥ ተደብቀዉ የነበሩት የትግሉን መሪዎች በተለያ ሴራ ጭዳ አድርገዋል ፡፡ የአገር ባለዉለታወችን ከአገር ጠላቶች ጋር ደባልቀዉ በተለያ መንገድ አስወግደዋል ፡፡ ይህ ሁሉ የሆነዉ በዉጭ ጠላቶች እና በዉስጥ ባንዳ እና የከዳ የከኃዲዎች ሶስት አንድ ጥምረት ነበር ፡፡

የኢትዮጵያ ጠላቶች ምኞት በግንባር ቀደምትነት ለዘመናት አገራቸዉን እና ህዝባቸዉን ክደዉ ያደሩ ድመቶች ሶስትም ፤ አንድም እየሆኑ  ኢትዮጵያን ለማፍረስ ይቻላቸዉ ዘንድ ሶስት ሆነዉ ሶስት ብለዉ ኢትዮጵያ ፤ ኢትዮጵያዊነት እና ዓማራ  በጠላትነት በመማል የተነሱት በግላጭ የ 1968 ዓ.ም. የብሄራዊ አንድነት እና ሉዓላዊነት ማርከሻ የአጥፍቶ ማጥፋት ስምምነት (Manifesto) እና የዚህ ተቀፅላ የሆነዉ ህገ- ኢህአዴግ በጥፋት ቅብል ዛሬ ከምንገኝበት የመከራ ጊዜ ጠርዝ አድርሶናል ፡፡

ኢህአዴግ አንድነቱም ሆነ ሶስትነቱ እየተድበሰበሰ እና ጥፋትን በጥፋት እያለባበሰ በፍትህ እና ዕኩልነት ስም በከተማ  በሌላ በኩል በነፃ አዉጭ ትግል ሽፋን በገጠር ( ጫካ/ በርኃ) የመከራ ዙሩ የማያልቀዉ  የኢትዮጵያ ህዝብ  ከግማሽ ክ/ዘመን ጀምሮ አስካዘሬ የህይወት እና ደም ግብር እንዲከፍል ተገዷል ፡፡

ይህ የማያባራ የኢትዮጵያ እና ዜጎች መከራ የኢትዮጵያን እንደ አገር የቀደመ ታሪኳን እና ዳር ድንበሯን ለማስከበርም ሆነ ለማስቀጠል ደንቀራ መሆናቸዉ እየታወቀ በመለባበስ  ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሩ ሲበባስ ይስተዋላል ፡፡

ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ልክፉቱ እና ሰንኮፉ ከዉስጥ ሆኖ ሳለ በማይረባ  ሰሞነኛ ማደናገሪያ ወደ ዉጭ ማላከክ የራስ ቁስል ትቶ ሌላዉን ማከክ  ኢትዮጵያን ሆነ ህዝቧን ከመከራ ወደ መከራ የሚዳርግ  ከመሆን ሊያድን አልቻለም  ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አማራ ሆይ አሁንም ጉድህን ስማና ላልሰማው አሰማ! - ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

የኢትዮጵያ አንድነት እና የህዝቦች ደህንነት የሚሳስባቸዉ ኢትዮጵያዉያን ፣ ዓማራ እና የዓማራ ህዝብ አንድነት ፣ ህብረት እና መደራጀት እና የፋኖ  ህዝባዊ ቅቡልነት ማበብ ምቾት የሚነሳቸዉ  ሲኖሩ ፀረ ኢትዮጵያ ቁመናቸዉን የሚያሳይ መሆኑን  በተለያ ጊዜ ከሚያስተጋቡት የፍርኃት እና ጥላቻ መልዕክት በተጨማሪ በዕኩይ ተግባራቸዉ በተለያየ ጊዜ ይገለጣሉ ፡፡

ኢህአዴግ በሶስት ዕግር ሶስት ቦታ ረግጦ እና አተገላብጦ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል እንዳለችዉ ….በጉያዉ አቅፎ እና ደግፎ የሚንከባከበቸዉ በስልጣን እና ጥቅም ካልሆነ በዓላማ የማይለያዩ መሆናቸዉን ሁሉም በኢትዮጵያ ፣ ኢትዮጵያዊነት እና ማንነት ጥቃት እና ዉርደት ላይ የግባቸዉ መነሻ እና መዳራሻ መሆኑን ካለፉት የረጂም ዓመታት የመከራ ታሪካችን የሚቀዳ ዕዉነታ ነዉ ፡፡

ዛሬ ደግሞ ከሶስት የኢትዮጵያዊነት ጉልቻ ወደ ፬ኛዉ  “ፋኖ ” ለዘመናት የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነት ተጋድሎ የማንነት ፣ የዕምቢ ባይነት እና የአርበኝነት ታሪክ በአገራችን ቀርቶ ዓለም አቀፍ ጠላት ሳይቀር የሚመሰከርለት የኢትዮጵያ ህዝብ ቁርጥ ቀን የመከራ ጊዜ ፈጥኖ ደራሽ  “ፋኖ ” ልደት  የሽ ዘመናት ድምር ሆኖ ታሪካዊ እና ብሄራዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች  በጥላቻቸዉ እና በፍርኃታቸዉ ስፍር ቁጥር ማጣት የጠነሳ የህዝብ እና የአገር ባለዉለታነቱን በክህደት ለሚያልፈዉ የስልጣን እና ጥቅም ፍላጎት እና ለከንቱ ዉዳሴ ሲሉ ይህን ሀቅ ለመደባበቅ የማይምሱት ዐፈር ፤የማይቆርጡት ቅጠል እንደማይኖር መታወቅ አለበት ፡፡

ስለ ኢትዮጵያ  የሚናገሩ በኢትዮጵያ ግዛት  እና ህዝብ ጫንቃ እየኖሩ ኢትዮጵያን ፤ ኢትዮጵያዊነትን እና የኢትዮጵያን አስኳል ማህበረሰብ ህብር እና ትስስር አምርረዉ የሚጠሉ ፀረ-ኢትዮጵያዉያን እሽሩር ማለት ያገባኛል ለሚል ሠባዊነት የሚሰማዉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በፅኑ ሊቋቋመዉ ይገባል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል - አምባቸው ዓለሙ (ከወልዲያ)

ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ ምድር እና ግዛት  ኢትዮጵያዊነት  በጠላትነት የሚታይበት የጌታ እና ባርነት ፣ የኗሪነት እና ባይታዋርነት  ፣ የሀብት እና ድህነት  ፤ስደት እና ሞት ታሪክ መለወጥ አለበት ፡፡ ከዚህ ዉጭ  ለራሱ እና ለአገሩ ትንሳዔ የሚተጋ ኢትዮጵያዊ የሚሰጠዉ ቅድሚያ ሊኖር እንደማይችል ተገንዝቦ በንቃት እና በአንድነት ለዘላቂ ዕድገት እና ነፃነት ዘብ መቆም አለበት ፡፡

የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን  ጠላቶች( ኢህአዴግ እና መሰሎች ) ዝንት ዓለም አገር እና ህዝብ አጋም እና ቀጋ ሆኖ እንዲኖር የሚሰሩት የጥላቻ እና በቀል ተግባር ከነአስተሳሰቡ በመንቀል  ዘላለማዊ አገር እና ትዉልድ እንጂ ጥቅም እና ስልጣን ቀሪ መሆኑን ተረድተዉ  ሳይመሽ ለቤተሰቦቻቸዉ ጠላት ከማብዛት በመቀነስ  ንስኃ በመግባት አሞሟታቸዉን  እና አይቀሬ ሽኝታቸዉን ሊያስቡበት እና ሊያስተካክሉበት የሚችሉበት ጊዜ እና ዕድል እንደ ጥላ ሳያልፍ ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡

 

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

NEILOOSS-Amber

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.