በፊደራል ደረጃ  ልዩ ትኩረት የተደረገበት  የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፣ የ 2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ  ፈተና ልዩ መረጃ  –  በመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

በመሥከረም 28/ 2015 ዓ/ም በሶሻል ሣይንሥ ተማሪዎች ፈተና ይጀመራል ። ይህ በፈተና አሰጣጡ ልዩ የሆነው አገር አቀፍ ፈተና ፣ የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን ጥንካሬ እና ደካማ ጎን በግልፅ እና በተጨባጭ የሚያመላክት ፣ በትምህርት ጥራት ላይ በትጋት እንዲሰራ የሚያደርግ ነው ። ተብሎ ይጠበቃል ። እንደሚታወቀው ገንዘብ ተኮር የትምህርት አሠጣጥ በሁሉም ትምህርት ቤቶች መኖሩን ( በግል ትምህርት ቤቶች በክፍያ በመንግሥት ተምህርት ቤቶች ኮራብት በሆኑ መምህራን የተነሣ … )  በይፋ የሚያሳውቀን ይኽ በየዩኒቨርስቲ የሚሠጠው ፈተና በመሆኑ ፣ የትምህርት ሚኒሰትር  እና መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት እንደሰጡት ይታወቃል ።

ይህ ፈተና በአገር አቀፍ ደረጃ ፣ በፊደራል  ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ነው የሚካሄደው ። ፈተናው ልዩ ጥበቃ ይደረግለታል ። ፈታኝ መምህራንም በዕጣ ነው ፣ ለየዩኒቨርሥቲዎቹ የሚመደቡት ።   እያንዳንዱ አሥፈታኝ ትምህርት ቤት ፤ ተማሪዎች  እና ዩኒቨርስቲዎችን የሚመለከት ግዴታ ና መብትም በግልፅ ወጥቷል ። ይህንን በተመለከተ ያገኘሁትን መረጃ አሣጥሬ ለተማሪዎች እና ለወላጆች አሣውቃለሁ ።

 የአሥፈታኝ ተምህርት ቤቶች ግዴታ

  1. የተፈታኝተማሪዎችንሥም ዝርዝር አሥቀድሞ ለሚመለከተው ክፍል ፕሮቶኮሉን በጠበቀ መልኩ ያሳውቃል ።

2 . በበቂ ሁኔታ ተፈታኙን ሥለ ዩኒቨርስቲው እና ሥለ ፈተናው ህግ ያሣውቃል ።

3 . በሳይኮሎጂ የተጎዱትን ተማሪዎች ( በኮቪድ እና በሶሻል ሚዲያ ውዠንብር ) ሞራል መገንባትና ከኩረጃ ይልቅ በራሳቸው አእምሮ መሥራት አማራጫቸው መሆኑንን በወጉ ያሥረዳል ። አቅማቸውን ሣይጠቀሙ ቀርተው ጠባቂ በመሆን እንዳይወድቁ አሥቀድሞ ያነቃል ።

4 . የትምህርት ቤት እና የአድሚሽን ካርዳቸውን እንዳይረሱ ያሳስባል ።

5 . እያንዳንዱ አሥፈተኛ ት/ቤት ፤ የማህበራዊ ሣይንሥ ተፈታኞችን በመሥከረም 28/01/2015 የተፈጥሮ ሣይንሥ ተማሪዎችን ደግሞ በጥቅምት 6/ 2015 ዓ ም ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርስቲዎች ቀጥሮ የማሥረከብ እና ፈተናቸውን ሲጨርሱ ቆጥሮ የመረከብ ግዴታ አለበት  ።

 

የተፈታኝ ተማሪውች ግዴታ 

  1. አንሶላ፣ብርድልብስ እና የሌሊት  ልብሶች ( ቱታ እና ፒጃማ ) ይዘው መምጣት አለባቸው ።
  2. ማንኛውንም ብልጭልጭ ቁሣቁሥ ፣ የመዘነጫ መነፅር ፣ የጆሮ ጌጥ ፣ ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ሌላ የጌጥ ቀለበት ማድረግ የለባቸውም ።
  3. ማንኛውም  ሞባይል ሥልክ ፣ ላፕቶፕ ፣ ታብሌት ፣  ይዞ ወደ ዩነኒቨርስቲ መግባት ክልክል  ነው ።
  4.  እርሳስ ፣ ላቢስ፣ መቅረጫ ፣ ማሥመሪያ መያዝ አለባቸው ።
  5. የትምህርት ቤታቸውን እና የመፈተኛ መታወቂያቸውን  የመያዝ ግዴታ አለባቸው ።
  6.  ዩኒቨርሲቲከገቡበኋላ በሚገለፅላቸው  በዩኒቨርሲቲው ህግ የመተዳደርና ህጉን የመጠበቅ  ግዴታ አለባቸው ።
  7. እርጉዝተማሪዎችመፈተን አይቹሉም ። ከወለዱ በኋላ የሚፈተኑበትን ሁኔታ መንግሥት ያመቻቻል ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት ‹‹ከኮሎኔሉ ወደ ኮሎኔሉ!!!›› ብዕረኞች እልፍ ጠመንጃን የማረኩባት ሃገር !!!

የዩኒቨርስቲዎች ግዴታ

  1. አሥቀድሞ  በተጠቀሰው ተማሪዎችን የመቀበል ቀን ፣ ከሚመለከተው አካል አሥቀድሞ በተረከቡት ሰነድ ፣ አንድ በአንድ ተማሪዎችን ማንነታቸውን በማረጋገጥ እና ከላይ የተጠቀሰውን ግዴታ ተማሪው ማሟላቱን በማረጋገጥ ፣ ህጋዊ ፍተሻ አድርገው ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርስቲዎቻቸው የማሥገባት ግዴታ አለባቸው ።
  2. ለተፈታኝ ተማሪዎች ፣ የሚያድሩበት ክፍል ፣ አልጋ እና ፍራሽ አሥቀድሞ አዘጋጅተው የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው ።
  3. ለተማሪዎቹቁርስ፣ ምሣና እራት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ። ( በምግብ የሚነሳን ቅሬታ ከወዲሁ ለማሶገድ ዩኒቨርስቲዎቹ ትኩረት ሊያደርጉበት ይገባል ።)
  4. የተማሪዎቹ ፀጥታ እንዳይናጋ ፣ ማንኛውንም የፀጥታ ሥጋት እንዳይኖር ከፍተኛ ጥበቃና ምሥጢራዊ ክትትል ያደርጋል ።
  5.  ፈተናውንበተመለከተለተማሪዎቹ መብራሪያ እንዲሰጥ አደራሾችን ያመቻቻል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.