ደረጀ ዘለቀና መሰሎቹ ፀራማራ “ምሁራን” – መስፍን አረጋ

ጠላትህ ሲጀምር ራሱን ማጋለጥ፣ እስከሚጨርስ ታዘብ ብለህ ጸጥ

(Never interfer with your enemy while he is destroying himself, Napoleon Bonapart)

 

ወያኔ አዲሳባን ተቆጣጥሮ በጦቢያ ላይ አዛዥ ናዛዥ መሆኑን እንዳረጋገጠ በመጀመርያ ያደረገው፣ ባዲሳባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሚያስተምሩትን፣ የወያኔን ፀራማራ ጎጠኛ ፖሊሲ ይቃወማሉ የሚላቸውን ታላላቅ የአማራ ምሁራን በብጣሽ ወረቀት ማባረርና ወደ ዩኒቨርስቲው ዝር እንዳይሉ በጥብቅ መከልከል ነበር፡፡  በዚህ ድርጊቱ በግልጽ ያረጋገጠው ደግሞ በወያኔ ዘመን አማራዊነት የሚሰማቸው፣ ለአማራ ሕዝብ የሚቆረቆሩ ምሁራን፣ በማናቸውም ዩኒቨርስቲ ውስጥ (በተለይም ደግሞ አዲሳባ ዩኒቨርስቲን በመሰሉ ትላልቅ ዩኒቨርሲቲወች ውስጥ) ቦታ እንደማይኖራቸው ነው፡፡  ጭራቅ አሕመድ የነገሰበት የኦነግ ዘመን ደግሞ ሌላ ምንም ሳይሆን የወያኔ  ፀራማራ ፖሊሲ እጅግ በከፋ ሁኔታ የቀጠለበት የአማራ ሰቆቃ ዘመን ነው፡፡

ስለዚህም በወያኔና በኦነግ ዘመን በረዳት ፕሮፌሰርነት (assistant professor)፣ ተባባሪ ፕሮፌሰርነት (associate professor) ወይም ሙሉ ፐሮፌሰርነት (full professor) ባዲሳባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዲያገለግሉ የወያኔንና የኦነግን እሽታ ያገኙ ሰወች ሊሆኑ የሚችሉት ከሚከተሉት ካራቱ ውስጥ አንዱን ነው፡፡

 1. የወያኔንና የኦነግን ፀራማራ ሕገመንግስሥት በሙሉ ልባቸው አምነውበት የተቀበሉ፣ የአማራን ሕዝብና አማራዊነትን አምርረው የሚጠሉ የትግሬና የኦሮሞ ፀራማራ ጽንፈኞች፡፡
 2. ያለም አገሮች እንዴት እንደተመሠረቱ የማያውቁ፣እንጨት ሳይቆረጥ ቤት እንደማይሠራ ያልተገነዘቡ የራሳቸውንና ያገራቸውን ማንነት በቅጡ ያልተረዱ በመሆናቸው የተነሳ፣ በወያኔወችና በኦነጎች ስብከት የጥፋተኝነት ወይም የዝቅተኝነት ስሜት እንዲያድርባቸው ተደርገው፣ የራሳቸውን አማራነት ከመጥላት አልፈው የአማራን ሕዝብ አምርረው እንዲጠሉ የተደረጉ፣ ስለ ብሔር ምንነት ሳይማሩ ስለ ብሔር ጭቆና የሚደሰኩሩ፣ በማርክሲዝም ጥራዝ የነጠቁ፣ ቢከፍቱት ተልባ የሆኑ የዋለልኝ መኮንን ቢጤ ግልብ አማሮች፡፡
 3. ለሆዳቸው ሲሉ ለወያኔና ለኦነግ ያደሩ ሆዳደር አማሮች፡፡
 4. ወያኔና አነግ አሸናፊወች ስለሆኑ ብቻ፣ ከወያኔና ከኦነግ ጋር ለመሥራት የመረጡ (ወይም ደግሞ ከወያኔና ከኦነግ ጋር ከመሥራት ውጭ ምርጫ የሌላቸው) አልአማራ(አማራ ያልሆኑ) ግለሰቦች፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:   የናዚሥቶቹ የመቀበሪያ ቀን ቅርብ ነው “በሰፈርከው  ቁና ይሰፈርልሃል“ ከአባታጠቅ ምንዳሁነኝ

በተራ ቁጥር (1) ከተገለጹት ፀራማሮች ውስጥ ለአማራ ሕዝብ እጅግ አደገኛ የሚሆኑት ትክክለኛ ስማቸው አማራዊ የሆነው ወይም ደግሞ የአማራን ሕዝብ ማታለል ይችሉ ዘንድ (ልክ እንደነ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋና ከበደ ጫኔ) ስማቸውን ወደ አማራዊ ስም የቀየሩት ናቸው፡፡

በተራ ቁጥሮች (2) እና (3) የተገለጹት ፀራማሮች ለአማራ ሕዝብ እጅግ አደገኛ የሚሆኑት፣ አማራ ስለሆኑ ብቻ የአማራን ሕዝብ ለጉዳት አይሰጡም ብሎ የአማራ ሕዝብ እምነት ካሳደረባቸው ብቻ ነው፡፡  እንደ እውነቱ ከሆነ፣ የአማራ ሕዝብ አስቀድሞ መታገል ያለበት፣ በተራ ቁጥር (1) የተገለጹትን የግንባር ጠላቶቹን ሳይሆን፣ በተራ ቁጥር (2) እና (3) የተገለጹትን የጉያ ጠላቶቹን ነው፡፡  አብናቶቻችን (አባቶቻችን እና እናቶቻችን) ጠላትማ ምንግዜም ጠላት ነው፣ አስቀድሞ መግደል አሾክሿኪውን ነው የሚሉት፣ የውጭ ጠላትን ማሸነፍ የሚቻለው የውስጥ ጠላትን አስወግዶ ውስጥን በማጠንከር ብቻ መሆኑን አጽንኦት ለመስጠት ነው፡፡

በተራ ቁጥር (4) የተገለጹት ግለሰቦች በነፈሰበት የሚነፍሱ (ወይም በነፈሰበት ከመንፈስ ውጭ ምርጫ የሌላቸው) በዋል ፈሰሶች ስለሆኑ፣ የአማራ ሕዝብ እነሱን ከጎኑ ማሰለፍ የሚችለው፣ ወያኔንና ኦነግን በማያዳግም ሁኔታ ድል በማድረግ አሸናፊነቱን ሲያረጋግጥላቸው ብቻ ነው፡፡

በወያኔ ዘመን የአዲሳባ ዩኒቨርስቲ አስተማሪወችና ሹሞች የነበሩትንና አሁንም በኦነግ ዘመን የሆኑትን እንደነ እንድርያስ እሸቴገነት ዘውዴዳኛቸው አሰፋደረጀ ዘለቀ እና በለጠ ሞላ ያሉትን ግለሰቦች፣ የአማራ ሕዝበ መመልከት ያለበት በተራቁጥሮች (1)፣ (2) እና (3) በተገለጹት መነጽሮች መሠረት ነው፡፡

አማራዊ ስም ያላቸው፣ ወይም ደግሞ አማራን ለማታለል ሲሉ ስማቸውን ወደ አማራዊ ስም የለወጡ የትግሬና የኦሮሞ ፀራማሮች፣ ወይም ደግሞ አማራ ሁነው አማራነታችን የሚጠሉ ፀራማሮች፣ ወይም ደግሞ ለሆዳቸው ሲሉ ላማራ ጠላቶች ያደሩ ሆዳደር ፀረማሮች፣ የአማራን ሕዝብ ከሚያጠቁባቸው የተለያዩ መንገዶች ውስጥ የሚከተሉት ሁለቱ ዋናወቹ ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እየተዋረዱ መገዛት እስከመቼ!?

አንደኛው መንገድ፣ ለአማራ ሕዝብ በሚታገል አብንን በመሰለ ድርጅት ውስጥ ተሹለክልከው በመግባት ያመራር ቦታወችን ይዘው፣ በድርጅቱ ላይ የአማራ ሕዝብ ትልቅ ተስፋ ማሳደር እስከሚጀምርና፣ ለአማራ ሕዝብ በቅን የሚታገሉት የድርጅቱ ሰወች በግልጽ እስከሚታወቁ ድረስ ከጠበቁ በኋላ፣ ድርጅቱን በማፈራረስ የአማራን ሕዝብ ተስፋ ማስቆረጥና ቆራጥ ታጋዮቹን ማስመታት ነው፡፡  ለንደዚህ ዓይነቶቹ ፀራማሮች ዓይነተኛው ምሳሌ በለጠ ሞላ ነው፡፡  በለጠ ሞላ የአማራ ሕዝብ ብዙ መስዋዕትነት የከፈለበትን ትግል አቅልጦ አበጠ እንጅ ስላልቀለጠ፣ ቀለጠ ሞላ ሊባል አይገባውም፡፡

ሁለተኛው መንገድ ወያኔንና ኦነግን በጽኑ የሚቃወሙ መስለው ከፍተኛ ያማራ ተከታይ ካፈሩ በኋላ፣ በድንገት እጥፍ ብለው በወያኔና በኦነግ ሚዲያወች ላይ በመቅረብ፣ የአማራን ሕዝብ ወያኔወችና ኦነጎች ከሚወቅሱትና ከሚከሱት እጅግ በከፋ ሁኔታ በመውቀስና በመክሰስ፣ የአማራ ሕዝብ መሪወቹን ሁሉ እንዲጠራጠርና ከእውነኛ መሪወቹ ጋር በሙሉ ልቡ እንዳይቆም ማድረግ ነው፡፡  ለንደዚህ ዓይነቶቹ ፀራማሮች ዓይነተኛው ምሳሌ ደረጀ ዘለቀ ነው፡፡  ደረጀ ዘለቀ ወያኔና ኦነግ ሲጣሉ ካደፈጠበት ወያኔና ኦነግ ሲታረቁ በድንገት ብቅ ያለው ያማራን ሕዝብ የሕልውና ትግል ለማጥለቅ (ወይም የማጥለቅ ተልእኮ ተሰጥቶት) ነው፡፡  የደረጀ ዘለቀ ፀራማራ ዓላማ የሚሳካው ደግሞ፣ የአማራ ሕዝብ ዋና ትኩረቱን በዋና የሕልውና ጠላቱ በጭራቅ አሕመድ ላይ ከማድረግ ይልቅ፣ በደረጀ ዘለቀ እንቶ ፈንቶ ላይ ካደረገ ብቻ ነው፡፡

የአማራ ሕዝብ፣ የሱ ወገን ይመስሉት የነበሩት ሕቡዕ ጠላቶቹ ራሳቸውን በራሳቸው ገሃድ አውጥተው ይፋ ጠላቶቹ መሆናቸውን ሲያረጋግጡለት ተስፋው ሊለመልም እንጅ ሊከስም አይገባም፡፡  ጠላቶችህን ማሸነፍ የምትችለው ጠላቶችህን በደንብ አውቀኻቸው ራስህን ከጠላቶችህ ሙሉ በሙሉ ስታጸዳ ብቻ ነው፡፡  ጠላቶችህ ራሳቸውን በራሳቸው ካጋለጡልህ ደግሞ ትልቁን ሥራ ራሳቸው ሰርተውልህ የራሳቸውን ሽንፈት ራሳቸው አቃረቡልህ ማለት ነው፡፡  ታላቁ ናፖሊዮን እንዳለው ጠላትህ ሲዋከብ ራሱን ሊያጠፋ፣ አንዳታውከው ድምጽህን አጥፋ (Never interfer with your enemy while he is destroying himself)፡፡  ደረጀ ዘለቀም ራሱን እያጠፋ ስለሆነ፣ የአማራ ታጋዮች ከሱ ጋር አታኻራ ገጥመው ራሱን ከማጥፋት ሊያውኩት አይገባም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በእውቀቱ ስዩም ስለ ድምፃዊዉ ኢዮብ መኮንን

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

 

 

12 Comments

 1. ትምህርት ሲበዛ ናላ ያዞራል የሚሉት ነገር እውነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ እስቲ እንተወው ትንሽ ችግር ላይ ነበርኩ ብሎናል ያለእኛ ማን አለው? ትምህርት ሲበዛ አእምሮ ይነካል የሚሉት ነገር እውነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ጊዜውን በምርምር ማሳለፉን ከሰውነቱ ክሳት መገመት ይቻላል፡፡ ምንም የማይሰማው ስለ ሆዱ ብቻ የሚያስብ ቢሆን እንደእነ ብርሃኑ ነጋ፤ዲማ ነገዎ፤ መራራ ጉዲና… ሰውነቱ ሞላ ይል ነበር እስቲ ጊዜ እንስጠው ነገሩ አልያያዝልኝ ብሏል፡፡ ዶር ደረጀ አዲሱ ጋር ያደረግኸው ቃለ ምልልስ ይሁን ስህተት ቢኖረውም፡፡ አዲሱም መስከረምም ወገን ናቸው እርከንህ ከፍ ብሎ ቴዎድሮስን የመሰለ የህዝብና የሃገር ጠላት ጋር በሱ ቦይ እየፈሰስክ ሃገርና ዜጋን መስደብህ ግ ን ይህ ጊዜ ሲያልፍ የምንተዛዘብበት ይሆናል፡፡ አሁን እንድርያስ እሸቴን ያየ እንዲህ አይነት ስህተት ይደግማል? አንዴ ሁኗል ይችን ስምህን ምን አድርገህ እንደምትመልስ አንተ ታውቃለህ ፡፡ አዲሱን ለምነህ ማብራሪያ ስጥበት ወደቦታው መመለስ ከተቻለ የእኛ ሰው መሃሪ ነው፡፡

 2. በአካባቢው ጸበል የለም እንዴ ይህን ሰው የሚያድን? ምን አይነት ጉድ ነው ሁሌ አፍራሽን በአፍራሽ ሃሳብ እያስታከከ ረብ የለሽ ነገር መለጠፉ? ጸረ አማራ፤ ጸረ ኦሮሞ ገለመሌ የሚባለው ሲጀመር በየጊዜው በተፈጠሩ ስርዓቶች የፓለቲካ አለቅላቂዎችና እኖር ባዪች ያኔም አሁንም አሉ ወደፊትም ይኖራሉ። ይህ በየትኛውም ሃገር አለ። ትላንት ከትላንት በስቲያ ሃገር የሸጡ፤ ህዝብን የገደሉና ሃብት የዘረፉ ስንቶች ናቸው በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ ተጠልለው የሚኖሩት? እነርሱን ማጋለጡ አይሻልም እንዴ? በቅርብ ቀን ጭራቅ አህመድ ኦነግ ሸኔ እና ሂትለር ኤስ ኤስ በማለት የጻፍከውንም ተመልክቸዋለሁ። እስከ መቼ ነው የሰው ጭንቅላት በቃላት ድላ ስንፈነክት የምንኖረው? እንዲህ ካለው የጥላቻ ጽሁፍ ህዝባችን የሚያተርፈው ምንድን ነው? ቢዘፈን የማይዘፍን ቢለቀስ የማያለቅስ የፓለቲካ አባዜ ይዞ ሁሌ እኔን ካልመሰላችሁ ጸረ እንዲህና እንዲያ ናችሁ ማለቱ የጥሎ ማለፍ ጫወታ እንጂ ሌላ ብልሃት የለውም። ጥለውን ያለፉም ራሳቸው በከፈቱት መንገድ ተጠልፈው የሰው መዘባበቻ ሲሆኑ በአይናችን እያየን ነው።
  ግን ደጋግሜ እንደምለው የሃበሻው ፓለቲካ ሌላው ላይ ድንጋይ ካልወረወረ ነገር ያሳካ አይመስለውም። ራሱ በሙስና ተነክሮ ሌላውን ሙሰኛ የሚል፤ ሁሌ ውስኪ እየተጋተ ለሌላው ውሃ የሚከለክል፤ የእኔ ዓለም ይኸ ነው በማለት ቤትና ንብረቱ አጥሮ የሌላው ሰቆቃና መከራ ምንም ከማይመስለው የሰው አምሳያ በባህሪ እንስሳ ከሆኑ ጋር እየኖርን ነው። አሁን እንሆ በሰሜኑ ጦርነት ያለቀው የሰው ቁጥር እትዬ ሌሌ ነው። ግን ምን ቸግሮ ለዚያውም ለጥቁር ሰው ደም። በአፍሪቃም ይፈሳል። በሌላም ቦታ ይጎርፋል። ችግሩ እኛ ነን። በቅርቡ አንድ ውሻ ልጅ ይነክሳል ሥፍራው በደቡብ አፍሪቃ ነው። የውሻው ፍጻሜ በቁሙ ማቃጠል ነው። ይህ ነው የእኛ ስብዕና። ያጠፋው ውሻው ነው የውሻው ባለቤት? እናንተ ፍረድ። ለነገሩ የመኪና ጎማ በሰው አንገት አድርገው ቤንዚን አርከፍክፈው አይደል እንዴ የራሳቸውን ሰዎች ሲያጋዪ የነበሩት የደቡብ አፍሪቃ ጥቁሮች። ተማረ አልተማረ ከመሰረቱ ጨካኝና አረመኔ የሆነ ሰው መዳኛ መድሃኒት የለውም። ችግራችን ብዙ ነው። መልካም የሰራና ክፉ ያደረገን የምንመዝንበት ሚዛን አንድ ነው። ያለቅጥ ያጋደለና ፍርደ ገምድል ሚዛን።
  የፓለቲካን ከንቱነት ለመረዳት ተመድ ላይ የተገተረውን (Let us beat the Swords into plowshares) ቅርጽ መመልከት ብቻ ይበቃል። የያኔው ሶቭየት ህብረት ለተመድ ያበረከቱት ስጦታ ነበር። ቁምነገሩ ሥራው የማን ነበር ነው። ያ ሰው የተወለደው (Dnipro, Ukraine) ዛሬ የትውልድ ሥፍራ እንዳልሆነ ሆናለች። ፓለቲካ እድሜ የጠገቡ መሪዎች ወጣቱን የሚያስጨሩስበትና ህዝቡን የሚያሸብሩበት ስልት ነው። ሌላው ሁሉ ማሟያ ውታፍ ነው። ለዚህ ነው ሃሳብን በሃሳብ ስንሞግት ወደኋላም፤ አሁን ያለንበትንም፤ ወደፊት እንሄዳለን ብለን የምናልመውንም ሁሉ ሚዛን ውስጥ ማስገባት ያለብን። ጎራዴውም ማረሻ አልሆንም። የምንገዳደልበትም መንገድ ከበፊቱ ይልቅ አሁን የቀለጠፈና ሰው አልባ እየሆነ መጥቷል። ጉራው፤ ፉከራው፤ ያዙኝ ልቀቁኝ ለዘሬ፤ ለወገኔ ለቋንቋዬ ለክልሌ የሚለው የጠባብ ብሄርተኞች እይታ ሁሉ ዛሬም አሻሮ ነው ቆይቶም አተላ ነው። አይረባም። ይልቅ ተዘርቶ በቅሎ፤ ተተክሎ አድጎ ሰውን የሚመግብና ለሰውና ለእንስ ሳ ጥላ የሚሆን ቋሚ ነገር እናድርግ። በመጨረሻም በዪፍታሄ ንጉሴ አንዲት ስንኝ ሃሳቤን ልቋጭ።
  አይዞህ የእኛ ጌታ ነግርህን አትርሳ
  አለስልሰህ ዝራ የስንዴውን ማሳ
  የተዘራችው ዘር ፈርሳና በስብሳ
  ታፈራለች ፍሬ ሙታ ስትነሳ።

 3. ተስፋ እንደ እውነት ከሆነ ትኩስ የፈለቀ ጸበል የሚያስፈልግህ አንተን ነው። ጽሀፍህን ሳጠናው አንድ ትንሽ ማደናገሪያ ጽሁፍ ከላይ አስቀምጠህ ሌላውን ብተናህን በጥሩ መንገድ መደምደሚያህ ታደርገዋለህ። ስለ ታረደው አማራ መከራ ስላለው አፋር ፣ስለ መከላከያው ጥቃት ሲነሳ እንደ እብድ ያደርግሀል። መስፍን አማራው አይታረድ ሰብአዊ መብቱ ይከበር ተሿሚዎቹና እበላ ባይ ምሁራን ተደርበው አያጥቁት ማለቱ ስህተቱ ምኑ ላይ ነው? ባንተ ቤት ማሸማቀቅህ ነው እንደምገምተው ጎንደር ወይም ጎጃም የተወለድክ የኖርክ በረከት ስምኦን ነህ። በምክር መልክ ፍልቀቃህን ተው አንተን የሀሳብ የበላይ school of thought ያደረገህ ማነው? ኢዜማን አትንኩብኝ፣ ኦነግን አትንኩብኝ ፣ህወአትን አትንኩብኝ መልካም አይደለም። አንድ ወጥ አስተማሪ ሀሳብ ካለህ እራስህን ችለህ ጽሁፍ ጻፍ የተሰጠኝ የስራ ድርሻ ኢትዮጵያውያን እንዳይግባቡ ማሳከር ነው ካልክ ተው ልትባል ይገባል። ሲጀመር ኢትዮጵያ የሚለውን መጠሪያ ተጠይፈህ ሀበሻ ነው የምትለን። ቅንነት ብዙ አይታይብህም ተስተካከል።

 4. ተስፋ እንደ እውነት ከሆነ ትኩስ የፈለቀ ጸበል የሚያስፈልግህ መስፍንን ሳይሆን አንተን ነው። ጽሀፍህን ሳጠናው አንድ ትንሽ ማደናገሪያ ማስመሰያ ሱንቅረህ ሌላውን ብተናህን በጥሩ መንገድ መደምደሚያህ ታደርገዋለህ። ስለ ታረደው አማራ መከራውን ስለሚበላው አፋር ፣ስለ መከላከያው ጥቃት ሲነሳ እንደ እብድ ያደርግሀል። መስፍን አማራው አይታረድ ሰብአዊ መብቱ ይከበር ተሿሚዎቹና እበላ ባይ ምሁራን ተደርበው አያጥቁት ማለቱ ስህተቱ ምኑ ላይ ነው? ባንተ ቤት ማሸማቀቅህ ነው ግን አይሆንም ሚዛንህ ካልተስተካከለ ዋጋ ያስከፍልሀል። እንደምገምተው ጎንደር ወይም ጎጃም የተወለድክ የኖርክ በረከት ስምኦን ነህ። በምክር መልክ ፍልቀቃህን ተወን አንተን የሀሳብ የበላይ school of thought ያደረገህ ማነው? የኢዜማን መሪ አትንኩብኝ፣ የኦነግን መሪ አትንኩብኝ ፣ህወአትን አትንኩብኝ መልካም አይደለም። አንድ ወጥራሱን ችሎ የሚወጣ አስተማሪ ሀሳብ ካለህ እራስህን ችለህ ጽፈህ አውጣና እንየው። የተሰጠኝ የስራ ድርሻ ኢትዮጵያውያን እንዳይግባቡ ማሳከር ነው ካልክ ተው ልትባል ይገባል። ሲጀመር ኢትዮጵያ የሚለውን መጠሪያ ተጠይፈህ ሀበሻ ነው የምትለን። ቅንነት ብዙ አይታይብህም ተስተካከል ካልሆነም እንደ ዶክተር ደረጀ ምዘናህ የተዛነፈ ከሆነ አንብብ፣ጠይቅ እንደ ፕላቶ ካልሆንኩ አትበለን ለሀገር አሳቢ ምሁራንን መጨርገድ የሙሉ ጊዜ ስራህ አታድርገው።

 5. Birega – ተከፋይና ቀልማዳ ፓለቲከኞች ሁልጊዜም ባልገባቸው ነገር ነው የሚወሸክቱት። አንቦ ጊዜ ወስዶ ምን ለማለት ተፈልጎ ነው ብሎ ነገር ማጤን የለም። የቢራ ቢልቃጥ እያቃጨሉና በዚህም በዚያም ይህን ያንም እየተጎነጩ እኔን ብቻ ስሙኝ ከሚሉ ዘላባጆች ሰው መራቅ የሚገባው የራስንም ሰላም ለመጠበቅ ነው። ባጭሩ በዘሩ ፓለቲካ ካበድት ጋር አብሮ ላለማበድ። ሃሳብህን ክብደት ለመስጠት ይመስላል አንድ መጣጥፍህን ሁለት ጊዜ የለጠፍከው። እኔ እንዳንተ ያለውን ወስላታ ላፍታም ጊዜ አልሰጠውም። በተደጋጋሚ እንዲህም እንዲያም እንደምትል ተመልክቻለሁ ይሻልሃል ብዬ ጠብቄ ነበር። ያ ግን አልሆነም። ድንጋይ መወራወርን ልማድ ካደረገ አተላ የሃበሻ የዘር ፓለቲካ ጋር አተካራ አልገጥምም። እንዳሻህ፤ እንደተረዳህ እንደ እንቁራሪት አብረህ ጩህ። እኔ ግን የሙታን ፓለቲካን አክ እንትፍ ያልኩት ዛሬ አይደለም።

 6. ·
  ይህ ስው አማኑኤል ወይንም ፀበል መግባት እንጀ ወደ ሚዲያ መቀረብ የለበትም:: የሚያወራውን የማያውቅ እርስ በእርሱ የሚጣረስ እንቶ ፈንቶ ነው ሲቀባጥር ያመሸው::

 7. ተስፋ እኛ አንድ ሃገር ነው ያለን አንተ በወጣትንትህ የተጣባህ የኢትዮጵያ ጥላቻ ዛሬ ላይ ይብስ እንደሁ እንጅ እንደማይሻልህ በተከታታይ ጽሁፎችህ ተረድቻለሁ እዚህ ነብስና ስጋይ ከሚላቀቅ የቴዎድሮስ ጸጋዬ የክብር እንግዳ ብትሆን በዛኛው ሰፈር ልዩ ክብር ያስገኝልሃል፡፡

 8. በእነዚህ “ዶክተር” የሚል ታፔላ ባንጠለጠሉ የጤናና የትዳር ችግር እንዳለባቸው ራሳቸው የሚመስክሩ ሰዎች እጅግ ውስብስቡ የሃገራችን ፖለቲካ ይተነተን ዘንድ መድረኩን የሰጡት ሚዲያ ተብዬዎች ሊወገዙ በህዝቡም ትኩረትና ክትትል ሊነገፉ ይገባል:: ወዳጄነህ የተባለው በትዳሩ ሁለቴ እንዳልተሳካለት እየመሰከረ የሚያስቁ የሚያምታቱ ገለጻዎችን ልብ በሚስብ ንግግሩ ሲያቀርብ ነበር:: ሰሞኑን ደግሞ ይህ ደረጀ የተባለው የጭንቀት ህመም አለብኝ እያለ የተከበረውን የአማራ ማህበረሰብና በዚያ ትውልድ ለህዝቡ የተሰዉትን እንዲዘልፍ የሚያበረታቱት እነዚህ ትኩረት ፈላጊ የሚዲያ ስነምግባር የሌላቸው ሚዲያ ተብዬዎች ለደረሰው ጥፋት ተጠያቂ ናቸው:: ይህን የሚከታተል ማህበር በሃገራችን ያለመኖሩ ህዝብ ማግኘት የሚገባውን ትክክለኛ ዜና ምክር መረጃ እንዳያገኝ ተዋጽ ማድረጉን የተረዱ ሁሉ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል::

 9. Birega – አንድ ሃገር ነው ያለን? ማንን ታሞኛለህ? የት ላይ ተቀምጠሽ ፈጣሪን ታሚያለሽ? አንተ የት ሆነህ ነው ይህን ምላሽ የጻፍከው? ያ ድሮ ቀርቶ አሁን ባህሩና ምድረበዳው የሌላው ሃገር ሃገራችን ሆኖአል። የሞተው ይሞታል፤ የቆመውም ቆሟል ለጊዜው። እውነቱ እሱ ነው። ደግሞስ አንድ ሃገር የምትለው በብሄር ተሸንሽና በክልል የታጠረችውን የሃበሻ ምድር ነው? የአፓርታይድ ክልሎች፤ ቋንቋየን ካልተናገርክ ከመኪና ውረድ የሚሉ ጉዶች የበቀሉባትን? ብቻ ለተመጻዳቂ ፓለቲከኞች መወሻከት የማጨበጥ ተስፋቸው ነው። እንዲሁ ሲላዝኑ፤ አብረው መከረው ሌላው ሲስያስገድሉ፤ አንጃ ግራንጃ ፈጥረው እርስ በእርስ ሲፋለሙ ወደማይመለሱበት ዓለም ተሻግረዋል። የዛሬው ሹኩታና ውካታም ካለፈው ቢከፋ እንጂ የተሻለ ነገር ተጨቆነ ለተባለው ህብረተሰብ አላስገኘም። ዛሬ በምድሪቱ ላይ ያለው እውነታ ገና መፈተሽና አፍርሶ መገንባት የሚጠይቅ ነው። ግን ማን ያን ይመለከታል? አስረሽ ምችው የወረፋ ፓለቲካ። የሞተንም የቆመንም ጭቃና ጥላሽት የሚቀባ የዘር ፓለቲካ። ይህ ነው በሃበሻዋ ምድር ለውጥ ማለት፡ የጠገበን አውርዶ የተራበን በሥፍራው የሚተካ። ለዚህ ስርዓት ነው ወገብህን ይዘህ የምትከራከረው ወይስ መሬት ላራሹ በማለት ህይወታቸውን ያሳለፉ እነዚያ የቀድሞዎቹ አብሪ ሃይሎች ዛሬ መሬቱ ሁሉ ለባለሃብት ሲባል ምን ይሰማቸው ይሆን ብለህ ራስህን ጠይቀሃል? የፎቅ መደርደር የሥልጣኔ ምልክት አይደለም። ትላንት የተገፉ ዛሬም ሲገፉና ሲያለቅሱ፤ ሲራቡ ቢመለከቱ ምን ያስቡ ይሆን? ኦሮማይ ይሉሃል ይሄ ነው። ሌላው ሁሉ ሰካራም የረገጠው ጣሳ ነው።

 10. ተስፋ ሀገር ወዳድ ዜጎችን መጨርገድህን ተው ተብለሀል ፊልምህ ተቃጥሏል ሀሳብ ካለህ እንደ መስፍን እራስህን ችለህ አርቲክል አውጣ በሰው ተደርበህ ስድብና ምክርህን ግን ተወን። የናንተ መንገድ ቢሰራ ዛሬ ላይ ሌላ ነበርን ።ተው አንተም እረፍት ውሰድ። ልዩ የስድብ ስልጠና እዚህ ጥቅም የለውም።

 11. Birega – አይ ሃገር ወዳድ፤ ሃገር አፍራሽ ብትል ይመረጥ ነበር። ግን ተጨፈኑና ላሳያችሁ በሚል የፓለቲካ ዘይቤ ልቡ ውልቅ ለሚል ሰው እውነት መች ትታየውና። እስቲ እናንተ ሃገር ወዳዶች ውደዷት። የአሻሮ ክምር ለቆሎ አይሆንም። እኔም ከእናንተ እብዶች ጋር አብሬ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ውሃ ስወቅጥ መኖሬ ያሳዝነኛል። ፈረሱም ሜዳውንም ለእናንተ ለሃገር ወዳዶች ትቻለሁ። ከአሁን በህዋላ ምክርም በለው ስድብ ከእኔ አይኖርም። ባለህበት ሰላም ሁን።

Leave a Reply

Your email address will not be published.