ብፁእ ቅዱስ ታዲዮስ ታንቶ! በፈሪሳውያን ዘመንም የሆነው ይኸው ነው! – በላይነህ አባተ

በላይነህ አባተ ([email protected])

የዛሬዋ ኢትዮጵያ የዘርፍ ፍጅት የፈጠሙን፣ ሕዝብን ለአስርተ ዓመታት ያሰቃዩን፣ ወህኒ በእሳት የጠበሱን ፈታ  የእድሜና የሙያ ባልጠጋውን ክቡር አቶ ታዲዮስ ታንቱን አስራ የምርድ ሲዖል የምታበላ አገር ናት፡፡ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ነፍሰ ገዳዮችና ሌባዎች የሚሾሙባት በማተባቸው በማድረቻቸው በድህነት የሚቆራመዱት እነ ታዲዎስ ታንቱ ወህኒ በእስተ እርጅና ከእነ ቅዱስ ጳውሎስ በከፋ ሁኔታ የሚሰቃዩባት ምድር ናት፡፡

“በማይጨበጥና በማይዳሰስ ነገር አላምንም” እያለ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ተረት የሚቆጥር ድስኩራም በሰላሳ ዓመታት ወስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኪያሄደውን የእውነት ተከታዮች መሰዋእትነት፣ የፈሪሳውያን ምሁራንን የነፈሰ ገዳዮች እግር ላሽነትና የጲላጦስ ዳኞችን ጭካኔ ይመልከት፡፡

ክቡር አቶ ታዲዮስ ታንቶ በፈሪሳውያን ከሳሽነትና  በጲላጦስ ዳኝነት እየተሳደዱና እየተንገላቱ ያሉ ብፁእ ቅዱስ አባት ናቸው፡፡ አቶ ታዲዎስ ብፁእ ቅዱስ ሲባሉ ከንፈርኑን እያሸራመመ የሚያሽሟጥጥ ከርሳምና እርኩስ ፈሪሳዊ አይጠፋም፡፡አቶ ታዲዎስ ታንቱ ለሚያምኑበት ታሪክ   እነ  ቅዱስ ጳውሎስ ለሚያምኑበት ወንጌል እንገታቸውን የሰጡትን ያህል አንገታቸው የሰጡ ቅዱስ አባት ናቸው፡፡ አቶ ታዲዎስ ታንቱ በመቶ ዓመት እንዴ በላንባ ዲና  ተፈልገው ተማይገኙት በለማተብ ሰዎች እንዱ ናቸው፡፡ ተዚህ ዘመን ከርሳም ፈሪሳዊ ምሁራን፣ ካህናት፣ ሼሆችና ፓስተሮች ጋር ሲነጣጠሩ አቶ ታዲዎስ ታንቱ ካባና ቆብ ያልደረቡ ብፁእ ቅዱስ አባት ናቸው፡፡

ስንቱ ካባ ደራቢ ጳጳስ፣ ስንቱ ጠምጣሚ ሼህ፣ ስንቱ አነብናቢ ፓስተር፣ ስንቱ ዲግሪ ጫኝ ፐሮፌስርና ዶክተር ለስጋው፣ ለገንዘብ፣ ለስልጣንና ለጉርሻ ተነፈሰ ገዳዮች ጀርባ ተሰልፎ ቂጡን እያማታ  በሚያረጠረጥበት ሰዓት አቶ ታዲዎስ የታሪክ መጻሕፍትን ተሽክመው የሚያምኑበት ታሪክ ያለመታከት የሚሰብኩ ሐዋርያ ናቸው፡፡ አቶ ታዲዎስ እንደ ሐዋሪያው ጳውሎስ፣ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስና ቡድሃ የስጋ ፍላጎታቸውን በእንዶድ አጥበው አስወግደው፤ ስልጣንን፣ ገንዘብንና መቅቡጥን ተጠይፈው፤ ተሚያምኑበት እውነት ጋር ቆመው ለማለፍ የተዘጋጁና የተመረጡ  ሰው ናቸው፡፡ ነቢይ በአገሩ አይከበር ሆኖ እኛ ባንገነባላቸውም አቶ ታዲዎስ ታንቱ ታሪክ ለጊዜው የማይታይ የምስክርነት ሐውልት ያቆመላቸው አባት ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ምንም ይሁን ምን ዲያስፖራው ቅሬታውን አይደብቅም፣

አምላክ ሆይ! እውንን እስር ቤት ማደር የነበረባቸው ሕዝብ ለምን ይሞታል አያሉ የታገሉት አቶ ታዲዎስ ታንቶ ወይስ ሰላሳ ዓመታት ሙሉ በጆሮ ጠቢነት፣ በካድሬነትና በታጣቂነት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲጨፈጭፉ የኖሩት አሳሪዎቻቸው? መለኮት ሆይ! እውንን ምሁራን የተባሉ ፈሪሳውያን መቆም የነበረባቸው ታሪክን ተሚመረምርቱ ፈላስፋ ታዲዎስ ታንቱ ጋር ወይስ በታሪክ ላይ ተሚፀዳዱት መሀይም አሳሪዎቻቸው ጋር!

ብፁእ ቅዱስ ታዲዎስ ታንቶ ሆይ! እኛ ፈሪሳውያን ከድተን ከጲላጦስ ዳኞችና ተአረመኔ አሳሪዎችዎ ጎን ብንቆም አይግረምዎ! በፈሪሳውያንም ዘመን የሆነው ይኸው ነው፡፡ የማታ ማታ አሸናፊው ግን እውነት ነው!

ይኸንን ሁሉ ግፍ የሚመለከተው መለኮት ለቅዱስ ጳውሎስና ጴጥሮስ የሰጠውን ጥናት ለእርስዎም ይስጥዎት!

 

መጀመርያ ሚያዝያ ሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ.. እንደገና ህራር ሁለት ሺህ አስራ አምስት ዓ..

9 Comments

 1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖትና ሥርዓት ወይም ፍትኃ ነገሥት (The Ethiopian Orthodox Tewhido Church Faith and Order) ከሊቀ ጳጳሳት በላይ ያለ ሹመት ብፁዕ ወቅዱስ ይባላል ይኸውም ቤተ ክርስቲያን በዕምነቷ ፀንታ እንድትኖር በበላይነት የሚመራ እንጂ እንዳለፉት የፖለቲካ ብፁዕ ወቅዱስ ሊቀ ጳጳስ መሆን ተገቢ እንዳልነበር እየታወቀ ዘሬ ደግሞ አቶውን ምንም አይነት ሥልጣነ ክህነት የሌለውን የፖለቲካ አቶውን አንዴ ክቡር አቶ ታዲዎስ ቀጥሎም አቶ ታዴውስ ከዚያም አቶ ታዲዎስ ብፁዕ ወቅዱስ ተብሎ መጻፉ ውሻ ወደ ሰርዶ አህያ ወደሊጥ የሚባለው ተረት በበላይነህ አባተ ተጀመረ ። እንዲያው አደራህን የማይሰማ ነገር የለምና ነገ ደግሞ ወይዘሮህን ሊቀ ጳጳስ ሆነች ፤ሥልጣነ ክህነትም ሰጠች፤ቀደሰችም ባረከችም ብለህ እንዳትነግረን አደራ ይሁንብህ።

 2. በጣም ግሩም ብለሀል ለኢትዮጵያ የቆመውን አማራ ካጸዱ በሗላ ወደእነ አቶ ታዲዮስ ተሻግረዋል ይህ የጥጋባቸው ልክ ነው። የሰው ቆዳ የገፈፉ ያኮላሹ የዘረፉ ትግሬዎች በነጻነት በሚኖሩበት አገር ሀቅን አበክረው ስለ ያዙ መታሰራቸው ያሳዝናል።

 3. አቶ አምባው በቀለ
  “ውሻ ወደ ሰርዶ አህያ ወደሊጥ” እንደሚባለው ሁሉ የወተት ዝንብ የሚባል ተረትም አለ፡፡ እርስዎን አይነት የዝንብ ወተት ተች እነሚኖር ገምተው ይመስለኛል ፀሀፊው ይኸንን ብለዋል “አቶ ታዲዎስ ብፁእ ቅዱስ ሲባሉ ከንፈርኑን እያሸራመመ የሚያሽሟጥጥ ከርሳምና እርኩስ ፈሪሳዊ አይጠፋም፡፡አቶ ታዲዎስ ታንቱ ለሚያምኑበት ታሪክ እነ ቅዱስ ጳውሎስ ለሚያምኑበት ወንጌል እንገታቸውን የሰጡትን ያህል አንገታቸው የሰጡ ቅዱስ አባት ናቸው፡፡”

  አርስቱን ብቻ አይተው እንደ ዝንብ ወተት ወደ መተቸቱ ሄደው የተንሳፈፉ ወይም የተንከረፈፉ ነው የሚመስለው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ጽሑፍ በእኔ እይታ የንፅፅር ጽሑፍ ይባላል፡፡ እስቲ ይጠየቁ አቶ አምባው? ለሕዝብና ለሚያምንበት እውነት ሲል እንደ አቶ ታንቱ መስዋትነት የከፈለ ከዘመኑ አንድ ጳጳስ መጥቀስ ይችላሉ? አንድ ፓትሪያሪክ ይጥቀሱ? ካባ መደረብና ጳጳስ መባል ብቻውን ቅዱስ ያሰኛል ተሚሉት ወገን ነዎትን?

  አቶ አምባው በቀለ ተየትኛው አምባ በቅለው ይህ አልታዮትና አልገባዎት አለ? ትረካን ታመጡት ዘንዳ! ተመጠምጠም መማር ይቅደም! ምንድንን ምንድን ታላሉት ገብቼ ልፈትፍት ይላል የሚባል ተረትም አለ፡፡

 4. አጅባው በቀለ አማርኛ ትችላለህ ተብሎ የተቀጠርክበት ስራ ስለሆነ አንተን እንኳን አንቀየመህም ተሳደብ የሚጽፉትን፡፡

 5. ግርማ ከበደ አምባውን አታውቀውም መሰል ለአንቱታም የደረሰ አይደለም የሚገርምህ ለአገልግሎቱ ብዙም የሚጠይቅ ሰው አይደለም ጥቂት ከከፈልከው እንደ ጌታቸው ረዳ በአንድ ቀን ጀምበር ማተቡን በጥሶ፣ጎሳውን ቀይሮ የሚኖር ስብእና የሌለው ሰው ነው። ልብ አላልከውም እንጅ ሀሳብን ማሳከር በሳይበር የተመደበበት የስራ ዘርፉ ነው። በረሀብ ሙት አትለውም ብትጨምቀው ጠብ የሚል ነገር የለውም እንዲህ እንዲህ እያለ ኑሮውን ኬልገፋ በረሀብ ይሞታል።

 6. አቶ ግርማ እንዳሉት የወተት ዝንብ ሳይሆን የዕርጎ ዝንብ ተብሎ ሲተረት ነው የማውቀው። በመሆኑን ብፁዕ ወቅዱስ ማለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሥርኣተ ቤተ ክርሥቲያን ወይም ህገ ቤተ ክርሥቲያን መሠረት ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለበላይ አስተዳድሪ በሊቀ ጳጳሳት ጉባኤ ተመርጦ የሚሰጥ ሹመት እንጂ ለአቶ ፖለቲከኞች የሚሰየም አይደለም። ጳጳስም ሆነ አቶ እውነት በመናገሩ ብፁዕ ወቅዱስ የሚባል ሹመት አይሰጠውም።ስለሆነም ከጸሐፊው እና አስተያይት ሰጭዎች በስተቀር ለአቶ ፖለቲከኞች ብፁዕ ወቅዱስ የሚል ስያሜ የተሰማም ሆነ የተጻፈ ያለ አይመስለኝም። ለንጽጽርም ጽሁፍነትም አያሟላም።እንዲሁም “ለሕዝብና ለሚያምንበት እውነት ሲል እንደ አቶ ታንቱ መስዋዕት የከፈለ ከዘመኑ አንድ ጳጳስ መጥቀስ ይቻላል? አንድ ፓትሪያሪክ ይጥቀሱ? ስለተባለው በመሠረቱ ዘመኑ የተባለው ከመቸ አመተ ምህረት ጀምሮ እንደሆነ ባይገባኝም እስከ እማውቀው ድረስ በአምሥት አመቱ የጣሊያን ወረራ ጊዜ ለእውነት ሲል የተሰው ብፁዕ ወቅዱስ ስይባሉ አቡነ ጰጥሮስ እና አቡነ ሚካኤል በደርግ አስተዳደር የተገደሉ ደግሞ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ርዕሳነ ሊቀ ጳጳሳት ፓትሪያሪክ ዘኢትዮጵያን ሲሆኑ የደርግ አስተዳረር ግድያውን ከፈጸመ በኃላ እስከአሁንም ድረስ ለእውነት ሲል መስዋዕትነት የከፈለ አንድም ፓትሪያሪክም ሆነ ጳጳስ የማውቀው የለም።እንዲሁም ከየትኛው አምባ (መንደር) በቅለው ነው ይህ ያልታየዎት ስለተባለው የበቀልኩበት ካሳስብዎት ከአንዷ እናቴ ኢትዮጵያ ነው። በተጨማሪ Berelea ለተባሉት በውነቱ ስምዎም ትንሽ ስለአስቸገረኝ የዕቃ መግፊያው ጋሪ ወይም ባሬላ መስለኝ ታዲያ እርስዎም አያውቁኝም እኔ አላውቅዎትም በመሆኑም ለአገልግሎቴ የሚክፍለኝ ማንም የለም የራሴን ለራሴ በወር የምከፍለው ለእርስዎ የአመት ገቢዎ ይሆናልና አይዘርፍጡ።

 7. Loughabable Ambaw Bekele

  The cadre is trying to teach Ato Abate about the Ethiopian Orthodox Church. Ambaw, please do not lay back on your back and pee up ward. It is will rain on your face, it is not going to go anywhere. Thank you.

 8. አቶ አምባው በቀለ
  በቅድሚያ ስለ ማብራሪያዎ አመሰግናለሁ፡፡ “ተዘመኑ” የሚመንለውን ባለማብራራቴ ደሞ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ የጠቅሷቸው ሰማእታት በዘመኑ የሚለውን አያጠቃልሉም፡፡ እርግጥ ነው ወደር የማይገኝላቸው ሳምዕታት፣ ቅዱሳን፣ ብፁእም ናቸው፡፡ ዳሩ ተዘመኑ ስል አቶ ታዲዎስ ታንቱ በሚታገሉበት ወቀት ማለቴ ነበር፡፡ ይህ ደሞ ከሰላሳ አመታት ብዙም አይበልጥም፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ደሞዝ የሚሰጧቸው ምዕመናን ሲያልቁና የሚቀድሱበት የክርስቶስ ቤት ሲቃጠልም እንደ አቶ ታዲዎስ ታንቱ የሚያምኑበትን ተናግረው ወይም በስራ ያስዩ አንድ ጳጳስ ወይም ፓትርያሪክ መጥቀስ ይቻላሉ? እንደሚመስለኝ እርስዎ የሚያዩት ግብርን ሳይሆን ካባና ቆብን ነው፡፡ ቅድስናም ሆነ ብፅዕነት ከግብር እንጅ ከልብስ አይገኝም፡፡ ይኸንን መቼም የሚያጡት አይመስለኝም፡፡ መጽሐፉ በሥራ እንጅ በልብስ ቅዱስ ትሆናለህ አላላም፡፡ ብሏል እንዴ? ከተሳሳትኩ ያርሙኝ!

 9. አቶ ግርማ ከበደ
  በማብራሪያዎ እያመሰገንኩ መግባባቱም የተፈጠረ ይመስለኛል።እንዲሁም ቅድስናም ሆነ ብፅዕነት ከግብር እና ከሥራ እንጂ ከልብስ አይገኝም ብለዋል። ጥርጥር በሌለበት እውነት ነው። እንዲያም በመጽሐፉ የተጻፈው ከባየን የለበሱ ሃሳትያን ይመጣሉና ተጠንቀቁ የሚል አንብቤአለሁ። በተጨማሪ ደርግ ሥልጣን ከያዘ ከሁለት ዓመት በኋላ ጀምሮ ቤተ ክርሥቲያን የምትገለገልበት ፍሬ ግብር ስታጣ፤ አገልጋይ ካህናት የሚበሉት ሲያጡ፤ቤተ ክርሥቲያን ስትዘረፍና ስትቃጠል ስለበደሉ አንድም ፓትሪያሪክም ሆነ ጳጳስ የተናገረ የለም። እንዲያውም ብፁዕ ወቅዱስ ሊቀ ጳጳስ ተብሎ ለመሾም በተፈጠረው አወዛጋቢ ችግር ቤት ክርሥቲያን የውስጥ ሲኖዶስ እና የውጭ ሲኖዶስ በመባባል ዲያስፖራው በሁለት እንዲከፋፈል ተደርጎ ነበር አሉ።ሌላው እርስዎ እንደመሰለዎት የሚያዩትት ግብርን ሳይሆን ካባና ቆብን ነው ስለአሉት ። ለማስታውስ የምፈልገው ቢኖር ቆብ መነኮሳት የሚደፉት ሲሆን ጳጳሳት የሚደፉት አስኬማ ነው። ካባንማ ሽልማት እየተባለ ማንም እየተጫነለት ነው።እንዲሁም አመተ ምህረቱ ጠፋኝ እንጂ የአክሱም ጽዮን ክብረ በዐል ላይ ደብረ ጽዮንስ በሊቀ ጳጳሱ ይመስለኛል ካባና ቆብ ተደፍቶለት አልነበረምን? በመሆኑም ካባ እና ቆብ በደፋ ሳይሆን የማየው በተግባር እና በሥራ በሚያሳዩ ነው።እያልኩ ያለሁት ብፁዕ ወቅዱስ የሚለው ሥራቱን እንደጠበቀ ይቆይ ነው። በዚሁ አጋጠሚ ለአቶ አበበ ለማስታውስ የበላይነህ አባተ ጽሁፍ ስለ ካድሬዎች አልመሰለኝ።ካድሬዎችን፤ የሚስብ የሚያነጋግርም አይደለም።እንደሚገባኝ ካድሬ ስለአንድ ድርጂት ወይም መንግሥት ትንሽ እውነት አያሌ ውሸት በመጨመር የሚያስተምር ነው ታዲይ የኔ ከድሬነት በየትኛው መደብከኝ? እንዲያው እንደ ጠንጋራ በቅሎ በተወላገደ የተውሶ ቋንቋ ከመንጀልፈፍ በአገርህ ቋንቋ አታጽፈውምን ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.