ይቅርታ መርሳት አይደለም – ጥሩነህ

ካርባ አመት በላይ የደረሰብንን ግፍ ይቅር ልንል እንችል ይሆናል፤ ያውም ደግ ልብ ካለን። ግፉን ግን ምን ጊዜም አንረሳውም። ለመርሳት መሞከርም የለብንም። ይልቁንም ተከታዩ ትውልድ ከትምህርት ቤት ጀምሮ እንዲማረው፣ እንዲያጤነው ማድረግ ታሪካዊ አላፊነት ነው። እርቀሰላም፣ ይቅርታ በመርህ ጥሩ ነው፣ የውደፊቱንም አብሮ ለመጓዝ ብቸኛ መንገድ ነው። መርሳትና ለማስረሳት መሞከር የነገውን ሌላ እልቂትና ግፍ ዛሬ ዘር መትከል ነው የሚሆነው። የቻላችሁ ይቅር በሉ ግን የሆነውን አትርሱ ትውልዱንም አስታውሱ፣ዛሬ የሆነውን መጠነ ሰፊ ግፍ ነገ እንዳይደገም ማድረግ የሚቻለው የሆነውን በማድበስበስ ሳይሆን እውነቱን አንጥሮ በማውጣት ትውልድ እንዳይደግመው ማስተማር ሲቻል ብች ነው። አይሁዳውያን በየቦታው የሆሎኮስት ሙዚየም የሚከፍቱትና የደረስባቸውን አበሳ ለአለም የሚያሳዩት የሰው ልጅ ከዚህ ተምሮ እንደገና እንዳይደግም ለማድርግ እንጂ እልቂቱን በማስታወስ የሚያገኙት የአእምሮ እፎይታ ስላለው አይደለም።

እውነትን ማድበስበስ የተጠናወተንን በሽታ አክመን የሚመጣውን ትውልድ እውነትን ማስጨበጥ ግዴታቸን መሆኑን ልንረዳ ይገባል። ታሪክን አለማወቅ፣ የተሰሩ ግፎችን አልማስታወስ  አስቀድመን እንዳንጠነቀቅባቸው ያጋልጣል።

ዛሬ የትግሬው ወሮ በላ በሃገራችን ላይ ያደረሰውን ግዙፍ ግፍ ወደጎን የምንልበት ምንም ምክንያት አይኖርም። የቅር ማለቱ እንዳለ ሆኑ፣ ይቅር ለማለት የሚችሉ። ይቅር በሉ ታሪኩን ግን አትርሱ ሌሎችም እንዲረሱ አትሞክሩ። አንዳንድ ሰዎች ከመንግስትም ጨምሮ በህዝባችን ላይ የውረደውን ምድራዊ ሲኦል ተውት አድርገን የውደፊቱን ብቻ እንመልከት ይሉናል። ይህ አደጋ አለው፣ ታሪክ የሌለው ዛሬንና ነገን የሚያመዛዝንበት ግንዛቤ አይኖረውም። ግፍና በደልን ደብቆ ሰላማዊና ጤነኛ መሆን አይቻልም። ባጭሩ የተቀበር ቦምብ ለምጭው ትውልድ ማቆየት ነው።

          እውነቱ ይነገር ከደረሰብን በደል አይበልጥም

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለዉጥ ሂደት እንጅ ዉጤት አይሆንም - ማላጂ

*ከወጣት እስከመነኩሴ የደፈረን እርጉም ቡድን፣

* ህጻናት ሽማግሌ ሳይል ህይወትን የቀጠፈ እርኩስ መንፈስ

* የቤት እንስሣትን የትኩስ ኢላም  ያደረገን አውሬ

* በበላበት ላይ የሚጽዳዳ ከከብት በታች ከብት ቡድን

* ከሊጥ ጀምሮ ስራውን በዘረፋ ያሰማራ ጠላት ዝርዝሩ ተቆጥሮ አያልቅም።

ወያኔ ያደረሰውን ስቃይ ልብ ያላችሁ፣ ደጎች ይቅር በሉት አሁንም የምደግመው ግን እውነታውን አታደባብሱት። ለቻለ ይቅር ማለት ጥሩ እንደሆነ አምናለሁ ከዚያ በላይ ደግሞ እውነታው በግልጽ እንዲወጣ እፈልጋለህ፣ ትውልድ እንዲማርበትና አይደገምም እንዲል እፈልጋለሁ።

የወያኔ መጀምሪያ ተግባር የኢትዮጵያን ህዝብ በተለይ የአማራንና የአፋርን ህዝብ ደግሞ በተለይ ክሽፍትነቱ ጅምሮ ያረደውን የወልቃይትንና ራያን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ ነው። የዘረፈውን መመለስ አንዱ ጸጸት ነው፣ ካሳ መክፈል ግዴታው መሆኑን ተረድቶ ከሰላሳ አመት በላይ የዘረፈውንና በውጭ ያስቀመጠውን የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሃብት መልሶ ለባለቤቱ መስጠት ነው።

በይቅርታ ስም ትውልድ የእውቅት ድሃ ሆኖ ለሌላ እልቂት አይዳረግ።ይቅርታና መርሳት አይምታቱ።

1 Comment

  1. The above-listed TPLF atrocities pale in comparison to the greatest systematic and structural crimes of the TPLF against the Amhara. The ethnic apartheid system that expropriated the Amhara of half their ancestral land, the inclusion of these lands into potentially “breakaway nations” , the deprivation of the democratic rights of the Amhara all over Ethiopia, and a constitutional system based on Amhara incrimination – these are the unforgivable crimes of the TPLF against the Amhara. As long as the Amhara live under the current political system, there is nothing to forgive and forget with respect to this structural and systematic order of oppression that the TPLF instituted and Abiy Ahmed only vows to preserve.

Leave a Reply

Your email address will not be published.