አዳነች አቤቤ በገነት ዘውዴ የዕብሪት መንገድ መሄድ

ብሃራቸውን ሳንቆጥር በርቱ ያልናቸው ከንቲባ ወ/ሮ ገነት ዘውዴን በሚያስንቅ የትምህርት ፖሊሲ ህጻናቱን ሊቀጡ ብቅ ብለዋል።

* ጥቂት የማይባል አዲስአበቤ ብሄር ሳይቆጥር የመጡበትን ድርጅት ሳይመትር ታከለ ኡማን – ታኬ ፣ አዳነች አበቤንም እንዲሁ እያቆላመጠ በርቱ ብሏል ጅምራቸው ይሳካ ዘንድ አይዟችሁ ሲል አበረታቷል።

* የአዲስአበባ ነዋሪ የኑሮ ውድነቱ ምሬቱን ጣሪያ ባደረሰበት ወቅት ከከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚጠብቀው የተቀናጀ የዋጋ ማረጋጊያ ስርአት ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፣ ፈር የለቀቀውን መንግስታዊ ሌብነት የማስታገሻ እርምጃዎች ነበር።

* አለመታደል ሆኖ የህዝብ ጥያቄ ሌላ የመንግስት ምላሽ እዚያ ግድም ሆኗል። የከተማው ህዝብ ሳይወያይበት ይሁንታ ሳይሰጥ የኦሮሚያ ክልል ባንዲራና ክልላዊ መዝሙር ለእነ አዳነች የቅድሚያ ቅድሚያ ሆኗል። ይሄ ጉዳይ ሊውል ሊያድር ህዝብ መክሮ ይሁንታ ሊሰጥበት የሚችል አጣዳፊ ያልሆነ አጃንዳ ነው።

* ዕድሜህ ይጠር ያለው የብልጽግና መንግስት የዛሬ አራት አመት በመቶ ሺዎች ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በአደባባይ ያነገሰው ከተሜ ላይ ዘመቻ ሊጀምር ዳር ዳር እያለ ያለ ይመስላል ። የብሄር ፖለቲካን ከዜግነት መብቶች ጋር ያስታርቃል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ብልጽግና ገና የትግራዩ ጦርነት ቁስል ሳይጠግ ፣ የኦሮሚያ ትርምስ መልክ ሳይይዝ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ያሉባት አዲስአበባ ላይ የብሄር ጦርነት ሊከፍት እየተቅበዘበዘ ነው።

* በፓርቲ ጉልበቱ ዕብሪት የወጠረው ህወሃት ከከተሜ ጋር ጸብ እንደማያዋጣው ያወቀው በምርጫ 97 ሸገር ላይ በዜሮ ከተሸኘ በኃላ ነው። የአዲስአበባን ነዋሪ እንኳን የሌቦች ስብስቡ ብልጽግና በድርጅታዊ ዲሲፒሊኑ የማይታማው ህወሃትም አንገት አላስደፋውም !

* አዳነች አቤቤ በገነት ዘውዴ የዕብሪት መንገድ መሄድ ከመረጡ ውጤቱን ብዙም ሳይቆዩ ማየታቸው አይቀርም። ህዝብን በጠላትነት ፈርጆ አንገቱን ሊያስደፋ የሞከረ የትኛውም ፖለቲከኛ ተሳክቶለት አያውቅም !

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቶ እውነቱ ብላታ የሥልጣን ዕድገት አገኙ

Habtamu As

2 Comments

  1. አዳነች አቤቤ፤ታከለ ኡማ፤ሽመልስ አብዲሳ፤ቀጀላ መርዳሳ፤ዳውድ ኢብሳ፤ዲማ ነገዎ፤ጁዋር መሃመድ፤ሌንጮ ለታ፤ባቲ፤አገኘሁ ተሻገር፤ደመቀ መኮንን፤ምናምን ጥሩነህ፤ከፍያለው ምናምን….. ልንፋታቸው ያቃተን የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው

  2. አዲስ አበቤ ዘምር የሚባለው ይህንን ጸያፍ ነገር ነው፡፡ «ስልጣንን መልሰን አገኘንሽ» ብሎ መዝሙር አለ? በነሱ አባባል አዲስ አበቤ ይህን እንዲዘምር ሲገደድ ህዝቡ እራስህን በራስህ ተኩስና ግደል እንደማለት ነው፡፡ አዲስ አበቤ ነፍጠኛ ነው፡፡ ነፍጠኛን የሚሳደብ መዝሙር ሊዘምር አይችልም፡፡ ነውር የሚባል የሌለባቸው፡፡ ምሁር ባይኖራቸው እንጅ ምሁር ቢኖራቸው መዝሙር እንዴት እንደሚጻፍ ያውቁ ነበር፡፡ እታች ያለውን የኦሮሞ ክልል መዝሙርና የኦሮሞ ክልል ተማሪዎች የሚዘምሩትን እዩና ፈረዱ!! እንኳን ለመዘመር ለማንበብ ያቅራል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.