የአማራ ሸኔ ይፈጠር እና የአማራ ሸኔ አለ፤ ለየቅል ነው፡፡ ሂሳብን በዚህ ዓነት መልኩ ኃላፊነት የሚሰማው መንግስት አያወራርድም

ሲና ዘ ሙሴ

የሚበላውን እና የሚለብሰውን ያጣ ደኻ   የተወለደበትን አገር የሚወድበትን ምክንያት ያጣልና የአገሩ  መንግሥት ቢበረታ ወይም  ቢጠፋ ግድ የለውም  …”

ሰውየው ለሚመራው ህዝብ አክብሮት የሌለው ከአፉ በቀር በጭራሽ ሰብአዊነት የሌለው አደገኛ ህልመኛ ሰው ነው

      የነጋድራስ /ህይወት ባይከዳኝ ዘላለማዊ መልዕክት እንሆ !

የሚበላውን እና የሚለብሰውን ያጣ ደኻ ፣ የተወለደበትን አገር የሚወድበትን ምክንያት ያጣልና የአገሩ መንግሥት ቢበረታ ወይም ቢጠፋ ግድ የለውም ። ስለ ሁም  መንግሥት  የሚጠቀምበት የአገሩ ሀብት በጥቂት ሰዎች እጅ ሲሰበሰብ አይደለም ።  የአገሩን ሀብት በመላው ህዝቡ ሲከፋፈለው ነው እንጂ ።  የሀብታምች   አኗኗር እና የሠራተኛው ደኻ አኗኗር አይነቱ እንበለ  መጠን የሚራራቅበት አገር መንግሥቱ ከጥፋት አፋፍ እንደደረሰ ያስረዳል ።  የኢትዮጵያን   ህዝብም ሁኔታ ብንመለከት እንደዚህ ያለ  ጥፋት እንዳይደርስ ያስፈራል ።

በአንድ ፊት ነግደው የሚያድሩት የውጪ  አገር ሰውች እና ለህዝቡ አንዳች  ጥቅም  ሳይሰሩ ድካሙን እየቀሙ አንዳንድ ሹማሙት ደኅና ደኅና ቤት እየሰሩ  እያጌጡ የተመቸ ኑሮ ሲኖሩ እናያለን ። በአንድ ፊትም የዕለት ምግብና የአንድ ዓመት ልብስ እናገኛለን ሲሉ  ብዙሺ ድኾች ወባና ችጋር ፈጅቷቸው ከድሬዋ አንስቶ እሥከ አዲስ አበባ ድረስ ከምድር ባቡር ጎን ለጎን አልፈው ፣ አልፈው ተቀብረዋል ። ግማሾቹም የተቀበሩበት መቃብር ጠሊቅ ሥላልሆነ ዱሮ አጥንታቸው ወጥቶ ከምድር ባቡር መንገድ  ግራ ና ቀኝ ተበታትኗል ።

ደግሞም ይኽን ያህል ሩቅ መንገድ መሄድ አያስፈልገንም ነገሩ ፣ በየከተማው ውሥጥ ይገለፃልና ። ያማረ የግንብ ቤትና ትንንሽ ጎዦ አጠገብ ለአጠገብ ተሠርተው እናያለን ። ባንዱ  ቤት ውሥጥ ትልቁ ጌታ ህዝቡ ደክሞ ያፈራውን ገንዘብ ሲያባክን በጎዦው ውስጥ የሚኖረው ደሃ የሚበላው ፣ የሚለብሰው ና የሚያበራው አጥቶ በረኻብና በብርድ ተጨብጦ  በኩበት ጪስ እና በእድፍ ውስጥ ይጨማለቃል ። በአንዱ ቤት ጌትነቱ እየበዛ ሲሄድ በአንዱቤት ድህነቱ እየሰፋ ይሄዳል ። የጎዦውን እና የአዲሱን ግንብ ቁመት ብናስተያይ በአገራችን ደሃ ና ጌታ እንዴት እየተራራቁ እንደሄዱ ይገልጹልናል ። ይኽ ግን ለመንግሥት ክፉ ምልክት ነው ። ይኽም ክፉ ነገር እየሰፋ እንዳይሄድ  መንግሥት ህዝቡን በሥራ እንዲያሠለጥን ያስፈልገዋል ። ህዝቡ በሥራ ከሠለጠነ ዘንድ ጌታና ደሃ እንደገና ይቃረባሉ ። በምክርና በኃይልም ተደጋግፈው የመንግሥታቸውን መሠረት ያጠናክራሉ ። ብርና ወረቅም ረዳቶች የለውጥ መሣሪያዎች የሚሆኑት በዚያን ጊዜ ነው ። ( መንግሥትና የህዝብ አሥተዳደር ተፃፈ በነጋድራስ ገ/ህይወት ባይከዳኝ ገፅ 119 እና 120 )  የብዕረኛው መልዕክትለም”    በቃላት መጫወትን  እንመርጣለን ? “ጉርጥ አደፈጠ ወይም ዘለለ ያው ጉርጥ ነው ። ”

ኦነግ ሸኔ  ኦነግ ነው ።  የአማራ ሸኔ   የተባለው  የአማራ  ፋኖ  መሆን ግን አይችልም ።  በግልፅ በአደባባይ ሰው የሚያርደውን የሤጣን ስብስብ ቡድን  ሥም ለአማራ መሥጠት በእውነቱ ሥርኤት የሌለው ሐጢያት ነው ። ጠቅላዩ በቅርብ ሰዎቻቸው አሉባልታ ብዙን ጊዜ ካልተሸወዱ በሥተቀር ይኽንን ተራ ሥህተት አይሳሳቱም ለማለት የሚያሥችል ጥርጣሬ ግን አለኝ ። ሙሉ ንግግራቸውን ያዳመጣችሁ እንደሆነ ኮንፊውዝድ የሆኑ ይመሥላል ።

በእርግጥ በግል  ጠቅላዩ ያላቸው ሁለት እግር ነው ። እናም በአንድ ጊዜ ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት አይችሉም ። ነገር ግን ሺ ዛፍ ላይ የሚወጡ የደህንነት ሰራተኞች አላቸው ። እውነቱን  ከእነሱ ቢሰሙ ይኽን መሠል ከእውነት የተጣረሰ ንግግር አይናገሩም ነበር ።

በእርግጥ ቅድሚያ የሚሰጠውን የሠንግሥት ሥራ ትቶ ነገ ሠላም ከሌለ ወደ ሚፈራርስ ፕሮጀክት ላይ ማተኮር ህፃንነት ነው ። ህፃናት በብልጭ ነገር እንደሚታለሊ ይታወቃል ። ዋናው እና ትልቁ ችግር መቀመጫ ላይ የተሳካ እሾህ ነው ። እርሱን ሳይነቅሉ የ20 እና የ40 ቢሎን ለሠገንባት መነሳት ትርፉ ለቻይና ሀብታሞች ና በቋንቋ ለተቧደኑ ሌቦች ነው ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እሰይ! ድል ለወጣቱ ትውልድ!!! (ከሮበሌ አባቢያ)

ጥቅላዩ አሥተዋይ እና ከሥልጣን ሥግብግብነት የፀዳ አእምሮ ያላቸው መሆኑንን የምናረጋግጥበት 11 ኛው ሰዓት ላይ ደርሰናል ።  ከአጠገባቸው ያሉትን የቋተቧዳኞች ፣ ወንዜኘዎችን እየሰሙ ከሄዱ ግን በቅርቡ ብልፅግና ተረት ይሆናል ። ኢትዮጵያ ግን በድል ትቀጥላለች ። …

ዘረኝነት ያበዱ ሰዎች በቅርቡ ይጠፋሉ ። የደሃው ህዝብ ትዕግሥት ተሟጧል ። ሰው መሆናቸውን የካዱ ሰዎችን ተሸክሞ አመታትን አይጓዝም። የሥልጣን አረቄ ጭንቅላታው ላይ ወጥቶ በሥካር ህዝብን የሚያሥተዳድሩ ሰዎችን ይዤ ህዝብን እንደ ህዝብ ፈቃድ ሊያሥተዳድር የቻለ መንግሥት እንደሌለም ሳይረፍድባቸው ከታሪክ ይማሩ  ።

የሥልጣን አረቄ ናላቸውን ባዞረው ጨካኝ እና ግፈኜ  ፣ በለሥልጣናት ላይ  ፣ የፈጣሪ ቁጣ በየቤተሰባቸው ላይ ጭምር ቁጣውን መውረዱ አይቀርም ።  እሥከዛሬም የቤተሰቦቻቸው እና የኃይማኖት ሰዎች   የዘወትር የልብ ፀሎት እንዲሁም የልጆቻቸው ፀሎት ጠብቋቸው   ( ጠቅላይ ማኒሥቴሩንም ጨምሮ ) ይኸው አገር እየመሩ ነው ።

ዛሬ እና አሁን ግን ጠቅላዩ  አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ፤ ወደው ይሁን ተገደው ፤ ግልፅ ባልሆነልን ሁኔታ የተወሰነ  Conspiracy እያስተዋልንባቸው ነው ።   የሚያነሱት ምሳሌ እና ምሣሌያዊ አነጋገር ከአምክንዮ ውጪ የሆነ ፣ ሣይንሣዊ እና ፖለቲካዊ ጭብጥም የሌለው የህፃን ማባበያ የመሠለ ሆ፣ ግራ አጋቢ ሆኖብናል ።

አሁን ማን የእያንዳንዱ ግለሰብ ፣ የእምነት ፣ የባህል ( ቋንቋንም ይጨምራል ) አይከበር አለ ? እንዴ ! በትልልቅ የኢትዮጵያ  ከተሞች  ( መቀሌም ከወያኔ ጥጋብ በፊት እኮ ከመላው ኢትዮጵያ በእንጀራ  አሥገዳጅነት  የመጡ ሰዎች ፣  አንድ ባህል ያላቸውን ያህል ተከባብረው ፣  ተፋቅረው ፣  አንድ  ላይ መዕድ ቆርሰው ሲኖሩ እኮ ነው የምናየው ። ህዝብ እኮ አልተለያየም ።

ዛሬ የወጣቶቹ መፋቀር የሚያሥቀና ነው ። ፖለቲከኞች ግን በአጥር ውሥጥ ሥላሉ የህዝቡን ፍቅር አያሥተውሉም ። እታች በቀበሌ ደረጃ ካሉት አመራሮችም ጋር ሆዳሙ እና መድረሻ ቢሱ እንጂ የየከተሞቹ ኗሪዎች ተሰብስበው አያውቁም ። በወያኔ ጊዜም ይኸው ነበር ።… እናም ይህንን እውነት አብይ ካላወቅህ እንደ ጉተማ ቡዳህ አንድ ቀን መናኛ ልብስ ለብሰህ ፣ እራሥህን ለውጠህ ከቤተመንግሥትህ ከአንድ ታማኝ ወታደር ጋ ውጣና የህዝቡን እውነት ተረዳ ።  እንደጉተማ ቡዳህ ቤተመንግሥት በቃኝ ። እንደማትል ግን እ ነዘባለሁ ። ሆኖም  ወቅታዊውን እውነት እና የፖለቲካውን ሸፍጥ በቅጡ ታውቃለህ  ። …

ውድ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ፤ የወያኔ ህገ መንግሥት  የፌደራል እና የክልልን አወቃቀር ከቋንቋ አኳያ እኮ ነው ፤  የሚያየው ።  እንዲሁም  እያንዳንዱ  ክልል  እንደ  አንድ ሉአላዊ አገር ህገ መንግሥታዊ መብቴ ነው ፣ ብሎ   ቋንቋውን እና የቋንቋውን የጎሣ  አባል ብቻ በክልሉ  እንደ ዜጋ ሌላውን  ጎሣ ና  የማህበረሰብ  ክፍል   መጤ አድርጎ ነው የሚቆጥረው።  ዜጎች በዚህ ህገመንግሥት እሥከተመሩ ድረስ ፣ መላዋ ኢትዮጵያ አገራቸው በተግባር አገራቸው እንዴት መሆን ትችላለች  ?

ምድር ላይ ያለው የዛሬው ዕውነት

ዛሬ ሰዎች በፖለቲካ አሥተሣሠባቸው ፣ ” ለምን ለእኔ ቋንቋ አልወገንክም ? ለምን ሰው ነኝ በማለት ከዜጎች እውነት ጋር አበርክ ? …ከሰዎች  ማህበራዊ ህይወት እና ኑሮ ጋርወገንክ ? ዜጎች ሰው እንጂ መግባቢያ ቋንቋ አይደሉም በማለት በሚዲያ  ተሟገትክ ? “ እየተባሉ እየታሰሩ ያሉት በወያኔያዊው አሥተሣሠብ የተቃኙ የፖሊሥ ሹመኞችና የህግ ሰዎች በብልፅግና (…) ውሥጥ ሥላሉ ነው ። ይኽ ቆሞ ቀር አሥተሣሠብ ነው ። አሥተሣሠቡሞ የመነጨው ፖለቲካው  ካሥገኘው ጥቅም አንፃር ነው ። ፖለቲካው ዛሬም ፣ ኦህዴዳዊ ፣ ብአዴንናዊ እና የደቡብ ህዝቦች ነው።  ከፖርቲነት የተቀነሰው  ህውሃት ብቻ ነው ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አማራ፦ ህልውናህ ያለው በአንተው መዳፍ ውስጥ ነው (እውነቱ ቢሆን)

ከዚህ እውነት አንፃር ፣ ብልፅግና ፖርቲ አዲስ አይደለም ። በጥገናዊ ለውጥ ሰበብ ፣ የመወሰን ሥልጣን የሌላቸውን አጋር  የነበሩትን ክልሎች ፣ በጥደፊያ አባል አድርጎ የአገሪቱን የአምሥት ዓመት ሥልጣን የያዘ ጠንካራ መሠረት የሌለው በአድር ባይ ካድሬዎች የተሞላ ቁጥር 2 ኢህአዴግ ነው ፤ ብልፅግና ተብሎ በድራማዊ መንገድ የተፈጠረው ። ይኽ የነቶሎ ቶሎ ቤት አሠራርን የሚያመለክት ፤ ዘመናዊነትን ያልተከተለ የፖርቲ አደረጃጀት መንገድ የዛሬው ጦስ ጥንቡሣሥ አዋላጅ ነው ። …

አብይ መራሹ መንግሥት  በድንገት ቢንኮታኮት  ድንገት  ሥልጣን ለያዘው ባለጠመንጃ   የሚያሸረግዱ ናቸው የብልፅግና አባላት ። አብዛኞቹ  ሆድ እንጂ መርህ የላቸውም ። የፖርቲውን ራዕይ ፣ ዓላማና ግብ ፈፅሞ የማያውቁ ፣ ቢያውቁም በተግባር የተለያዩ ናቸው ።   ለኃይለኛው ለመሰለፍ አይናቸውን የማያሹ ፤ ኮሽ ሲል ወደ ውጪ ለመፈርጠጥ ሻንጣ የሚሸክፉ ቦቅባቆች ናቸው ። ዕድሜ ለኢትዮጵያ ልጅ  ፣ ለመከላከያ ና ለፋኖ ይበሉ ። ከሞት አፋፍ ነው የመለሣቸው ። ዛሬም ከነዚህ ገሚሶቹ ፣ በሱስ የተበከሉ ህሊና ቢሶች ናቸው ።  ቁጥራቸው የትየለሌ የሆነ ህሊና ቢስ ፣ የበሰበሱ  አባላትን  ይዞ በሥመ ብልፅግና አገርን ወደ ብልፅግና መውሰድ እንዴት ይቻላል ?

ደግሞስ ፣ ህገ መንግሥቱ የፌደራል እና የክልልን አወቃቀር ከቋንቋ አኳያ  እያየ እንዴት አሥተማማኝ ሰላም በአገር ሊመጣ ይችላል ? ዛሬ እና አሁን ፣ እያንዳንዱ ክልል እንደ አንድ ሉአላዊ አገር ህገ መንግሥት ብሎ  ቋንቋውን እና የቋንቋውን የጎሣ አባል ብቻ በክልሉ እንደ ዜጋ ሌላውን ጎሣ ና የማህበረሰብ ክፍል መጤ አድርጎ ነው የሚመለከተው ። ዜጎች በዚህ ከፋፋይ የአፖርታይድ  ህገመንግሥት እሥከተመሩ ጊዜ  ድረስ ፣ መላዋ ኢትዮጵያ አገራቸው አትሆንም ።

አንድ ኦሮሞ ትግራይ ሄዶ ኑሮውን መመሥረት ፤ ቤተሰብ እና ሀብት ማፍራት  ቢችልና እርሱ ዕድሜ ጠግቦ ቢሞት ና የልጅ ልጆቹ በመቀሌ የቱንም ያህል ቢበዙ  በትግራይ ህገ ንግሥት መሰረት የመምረጥ እንጂ የመመረጥ መብት አይኖራቸውም ። በተገላቢጦሽ ትግሬውም ኦሮምኛን  አርሲ በመወለዱ አቀላጥፎ ቢናገርም በትግሬነቱ ምክንያት ” ጨፌ ”  ወይም ምክር ቤት ለመግባት አይችልም ። በተቀሩትም ክልልች   እንዲሁ ነው ። …

እንዲህ አይነቱ ኢ ፍትሐዊ  ህገ መንግሥት በመላው ዓለም የለም ። የዓለም የፊደረሽን ሥርዓት  ፣” ፌደረሽኖች ፣በማዕከላዊው መንግስት የማይተገበሩ ፣ ውሥጣዊ የአሥተዳደር ስልጣኖች  ይጠበቁላቸዋል ። ከዚህ አንፃር ፣ ክልሎች በተወሰነ መልኩ ሉዓላዊ ናቸው ። ነገር ግን ፌዴሬሽኑ የነፃ ክልሎች  ጥምረት ብቻ አይደለም። የፌደራሉ ክልሎች የውጭ ፖሊሲን በተመለከተ ስልጣን  የላቸውም ። የጦር ኃይል ሊመሠረቱ አይችሉም ። የፀጥታ አሥከባሪ ተቋም ቢኖራቸውም የሚቀጠሩት ከህዝቡ ውሥጥ ያለአድሎ መሆን ይኖረበታል ። በከተሞች የሚኖሩ ዜጎች በዜግነታቸው እንጂ በቋንቋቸው እየተመዘኑ እየተለዩ ፣ ፖሊሥ እና ወታደር መሆን የለባቸውም ። ” ቢልም  ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ፣

ፖሊሥ ብቻ ሣይሆን መምህራን ፣  ኃኪሞች ፣ የሂሣብ ሠራተኞች ፣ ወዘተ ። በየክልሎቹ በቋንቋ መሥፈርት እየተቀጠሩ እንጂ ዜጎች በሰብዓዊ እና ተፈጥሯዊ መብታቸው ታይተው  የኢትዮጵያን ገበታ በጋራ ተቋዳሽ አልተደረጉም ።  የህ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን የአፖርታይድ ሥርዓት ነው ። ( እንዴት ለአፍሪካዊያን ነፃነት ፣ አፖርታይድን ለመገርሰሰ ግንባር ቀደም ተፋላሚ የሆነች ፣ በባርነት ያልተገዛች አገር ዛሬ  መንግሥቷ የአፖርታይድን አገዛዝ በየክልሉ ሁሉ እንዲተገበር እንዴት ያደርጋል  ?   ከዚህ በከፋ መልኩ ደግሞ ህሊናቸውን ለነዋይ በሸጡ ፣    በጥቂት የህወሓት አባላት ጠብ አጫሪነት እርስ በራሣችን ተገዳድለን ሥናበቃ ፣ ትላንት ነፃ እንዲወጡ በታገልንላቸው ውንድም የአፍሪካ አገራት መሪ ልጆች ሥንሸመገል ማፈር ነበረብን ።ተዋርደናል ። ወያኔዎች ከከፍታችን አውርደውናል ። የቁሥ እንጂ የሰው ፍቅር ሥለሌላቸው ኢትዮጵያን ክደዋል ። ታላቅነታቸውን በሆዳቸው ለውጠዋል ። የኢትዮጵያን እድገት በ15 እና 20 ዓመት ወደኋላ ጎትተዋል ። ኢኮኖሚዋ እንዲኮታኮት አድርገዋል ። )

ተጨማሪ ያንብቡ:  የብሔር ጽንፈኝነት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር

ይኽ  ዜጎችን በቋንቋ የማበላለጥ ከእምነት የሚያጣላ ( ከፈጣሪ የሚያርቅ ) ሥርዓት  ሂትለራዊ እና ሞሶሎኒያዊ  ነው ። በዚህ ሥርዓት ከቀጠልን ኢትዮጵያን አጥፍተን 17  አገር የማንሆንበት አንዳች መንገድ አይኖርም ።

እንበልና የአማራ ክልል ዘርን መሠረት በማድረግ አማርኛ የሚናገሩ ሆኖም ከኦሮሞ ማህበረሰብ የተገኙ ባለሙያዎች ሁሉ  ሥራቸውን ለቀው ወደ ክልላቸው ይሂዱ ቢል ፣ የሚ ጠረውን ትርምሥ  አስባችሁታል ?  አገርን ወደ መበታተን የሚያመራ አይደለምን ?

ኦሮሚያ በተሰኘው ክልል አመራሮች የኽ አገርን የማፍረስ ድርጊት   በህቡ እየተከወነ ነው ።   ይሄ ድርጊት ” አሳፋሪ ነው ።  ” ብለን የምናልፈው አይደለም ። ” እጅግ አሥፈሪ እና ደም አፈሳሽ ነው ። ” ሥለሚሆን ከወዲሁ ልንገታው ወይም ልንቀለብሰው በጀግንነት መነሳት አለብን  ። ቅኝ ገዢው  ሞሶሎኒ እንኳ በአምሥት ዓመት ቆይታው  የዛሬውን አይነት አሥጠሊ የከፋፍለህ ግዛ እና የዘረፋ  መንገድ አልተከተለም ።

ከሞሶሊኒ የባሰ የዘረኝነት እና የዘረፋ መንገድን  በመከተል ፣ በአማርኛ እያወሩ አማርኛን መጥላት ፤ በበኩሌ በታሪክ ተፅፎ ፣ የፋሺሥቱ ኢጣሊያ ሥራ ነው ተብሎ አላነበብኩም ። የዛሬው የዘር ፖለቲካ  የጤነኝነት ነው አልልም ። የቁሥ ሠቀቀን እና የሥግብግብነት ነው ።  ” ሌላው ዜጋ አራት እግሩን ይብላ እኔ እና መሰሎቼ ግን በጥጋብ ሰማይን በእርግጫ እያልን እሥከህልፈታችን እንኑር ። ”   የማለት የጅል  አሥተሣሠብ የወለደው የህሊና ቢሶች የውድቀት መንገድም ነው   ።

ሰው ህሊና ቢሥ ሲሆን የሤጣን ቁራኛ ይሆናል ። እንደዚህ ያለው ሰው ተሰባስቦ ፖርቲ ከመሠረተና መንግሥት ከሆነ ደግሞ ፣ አዲዮስ ! … እጅግ ዘግናኝ ተግባራትን ከመፈፀም ወደ ኋላ አይልም ። ምክንያቱም እርሱ ባለመማሩ ዕውቀት ሥለሌለው በዙሪያው የሚያሰልፋቸው በዕወቀት ዕጦት ማመዛዘን የማይችሉ ሰዎችን እና በተለያዩ ጎጂ ሱሶች የተዘፈቁ ግለሰቦችን በመሆኑ ፣ ቆሜለታለሁ ለሚለው ህዝብ እልቂት ነው ጠብ የሚልለት   ።

( ዕውቀት ማለት ባችለር ፣ ማሥተርሥ ፣ እና ፒኤች ዲ በአንድ የዕውቀት ዘርፍ ማገኘት ማለት አይደለም ። ዕውቀት ከዚህ ባሻገር ነው ። ሰው ራሱን ፣ ማንነቱን ፣ ተፈጥሮውን ሰብዓዊ መብቱን በቅጡ የሚገነዘብበት እና   አምሳያውንም  እንደእራሱ የሚያይበትን አመዛዛኝ ህሊና መጎናፀፊያ መሣሪያ ነው ። አብዛኛዎችን በጎ ዕውቀቶች ሰው ከህይወት ዩኒቨርስቲ ደረጃ በደረጃ ይቀስማል ። ጎጂዎችንም እንዲሁ ።

ሰው ልጅ በዓለም ላይ ሲኖር በጎ ና መጥፎ ትምህርቶችን በተለያየ መንገድ በመማሩ አዋቂ አይሰኝም ። አዋቂ ሰው ሰው መሆኑንን በቅጡ የተገነዘበ እና ለእርሱ የሚያሥፈልገው  መልካም ነገር ሁሉ ለአምሳያው ያሥፈልገዋል ብሎ ከልቡ የሚያምን ነው ። … ሰው የሚባለውም ይኽ ሰው ነው ።)

ትላንት ከ80 ዓመት በፊት ነጋድራስ ገ ህይወት ባይከዳኝ ሰው የሚመራበትን መንገድ ከኢኮኖሚና ከአሥተዳደር አንፃር መፃፋቸውን ከላይ ገልጫለሁ ። ይኽንን ሥለመንግሥትና  ህዝብ አሥተዳደር የፃፉትን መፅሐፍ   እንኳ አንብበው ጠቃሚ ፍሬዎቹን የለቀሙ   ግለሰቦች በመንግሥት ሥልጣን ላይ በብዛት ይቅርና በጥቂቱ እንኳን የሉም ። በአማካሪነት ደረጃ ግን አንድ ሁለት አሉ ።

ወያኔ እንደ ዕቃ፣ዕቃ ጫወታ “ፖርቲ” እና ” ዴድ “በማድረግ ሥልጣን ሥለሰጠቻቸው ራሳቸውን እንደ አዋቂ እና እና እንደ መኮንንት ቆጥረው  የወጡበትን ማህበረሰብ ቁልቁል ማየት   የጀመሩ ግን መሃት ናቸው  ። …

 

3 Comments

  1. Most of your points of view and points of argument tell the very hard reality on the ground ! Good !

    But the way you tried to describe and characterize the prime minister makes the whole of your points of argument very weak if not badly paradoxical ! To describe a guy whose political personality is full of deception, dishonesty , hypocrisy, conspiracy , lie , arrogance, narcissism, immorality , and of course cruelty, … as someone who does wrong things knowingly or unknowingly and also because of his bad advisors is terribly misleading if not politically nonsensical!!!

  2. ጠ/ሚሩ ተናግሮ የማይጠግብ፤ ሁሉን አውቃለሁ የሚል፤ በስማ በለው እንጂ በመረጃ የማይመራ ለመሆኑ በየጊዜው ከሚደሰኩራቸው ንግግሮች መረዳት ይቻላል። የሚገርመው አፉን በከፈተ ቁጥር እያዋዛ ጣል የሚያደርጋቸው ከፋፋይና ከንቱ ውዳሴዎች አንድን ደስ አሰኝቶ ሌላውን ለማስከፋት በእቅድ የሚሰራበት ይመስላል። በምድሪቱ ሙሰኝነትን መዋጋት በብልጽግና (በድህነት) ፓርቲ አልተጀመረም። ደርግም ከበሮ መቶበታል፤ ወያኔ ከአዲስ አበባ መሃል ከተማ ብዙ ሺህ ኩንታል ቡና ሲሰረቅ እጅ እንቆርጣለን ብሎ ዝቶ ነበር። ያለፈውም ሆነ የአሁኑ የውስልትና ዛቻ ነው። የተደረገ የሚደረግም ነገር የለም። ጉቦውና ስርቆቱ ይቀጥላል። የሚያሳዝነው ጠ/ሚሩ የሰረቃችሁም በዛው ሃብት ዳቦ ቤት ክፈቱልን ማለቱ ነው። ይህችን ይወዳል። ለየትኞቹ ሌቦች ነው ይህ ሰርቆ በዳቦ ቤት ምህረት ማግኘት? ለወያኔ ዘራፊዎች ወይስ አሁን በኦሮሞ ህዝብ ስም በየስፍራው ተሰግስገው ህዝብን የሚግጡትን የቀን ጅቦች? ግን ሰውየው ተማቶበታል። መካሪ ቢኖረው ባይናገር ይመረጣል። በምን ሂሳብ ነው የአንዲት ሃገር መሪ እንዲህ ያለ ቃል የሚናገረው?
    ቀጥሎም በንግግሩ ነገር ሲያደፈርስ የአማራና የኦነግ ሸኔ። እነማን ይሆኑ? መቼ ነው ይህ ጥምረትም ሆን ስም ለአማራው የተሰጠው? ግን አበው እንደሚሉት አህያውን ፈርተው ዳውላውን እንዲሉ ነውና ከኦነጎች ጋር ላለመላተም ተለጣፊ ስም መፈለግ አስፈላጊ ስለሆነ ነው እንዲህ ነገር የሚያምታታው። እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም። አንገታችን ይቆረጣል እንጂ እያለ እንዳልደነፋ አሁን ደግሞ ይህች ሃገር እንዳትፍረከረክ እሰጋለሁ ይለናል። ትፍረክረካ፡ ኑሯም አላማረባትም። ግን አትራፊ አይኖርም። መጫረስ፤ መገዳደል፤ መወነጃጀል፤ ረሃብና ሰቆቃ ነው የምናተርፈው። እንዲህ በተሳከረ የፓለቲካ አስረሽ ምቺው እሰጣ ገባ እንዴት ነው ሃገር ገንብቶ ተተኪ ትውልድ ማፍራት የሚቻለው? ጠ/ሚሩ ያው ወያኔ ወልዶ ያሳደገው በወያኔ የተንኮል ፓለቲካ የተቃመሰ በመሆኑ የፓለቲካ ሸሩን ተክኖበታል። ግን ለምን ይሆን ከዘመን ዘመን ምድሪቱ የክፋት ጥግ የወጡ መሪዎች ብቻ የሚያተራምሷት? ፊውዳሉ ሲሄድ፤ አውሬው ደርግ ተተካ፤ ኦ ይህም አለፈ ሲባል በዘርና በቋንቋ የተደራጀው የወያኔ ግፍ ምድሪቱን አስረገዳት፤ እስቲ አሁን በቃ በለን ስንል ቋንጭራ ይዞ ነፍሰ ጡር ሴትን ሆዷን የሚዘነጥል፤ ከሃገሬ ውጡልኝ የሚል የኦሮሞ ስብስብን ላከብን። አሁን በእውነት ፈጣሪ አለ? ወይስ ከላይ ሆኖ እያየ ይስቃል በጅልነታችን? አላውቅም። እንደ ሃበሻ ምድር ያለ ከጊዜ ወደ ጊዜ የማይሻለው ህዝብና ምድር የትም የለም።
    እውቁ ደራሲ አቤ ጉበኛ – አቤ ሰፊ ህዝብ ማለት ምን ማለት ነው ተብሎ ሲጠየቅ “ሞቶ የማያልቅ ማለት ነው” ነበር ያለው። ጠ/ሚሩ ሃገር ያቆመ እየመሰለው በየጊዜው የሚናገራቸው ንግግሮች ከፋፋይና ግርግር ፈጣሪዎች እየሆኑ ነው። ለምሳሌ ያህል “አዲስ አበባ ውስጥ ኦሮሞ ጠሎች አሉ” ሰውን እንዲጠላ የሚያደርገው ተግባሩ እንጂ ዘሩ አይደለም። ወያኔን እንዲጠላ ያደረገው ድርቡሻዊ ሥራው ነው። ደርግን እንዲጠላ ያደረገው ገድሎ መሰንበት መሻቱ ነው። የፊዳሉን መንግስትም መንኮታኮት እልፎች እየተራቡ ጥቂቶች የሚፈነጩባት ምድር በመሆኗ ነው። ጥያቄው የዛሬው ካለፈው የሚለየው የቱ ላይ ነው? የኦሮሞን ባንዲራና መዝሙር በግድ ዘምር መባሉ ከጣሊያን ወረራና በግድ ጣሊያንኛ ልመድ ወይም የጣሊያን ሰንደቅ መዝሙር ዘምር ከሚለው ምን ለየው? ፓለቲከኞች ልበ ቢሶች ናቸው። ይህ የእኛው ሃገር የዘር ፓለቲካ ቢይዙት የማይጨበጥ ንፋስ ነው። ለጊዜው ሰውን አፋጅቶና የሌለ ተስፋ አስታቅፎ በምትኩ ደግሞ ሌላ ገፊና ገፍታሪ ይመጣል። በታሪክ ያየነው ይህን ነው። ጠ/ሚሩ ቃሉ አጭር፤ የሚናገረውን በጽሁፍ አዘጋጅቶ ቢደሰኩር ይሻላል። ዝም ብሎ አፍ እንዳመጣ መለፍለፍ ከአፍ የወጣ አፋፍ ነውና ጥንቃቄ ያስፈልጋል። የአማራ ሸኔ የለም። የኦሮሞ እንጂ! እያማቱ መኖር ይቅር።
    በመጨረሻም ዮሃንስ ፍሥሃ – ናፋቂ ዜማዎች ላይ ካሳተመው አንድ ግጥም አልፍ አለፍ ብዬ ጥቂት ስንኞች ልዋስና ነገሬን ልቋጭ።
    ህልም አይቼ ነበር መሃል አዲሳባ
    የጎመን ድስት ወቶ የገንፎ ሲገባ
    ለጎመን ድስት ቀብር አፈር እየማስኩኝ
    ቀበርኩት ስል ከሥር ወጣሁኝ ስል ከላይ
    እኚህን ጅምር ህልሞች በቅዥት ለውሶ
    ከማረፊያው ጣለኝ ከህልሜ ቀስቅሶ
    የሃበሻው የፓለቲካ ተንኮል ይገታ ይሆን? ወይስ ዝንተ ዓለም አንድ በአንድ ሌላው በሌላው እያሳበበ ትውልድ እያስጨረስን፤ ያለፈውን እየደገምን፤ ካለፈውም የከፋና የከረፋ ነገር እየፈጸምን በደምበር ገተር ፓለቲካ ውስጥ ተዘፍቀን እንኖር ይሆን? በቃኝ!

  3. ለሃገርና ለሰፊው ህዝብ ጥቅም በቅንነትና በአንድ ልብ እስካልተቆመ ድረስ ሃገሪቱ እንዲህ ባሉ እውቀትም፤ ቅንነትም፤ ሰውነትም በጎደላቸው ሃይሎች ህልውናዋ አደጋ ውስጥ መግባቱ እማይቀር ነው፡፡
    የሰውን ስብእና በውጫዊ ተክለሰውነትና በአፍ ሽንገላ መዝኖ የሚቀበል ህዝብ ከዚህ መማር ካልቻለ ነገም ሌላ አፈ-ቀላጤ የመንግስትን ቦታ ተቆጣጥሮ ሃገርንና ህዝብን መጫዎቻ የማያደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.