ሁሉም በአንድ አላማ ይታገል – እውጡት ከፓርላማ (አቡሽ) + ወንበርሽ (ቴዲ ዮ)

እርግጥ ነው የደፋር አርቲስቶቹ መልእክት ያለውን የገማ የገለማ ዃላ ቀር የጎሰኞች ስርዓትና የሚመራበትን አገር አፍራሽ ህዝብ አጫራሽ የጥፋት ሰነድ ይወገድና አገራችን በአንድነትና በነጻነት ህዝብም በእኩልነትና በህብረት ይኑር ነው እነዚህ ደፋሮች በአገር ውስጥ ለዚያውም  በአዲስ አበባ ተቃምጠው ይህንን የመሰለ ጀግንነትን የተላበሰ ትግል በሙያቸው ሲያደርጉ ምሁር ተብዬው አድር ባይ በሽህ ኪሎሜትር እርቀት ላይ ሆኖ ሥርዓቱን ለማዳን በኤኮኖሚ፣በፖለቲካ፣አማካሪነትና በገንዘብ ተባባሪ መሆኑ ያሳዝናል።የትኛው ምሁር እንደሆነ ያዬንበት ጊዜ ነው።ህዝባዊ ትግሉ ተሳክቶ ሥርዓቱ ሲገረሰስ የስርዓቱ አዘጥዛጭ ጎራ ምን ይውጠው ይሆን?ሁሉም የስራውን ያገኛል፣እያምታቱ መኖር አይቻልም።ማን ምን እንደሰራ ተመዝግቧል።

Agere Addis

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዘረኛ አምባገነን መንግሥትና እብድ ውሻ አንድም ሁለትም ናቸው - አገሬ አዲስ

Leave a Reply

Your email address will not be published.