ይድረስ ለሚመለከተው


የሚጫወት የፖለቲካ ገበጣ
ገጣባ፣ አንኮላ፣ ባዶ ሌጣ
እንደ እስስት ተለዋዋጭ
ለምዕራብ-ምሥራቅ አሽቃባጭ፣
ትናንት ግፋ በለው ጦረኛ
ዛሬ የሰላም ዘብ ሃገርተኛ
ሃኬተኛ፣ አገዳዳይ ዓይን አውጣ
ተገለባባጭ የወሬ ሞጥሟጣ
ዘር-ጎሳ-ብሄረሰብ መዝግቦ
በህገ-መንግስት ደንግጎ ገድቦ
ሃገር በክልል ሰነጣጥቆ ከፋፍሎ
ግላዊ ዜግነትን መንጥሮ ጥሎ
ሰው በሃገሩ መጤና ባዕድ በሆነበት
ተፈናቅሎ በየቦታው ሲንከራተት
በዚህ ዓይነት ሃገር እንዴት ይገነባል?
ከቶስ ይህ “ልማት“ ምን ይባላል?
የጎሳ እልቂት መች ቆመና
አባራ እንጂ መች ከሰመና?
ያ ነው ማጠየቂያው፣  መጠይቁ
የዕንቆቅልሹ ዕንብርት ወርቁ::
***************************
ፈ.ፉ. (16 Jan 2023)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ነፋስ ሰውን ነዳው! - በላይነህ አባተ

Leave a Reply

Your email address will not be published.