ጴጥሮስ አንተ አለት ነህ! – አሰፋ በዱሉ

የዛሬው ጉዳይ በጽሁፍ የሚገለጽ አይደለም፤ምንም ነገር አይገልጸውም፡፡ጌታ እናቱን እናቴ በእኔ ምክንያት ከአገኘሽ ሃዘን ሁሉ የትኛው ይበልጣል እንዳላት አይነት ነው የሆነብኝ፡፡በዕርግጥ ይሄ ሰው-አብይ ማለቴ ነው ስንት ጊዜ ቢገለን ነው ነፍሱ የሚረካው? በቀሉስ የሚወጣለት ምን ቢያደርገን ነው? ስጋችንን አቃጠለ፤ በግሬደር በጅምላ እንደቆሻሻ ቀበረን፤አልረካም፤ልብሳችንን፤ቀለባችንን፤ሙሉ ከተማ ወደ አመድ ቀየረ አልረካም፤የራያዋ ሴት አብይ ሁሉንም ልጆቼን ጨረሳቸው በማለት የወላድ መካን እናቶችን አደረጋቸው፤ህጻናትን ሜዳ ላይ ብቻቸውን መንታ መንታ እያለቀሱ ወላጆቻቸውን እንዲጠብቁ አደረጋቸው (5 ብር በእጁ ይዞ ጉንጩ ላይ እንባ ሳይሆን ዝናብ የሚወርድ የሚመስለውን የወለጋው ህጻን ማለቴ ነው፤በፓርላማ በተለይ አንዲት እናት ያነባችውን ያስታውሷል፤ወላድ ይፍረደኝ የሚባለው ለዘሂህ ነው፤ሰው መስሏት አብይ፡እሱ ጥላ እንተክላለን የሚለውን ለቀጣይ ዕየተዘጋጀ ነበር)፤ይሄንና የመሳሰለው አላረካውም፡፡ፈሪ ሁላ ሺመልስ አብዲሳ ይላል፡፡ ሰወች- የሆነው ሁሉ አብይ ከአቅሙ በላይ የሆነ ነገር አድርገው አውነትን ለመጋፈጥ ወኔ ሲከዳቸው አልያም ጥቅም ሲሰለጥንባቸው ይሄንን ሰበብ ይደረድራሉ፡፡ሰውየው ምናልባት ትምህርት ተምሮ ከሆነ የተማረው ማታለል ብቻ ነው፡፡የእሱን ዕውነተኛ ማንነት ምናልባት አንድ የሲአይኤ አባል ጡረታ እስኪወጣ መጠበቅ ይኖርብናል፡፡

አሁን ስጋችንን ጨርሶ ወደ ነፍሳችን ቀጥሏል፡፡ እነሆ ሐዋሪያት የመሠረቷትን፤ምድራዊት ያይደለች ሰማያዊት ቤተ-ክርስቲያንን መታገል ጀምሯል፡፡ትዕቢቱ ከራስ ዳሽን ተካክሏል፡፡ይሄውና ከሽብር ወደ ሽብር እሱ እንደሚለው ሲያሻግረን አምስተኛ ዓመታችንን ደፈንን፡፡በሶስት ሺህ ዘመን ታሪካችን እንኳን በጽሁፍ፤በአፈ ታሪክ ያልሰማናቸው ታሪኮች በዚህ ጉደኛ መሪ ዘመን አይተናል፡፡ዕኛ ክርስቶስን ከነ ሙሉ መንግስቱ እንደምናምልከው በቀላዋጭ ሰብዕናው ያውቃል፡፡እናቱን፡ቅዱሳኑን፤መላዕክቱን ፈጣሪ እንዳከበራቸው፤ሁሉ እንደምናከብር በደንብ ያውቃል፤፤ዕናም በአንደኛው የሃይማኖታዊ አፈ-አብይ፤ፓስተር (ፖለቲካዊ አፈ-አብይ ሺመልስ አብዲሳ ነው) ዮናታንን፤ተጠቅሞ፤የአምላክን እናት ተሳደበ፡፡አባቶችም በእሷስ ቀልድ የለም በማለት ዕውነቱን ገለጡት፡፡ወጣቱ፤ ያለውን መንፈሳዊ ትጥቅ ታጥቆ በዘመኑ ቴክኖሎጂ አውሬውን ገጠመው፡፡ሊቃውንቱ የጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ እነዲሉ አውደ ምህረቱን ሞሉት፡፡ብዙወችም ተጸጽተው በንስሃ ተመለሱ፡፡ይህንን ሲያይ በእጅጉ ተናደደ፡፡ እናም ይቺን ቤተ-ክርስቲያን አፈርሳታለሁ ሲል አሰበ፡፡አስቦም አልቀረ፡፡ስክሪፐት ጻፈ፡፡እናም አለው አፈ-ሃይማኖት ፓስተሩን-አለት ሲሰነጠቅ፤ታያለህ፡ማህበሩም ለሁለት ይከፈላል፤የእኛ የሆነው ይለያል፤በሃይልም ይቀባል፡ እያልህ አዳራሹን በታላቅ ጩኸት ሙላው አለው፡፡አንተም ለቀጣዩ ተልኮ የእግዚአብሄር ሰው መሆንህን ታሳምናለህ፤ የመጀመሪያው አገር የማፍረስ ስራም ይጠናቀቃል፡አለው፡፡የአብይ አፈ-ሃይማኖት፤ፓስተሩም፤በደንብ ሪኸርስ  አደረገና ተወነው፡፡ግና ምን ያደርጋል፡፡የዘመኑ ወጣቶች በእነሱ አነጋገር ባነኑበት፡፡ምስሉንም አጋሩን፡፡ተመለከትሁት፡፡ የገረመኝ አባቶቻችንን በአለት መስሎ ሲተውን፤የሳተው ነገር ግን የተሸከመው መጽሀፍ ቅዱስ ስለ አለት የተናገረውን ነው፡፡ጴጥሮስ አንተ አለት ነህ፤በአንተም ላይ በተ-ክርስቲያንን እሰራታለሁ፡የሲዖል ደጆችም አይችሏትም ያለውን ነው፡፡አለቱም አይሰነጥቅም፡፡እሱ ያልተከለው ይነቀላል እንጂ፡፡ አልፎ አልፎ እሁድ፤አሁድ ስሄድ የሰማኋት ናት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ያ ትውልድ፡ ሜይ ደይ'ና ዝክረ ሰማዕታት

አባቶቻችንን ተከትለን ያሉንን ሁሉ፤እንሆናለን፡፡እነሱ፤ስለ ክርስቶስ አለሙን የተው ናቸውና፡፡ መንፈስ ቅዱስም ይመራቸዋል፡፡ስለ አቡነ ሳዊሮስ፤ አንድ ካህን ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ይሄንን አሁን ያሳዩትን ጠባያቸውን ታዝቦ ኖሮ በምን እንዳነሳናቸው ባላስታውስም ያወራኝን አስታውሳለሁ፡፡ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፋልኝ እንዳለው አይነት ነው፡፡እነ መላከ ኤዶም ኤፍሬም ሲመክሩ የሰማሁትን መሰረት በማድረግ ከመናገር እቆጠባለሁ፡፡

ብአዴን ያላደረግኝ አምላክ ክብር ምስጋና ይድረስህ!!!

አንድ እግር በርበሬ መንቀል ይቺን አገር ሰላም እንደሚያደርጋት ፍጹም እምነቴ ነው!

 

1 Comment

  1. ጡጦውን ማን ያምጣለት?
    አንድ ጊዜ ሰው አንድ ጊዜ አፈር
    አንዴ አዋቂ አንዴ ማሞ
    እየሆነ አስቸገረን በዙፋኑ ተሰይሞ።
    ጠብቶ ጠብቶ ያልጨረሰው ከዙፋኑ ላይ ሲጎለት
    ነደን ነደን ሳናልቅ እኛ ጡጦውን ማን ያምጣለት?
    ሀ ሁ ብሎ ያልቆጠራት የፍትሕን ሰሌዳ
    ያወርድብን ቀጠለ ካምናው የባሰ ዱብ እዳ
    ተረት ተረት የላምበረት ሲያጫውቱት እነ ሌንጮ
    በፊኛና ከረሜላ ሲሸምቱት እነ ነጮ
    ለስንቱ ሚሊዮን ደሃ አለኝታ ይሆናል ሲባል
    ምድጃው ጥግ ጋዝ ለኩሶ ይጫወታል በነበልባል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.