ከዐማራ ጋር ጦርነት የገጠሙ ኃይሎች ስም ዝርዝር እነሆ!

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

የዛሬውን ጽሑፌን ማን እንደሚያስተናግድልኝ ከወዲሁ ሳስበው ይጨንቀኛል፡፡ ባህላችን ባብዛኛው የመሸፋፈንና እውነትን የመደበቅ በመሆኑ ትንሽ ገለጥ ያለ ነገር ሲገጥመን በ“ከነገሩ ጦም እደሩ” ብሂላችን እየተጋረድን ብዙዎቻችን ከእውነቱ እንርቃለን፡፡ እውነት ግን ምን ጊዜም እውነት ናትና የትም አትሄድም፤ እኛ ብንሸሻትም እርሷ ግን እኛኑ ትከተለናለች፤ ከኛው ጋርም ትኖራለች፡፡ ይህ ሁሉ ዳር ዳርታ አንዲት አይነኬ ጉዳይ ልናገር ስላቆበቆብኩ ነው – ወረድ ሲል ታገኟታላችሁ፡፡

እንደውነቱ ዐማራ ያልታደለ ሕዝብ ነው፡፡ ምናልባት እርግማን ይኖርበት ይሆናል፡፡ እርግማን ደግሞ ጊዜውን ጠብቆ ቢነሳም እስከዚያው ግን አሣርን ያበላል፤ እያየነው ስለሆነ ማስረጃ መጥቀስ አያስፈልገንም፡፡ እኔ ሳውቅ እንኳን ላለፉት 40 ዓመታት ገደማ ዐማራ በገጠርም በከተማም ፍዳውን ሲቆጥር እንጂ አንድም ጊዜ እፎይ ሲል አላስተዋልኩም – በአንጻራዊነት አንዱ አገዛዝ ከሌላው ሻል ሊል ቢችል እምብዝም አትታዘቡኝ፡፡ ይሄ መከራና ስቃዩ ደግሞ ለዐማራ የሚሞቀው የሚበርደው አይመስልም፡፡ በጣሙን ተለማምዶታል፡፡ እንደበግ መታረዱንም፣ እንደፍልስጥኤም መሳደዱንም፣  በሀሰት ትርክት የተነሣ እንደ አይሁዳውያን መጠላቱንም … ተለማምዶት ደንዝዟል፡፡ “ለዚህ ሕዝብ ይህ ሁሉ ይገባዋል ወይ?” የሚለው ጥያቄ ትልቅ ጥያቄ ነው፡፡ ዕውቀቱ ያላችሁ ፈትሹና ንገሩን፡፡

የዐማራ ጠላቶች በስም ይታወቃሉ፡፡ የተወሰኑትን አሁን በዚህ አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡ በክፋት ደረጃቸው ቅደም ተከተል ስለመጥቀሴ እጠራጠራለሁና ደረጃ ውስጥ አልገባም፡፡

  1. ኢሕዲን – ብአዴን – አዴፓ፡፡ይህ ሳይወለድ የጨነገፈ ሕወሓት ሠራሽ የሆዳሞች ጥርቅም ላለፉት 40 ምናምን ዓመታት በዐማራ ስም በወያኔ ተሰፍሮና ተለክቶ ለዐማራ በተሰጠው ክልል ውሰጥ ዐማራን እንደሚወክል የክልል መንግሥት ተቆጥሮ በዐማራ ላይ ጢባጢቤ ሲጫወት ከረመ፤ አሁንም በዐማራ ስም የዐማራ አለኝታዎችን እያሳደደ በመግደልና በማሰር መላውን የዐማራ ሕዝብ ለተረኞች አስረክቦ ዐማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት እየተጋ ይገኛል፤ የጭራቁ አቢይ ኦነግ-ሸኔ አማራን አርዶ እንዲጨርስ ከተፈለገ ለአማራ የሚቆረቆር አንድም ኃይል የትም ሥፍራ መኖር የለበትም፡፡ ስለዚህም ዐማራን የሚያርደው ሸኔ እየፋፋና እየለመለመ፣ አርፎ የተቀመጠው ፋኖ ግን መወገድ አለበት፡፡ ከዚህ መሪር እውነት በተጓዳኝ ያለው ሃቅ ደግሞ አንድ የብአዴን አባል ሆዱ አይጉደልበት እንጂ የዐማራ ማለቅ ሲያሳስበው አይታይም፡፡ እንደምገምተው የዚህ ቡድን አባላት የሰውነትን ቅርጽ ተላብሰው በሰው አምሳል የተፈጠሩ ዓሣሞችና ጅቦች ይመስሉኛል፡፡ በዚህን አሳሳቢ የኅልውና ወቅት እንኳን ከአራጆቹ ጋር ተባብረው ዐማራን እያሳደዱት ነው – የሚገርም ተፈጥሮ ነው፡፡ ለወደፊቱ ቢቻል በሕይወት ተይዘው አለበለዚያም ሬሣቸው/አፅማቸው ተለይቶ መመርመርና ሥነ ተፈጥሯቸው መታወቅ አለበት፡፡ ዓለም እስከዛሬ እንደነዚህ ያለ ጉግማንግ ፍጡር አይታ አታውቅም፡፡ ሁሉም በመጨረሻ ከነዘር ማንዘሩ ዋጋውን ማግኘቱ ባይቀርም አሁን ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ዐማራውን ከውስጥ ሆኖ እያስጠቃና የዐማራን የነጻነት ዐውደ ግንባር በአንድ ቁጥር ጨምሮ ሀገራችንን እያወደመ ያለው ብአዴን ነው፡፡ ይህ ድርጅት ከሁሉ አስቀድሞ መጥፋት ያለበት መሆኑን ላስምርበትና ወደሌላ የጠላት ጎራ ልለፍ፡፡
  2. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን– ይህች ቤተ ክርስቲያናችን በመሠረቱ በብዙ ቁም ነገሮችና በሀገር ባለውታነት ትጠቀሳለች፡፡ እኔም ከዲቁና እስከ አርሶ ፈረስ አወዳሽነት አገልግያታለሁና ባውለታነቷን አልረሳም፡፡ አሁንም በርሷው ሥር ነኝ – አማራጭ በማጣት ጭምር፡፡ እንጂ የዚህች ተቋም በደል ተነገሮም ሆነ ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ የሚታወቅን መናገር ኃጢኣትም ነውርም አይደለምና እባካችሁን ልደመጥ፡፡ ዝም ብሎ የሚያወግዝ – ሳይገባው የሚቃወም – ብልኅነቱን አልገለጠም፡፡

2.1 ከግብጽ እንደመጣ በሚነገር የበዓል አከባበር የወሩ 30 ቀናት ሁሉምና እንዲያውም በድራቦሽ የሚከበሩ በዓላትን በመደረት ሕዝቡ ሰነፍ እንዲሆን አድርጋለች፡፡ እግዚአብሔር “በላባችሁና በወዛችሁ ለፍታችሁ ደክማችሁ ብሉ፤ ጠጡም” ያለውን ህግ ወደጎን በመተው በሕዝብ ላይ ብዙ የስንፍናና የሥራ ማቆም አድማ እንዲሰፍን ተደርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት ከወር እወር በማያቋርጡ የበዓላት ጋጋታዎች ርሀብና ችግር እንዳይለቀን ከመደረጉም በተጨማሪ ህገ እግዚአብሔርን ጥሰናል፡፡ ምዕመናንን በረጃጅም የጸሎት መርሐ ግብሮች ሌት ተቀን እያደከምን እንቅልፋምነትን አበረታትተናል፡፡ አላስፈላጊ ድግሶችንና የፍትሃት ሥነ ሥርዓቶችን በመተግበር ዜጎችን አደኽይተናል፡፡ ሁሉን ነገር በአንተ ታውቃለህ ለፈጣሪ እየሰጠን ከእኛ የሚጠበቀውን ልፋትና ጥረት እንድንቀንስ ተገደናል፡፡ ….

ተጨማሪ ያንብቡ:  [የለንደኗ ጽዮን ቤ/ክ ጉዳይ] ወፈ ግዝት! - የምንኩስናን ሥርዐት ያጎደፉ፣ ጣምራ የቀበሮ ባኅታውያን

2.2 በአምልኮት ደረጃ ካየን ብዙ ህፀፆችን መንቀስ ይቻላል፡፡ መነሻችንም መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ራሷን ከሀዲስ ኪዳን ጋር ማስተካከል አቅቷት ወይም ለማስተካከል ባለመፈለግ በብሉይ ኪዳን ብቻ እየተጓዘች ሕዝቡን አደንቁራና ከእውነተኛው አምልኮ እንዲያፈነግጥ በማድረግ ኮድኩዳ አስቀምጣዋለች፡፡ በዚያም ምክንያት ራሷ ተፈረካክሳ ለሌሎች መጤ ሃይማኖቶች ዋና መጋቢ ሆነ ትገኛለች፡፡ የርሷን ዶግማ የሚቃወም ሁሉ እንደጴንጤ ወይም እንደመናፍቅ እየተቆጠረ በዐውደ ምሕረት ላይ ስለሚሰደብና ስለሚሳቀቅ በርካታው ሊቅ በየቤቱ ቀርቷል ወይንም ቀልቡ ወዳልፈለገው ሌላ ቤተ እምነት እየሄደ የሌላ ቀማኛ ቡድን አድማቂ ሆኗል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ግትር ባትሆንና ለውጥና ዕድሳት ቢያውቃት ኖሮ፣ ሰዎቿም ከምዕመኑ የበለጡ አንባቢና ተመራማሪ ቢሆኑ ኖሮ፣ ከተራ አቡነ ዘበሰማያትና “ይምሃረነ ይሰሃለነ…”  ባለፈ ቀሳውስቷ በሃይማኖቱ ገፋ ያለ ዕውቀትና ግንዛቤ ቢኖራቸው ኖሮ፣ የኦሪትን ብቻ ሣይሆን የሀዲሳት መጻሕፍትን የኢየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮዎች ብንከተል ኖሮ ….ይሄኔ ቤተ ክርስቲያናችን ኅልውናዋን የሚፈታተን ነገር ውስጥ ባልገባች ነበር፡፡ ምዕመናን ጠያቂ አእምሮ አላቸው – የሚያድግ የሚመነደግ አንጎልም አላቸው፡፡ ያን የሚመጥን የሃይማኖት አመራርና አገልጋይ ደግሞ ያስፈልጋል – ዘመናዊ ማኅበረሰብን ባረጀ ባፈጀ ሥርዓተ ቀኖና ለማገልገል መሞከር ውኃ መውቀጥ ነው፤ አይሆንም፡፡ ሕዝብ ይጠይቃል፡፡ በዱሮው በሬ እያረሱ፣ ፈታኝ ጥያቄዎችን ሲጠየቁ ደግሞ በ“ትቀሰፋለህ!” ጥንታዊ የሞኝ ፈሊጥ እያስፈራሩ በልብሰ ተክህኖ በተጀቦነ አላዋቂነት ማገልገል ሃይማኖትን ለማጥፋት ካልሆነ ለማልማት እንደማይጠቅም ካህኖቻችን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ይህን የምለው የሚሉትን የማይሆኑ ጳጳሣትንና ቀሳውስትን ውስጣዊ ችግር እዚህ ላይ መጥቀስ ባለመፈለግ ነው፡፡ እንጂ ወደዝርዝሩ ብገባ ጨዋው ከሊቅ ተብዬው የሚበልጥባቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ፖለቲካና ቤተ እምነት በተስተካከለ የማጭበርበርና የማስመሰል ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ማሳየት ይቻላል፡፡ ይቅር ይበለን፡፡

2.3 ቤተ ክርስቲያን ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለገንዘብ ካደረች ቆየች፡፡ በቤተ ክርስቲያን ገንዘብ አፍ አውጥቶ ይናገራል፤ እግር አውጥቶም ይራመዳል፡፡ በገንዘብ የሚጸደቅ ይመስል ስብከቱም ዐውደ ምሕረቱም ብዙ ጊዜያቸውን የሚያባክኑት ስለገንዘብ በማውራት ነው – ያቺን የፈረደባትን ከመቀነቷ ያላትን አውጥታ የሰጠች የመጽሐፍ ቅዱስ ባልቴት በመጥቀስ፡፡ ካህኑም ሆነ ደብተራው በገንዘብ ፍቅር ተጠምዶ ቃለ እግዚአብሔርን ዘንግቷል፡፡ በየቦታው የሚተከሉ ቤተ ክርስቲያናት ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ “ሕዝቡ የትኛውን ጽላት ይፈልጋል?” ተብሎ የሚተከል ቤተ ክርስቲያን ምን ዓይነት ጽድቅ እንደሚኖረው እግዜር ይወቅ፡፡ አንድ አካባቢ ለምሣሌ የቅዱስ ገብርኤል ጽላት ሊገባ ቢል በአካባቢው የሚገኝ የሌላ የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ይከለክላል፡፡ ምክንያቱ ሲጠየቅ “ሕዝብን ይወስድብናል” ነው፡፡ በዚህና በመሰል ርዕሰ ጉዳዮች የምንሰማው ሁሉ ይሰቀጥጣል – የካህናቱንና የአድባራቱን በጠብ መናከስ፣ የደባትሩን የድግምትና የአስማት ቱማታና የደብር አለቆችን የሙስና ባህርና ውቅያኖስ ትተነው ሊያውም፡፡ ሠጋር በቅሎና አምባላይ ፈረስ በነበሩበት ዘመን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በውርንጭላ አህያ የሄደው ለዛሬዎቹ ካህናትና ጳጳሣት በቪ8 እና በፕራዶ መሄድ ሃይማኖታዊ ጽድቅን እንደሚያስገኝ(ላቸው) ለማስገንዘብ አልነበረም፡፡ የኞቹ አባቶች ብዙዎቹ አልታደሉም፡፡ ያሳዝናሉ፡፡ አንድ እንኳን ጴጥሮስን ፈልጌ በመሃላቸው አጣሁባቸው፤ አንድ እንኳን ጳውሎስን ዳስሼ አጠገባቸው አላገኘሁም፡፡ እምነት በገንዘብ ከተለወጠ አዲዮስ ፈጣሪ፡፡ በዚህ ረገድ ተበለሻሽተናል፡፡ በዚህ በዚህ ሁኔታችን ጴንጤ ጥርሱን ተነቅሶ ቢስቅብን መብቱ ነው፡፡ ሃይማኖት ሸቀጥ ከሆነ የለየላቸው ኢአማኒያን (ኤቲስቶች) ይሻላሉ፡፡ ኤቲይስት ሁኑ እያልኩ ግን አይደለም፡፡ የእግዚአብሔርን መንገድ አስተካክለን እንያዝ፤ አለበለዚያ ተሳስተን እናሳስታለንና የሥራ መስክ እንቀይር ማለቴ ነው፡፡ አሁን ያለነው ደግሞ በቸርነቱ ብዛት እንጂ በቤተ እምነቶቻችን ጥረትና ፆም ጸሎት አይደለም፡፡ እንዲያ ቢሆን ኖሮ በየቀኑ የዐማራን ደም ካልጠጣ በሕይወት የሚቆይ የማይመስለው ጭራቅ (ቫምፓየር) ጠ/ሚኒስትር አይኖረንም ነበር፡፡ መጽሐፉ አስቀድሞ “ሁሉም በኃጢኣት ሥር ወድቋልና አንድስ እንኳ ፃዲቅ የለም” ስለሚል ይህ ዓይነቱ ክስተት ለኔ ምንም ማለት አይደለም – ሀገርን እያጠፋ መሆኑ ግና ይሰመርበት፡፡ ይህ ሁሉ ነውረኝነት የመጨረሻው ዘመን ምልክት ነው፤ በዘመኑም ውስጥ እንገኛለንና ብዙ አንደናገጥ፡፡ ይልቁንስ ራሳችንን በቶሎ እንፈትሽና ወደ ደገኛይቱ መንገድ እንመለስ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጦርነቱና  ከጦርነቱ ማግስት - አገሬ አዲስ

2.4 ጽላትን በተመለከተ ብዙ ገፍቼ አልናገርም፡፡ ነገር ግን ይታሰብበት፡፡ ትምህርተ ክርስቶስን እናስታውስ፡፡ ሕዝብን አደንቁረን አንያዘው፡፡ ስግደትን ለፈጣሪ ብቻ እንዲያደርግ ሕዝብን እናስተምር፡፡ ከመጽሐፍ ቃል አናፈንግጥ፡፡ ከሃይማኖታዊ ባህልና ልማድ ፈጥነን እንውጣ፡፡ በጸሎት እርዝመትም የሚገኝ ጽድቅ እንደሌለ ከኢየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮ እንማር፡፡ አሁን ክርስቶስ ቢመጣ በምድር ሳለ “የአባቴን ቤት መሸቀጫ አደረጋችሁት” በማለት ቤተ ክርስቲያንን በካልቾ ብሎ ሁሉን ነገር እንደበታተነው የኛንም አብያተ ክርስቲያን በመነቃቀራቸውና ጉዳችንን አደባባይ አውጥቶ ባሰጣው ነበር፡፡ በዚህ ነጥብ ዙሪያ ብዙ ገባ እንዳላልኩ ይታወቅልኝ፡፡ ቤቴን ሰድቤ ለሰዳቢ አልሰጥም፡፡ ግን ውስጣችንን እንመርምር፡፡ የሰው መሣቂያም አንሁን፡፡ ከእውነተኛው መንገድ በእጅጉ መውጣታችንን እንረዳ፡፡

  1. ሕወሓት– ሕወሓት አብዛኛውን የትግራይ ሕዝብ በመርዘኛ ፕሮፓጋንዳ ጠልፋ ፀረ ዐማራ አድርጋዋለች፡፡ በዚያም ምክንያት ለዐማራ አንዱና ትልቁ ተግዳሮት ከትግራይ ምድር ይፈልቃል፡፡ እነዚህ አንድ ሊሆኑ የሚገባቸው ሁለት ማኅበረሰቦች ዕርቅ ቢያወርዱ ግን ማንም አይፈነጥዝባቸውም ነበር፡፡ የሀገራችንም ችግር በቀናትና በወራት ውስጥ በተፈታ፡፡ ይህ ደግሞ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አይቀርም፡፡ ነቀርሣ ነቀርሣው ይቆረጥና ሣምራውያን ዐማሮችና ተጋሩ ወደፊት ከሌሎች ደጋግ ዜጎች ጋር በመቀናጀት  የዚህችን ሀገር መፃዒ ዕድል ያሳምሩታል፡፡ አሁን ግን እውነቱ ሌላ ነው፡፡ አንድዬ ይማረን፡፡
  2. ሻዕቢያ– ዐማራ ጠሉ ኢሳይያስ በሰጠን የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ውስጥ እንደምንገኝ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ ኦነግ ወለዱ ጭራቅ ጠ/ሚኒስትርም ለአያቱ ሻዕቢያ አድሮ ኢትዮጵያን በሻዕቢያ ወሮበሎች እያስፈነጨባት ነው – የትግሬና የዐማራ በሤራ ፖለቲካ መፋጀት ለሻዕቢያና መሰል የሀገራችን ጠላቶች ሠርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ የነፃነት ትግል ከሻዕቢያም ጋር ነውና እንዘጋጅ፡፡  ድራማዎቹን ተዋቸው፡፡ ጭራቁ አቢይም ሆነ ኢሳይያስ በድራማ የሰለጠኑ፣ እውነተኛ ተፈጥሯቸውን ግን በምንም መንገድ የማይቀይሩ እባቦች ናቸውና በትያትር አትጠለፉ፡፡ እውነቱን ተገንዝባችሁ ለማይቀረው አርማጌዴዖን ተዘጋጁ፡፡ የአርማጌዴዖን ሰዓት ቀርባለች – በየበራችንም ደርሳለች፡፡ ወለጋ ጊምቢ ቶሌ ቀበሌና አጣዬ ተወስና የምትቀር ከመሰለህ ክፉኛ ተጃጅለሃልና ከጮቤ ረገጣህ ተመለስ፡፡
  3. ኦነግ – ኦህዲድ – ኦሮሙማ፡፡ አንድም ብዙም የሚመስሉት የኦሮሙማ ቤተሰቦች ቀላል እንዳይመስሏችሁ፡፡ በ27 ዓመት የሰለጠኑትን ዐማራን የማረድ “ጥበብ” በአራት ዓመታት ውስጥ እንዴት እያቀላጠፉት እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡ የሥልጠናቸው ግዝፈት ደግሞ ቦርቀው ያልጠገቡት አቢይና ሽመልስ በዚህ ለጋ ዕድሜያቸው ስንቱን ዶክተርና ፕሮፌሰር ነኝ ባይ ሁላ በንክኪ በሚተላለፍ አፍዝ አደንግዛቸው እያነሆለሉና በግሩም ንግግር እያማለሉ ከጎናቸው ማቆማቸው ዋና ምሥክር ነው፡፡ አሁን ድረስ ለነሱ የሚንሰፈሰፍ ዐማራና የሌላ ነገድ አባል ሞልቷል፡፡ በቀደምለት ወለጋ ላይ ከ3000 የማያንስ ዐማራ በኦነግ-ሸኔ ጦር ተከብቦ እንደዐይጥ ሲጨፈጨፍና ለዚያም ዕውቅና በመንፈግ የኅሊና ጸሎትም እንደብርቅ ተቆጥሮ ሲከለከል እያዩ “ዐቢይ ብቻውን ምን ያድርግ? ከሥሩ ያሉት እኮ ናቸው ሥራውን የሚያበላሹበት …” የሚሉ አሽቃባጭ-አሸርጋጆችን ማየት ከዐቢይ ሰይጣናዊ ዕኩይ ድርጊት ይበልጥ ያሳምመናል፡፡ ጊዜያቸው ነው ብለን ግን ተቀምጠናል – ፍርዱን ለፈራጁ ሰጥተን፡፡ እንጂ አያያዛቸው ሁላችንንም ሳይፈጁ አካላዊም ሆነ ኅሊናዊ ዕረፍት የሚያገኙ አይመስሉም፡፡ ለማንኛውም ይህም አንዱና ትልቁ ዐውደ ግንባር ነውና ይታሰብበት፡፡ ከታሰበበት ቀላል ነው፡፡ አለማሰባችን ነው ችግሩ – ዝምታችን፡፡
  4. ግብጽና ልጆቿ፡፡ ይህም የታወቀ ነውና ዝርዝሩ አያስፈልግም፡፡ የግብጽ እጅ በጣም ረጂም ነው፡፡ ወጥነት ያለው አቋም የሌላቸውን ሱዳንን የመሰሉ ሀገራትን እንደልቧ የምታዘውና ከአሜሪካ ዓመታዊ የበጀት ድጋፍ የሚደረግላት ይህች የመርገምት ፍሬ ግብጽ ለኢትዮጵያ ተኝታ አታውቅም፤ ወደፊትም ቢሆን መቼም አትተኛልንም፡፡ ኢትዮጵያውያንን በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች በመግዛት ከመከፋፈሏ በተጨማሪ በሱዳኖችና በሌሎች ሀገራት በኩልም የምትከፍትብን ጦርነት በቀላሉ የሚታይ አይደለምና ጠንቀቅ ነው ደጉ፡፡ የዐዋጁን በጀሮ አትሉኝም መቼም፡፡ ለማስታወስ ያህል ብቻ ነው፡፡
  5. ምዕራባውያን– በአሜሪካን መንግሥት የሚመራው ይህ ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ዐውደ ውጊያ እጅግ ከባድ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያና አሜሪካ ማለት ጎልያድና ዳዊት እንደማለት ነው በመሠረቱ፡፡ በዚያ ላይ በዚሁ ጎራ ውስጥ የምትገኝን እንግሊዝን የመሰለች ማሽንክ ሀገር በጠላትነት ይዘን ትግላችን ፈጣሪ ካልታከለበት አደጋ ውስጥ ነው፡፡ እርግጥ ነው ዳዊትን አንረሳም፡፡ ጦርነትን እግዚአብሔር ካልተዋጋ ወታደር በከንቱ ይደክማል፡፡ የሆኖ ሆኖ ይህ የምዕራቡ ዓለም የኢሉሚናቲዎች ስብስብ በሀገራችን ወቅታዊና መፃዒ ዕድል ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ የጦር መሣሪያንና ሌላውን ሎጂስቲክስ ጨምሮ በገንዘብም በማቴሪያልም በሰው ኃይልም በሥልጠናም በመረጃም ጠላቶቻችንን እያስታጠቁ ስለሚያሰማሩብን ብፁዓን የሃይማኖት አባቶች ኖረውን በምህላና በፆም በሱባኤ ባንታገዝም ጸሎትን ጨምሮ ሁል-አቀፍ ዝግጅት ማድረግ አለብን፤ አለበለዚያ ትግላችን ረጂም ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡ “ረጂም ጊዜ ሊወስድ ይችላል” ነው ያልኩት – ሌላ አላልኩም፤ አልልምም፡፡
  6. የኑሮ ውድነቱ– ሆን ተብሎ በየቀኑ የሚያሻቅበው የኑሮ ውድነት ትልቅ ዐውደ ግንባር ነው፡፡ ሰዎች በኑሮ ውድነቱ እየተጠበሱ ነው፤ በርሀብ እያለቁ ነው፡፡ የብር አሥር ሽህና 20 ሽህ ደመወዝ ሊቋቋመው ያልቻለ የኑሮ ውድነት ገጥሞናል፡፡ የግል ህክምናውና ንግዱ እሳት ሆኗል፡፡ በእግርህ ወይ በመኪና ሮጠህ የገባህበት የግል ሆስፒታል በህክምና ስህተት ከገደለህ በኋላ ቤተሰቦችህን “ የታከመበትንና የዋለ ያደረበትን 700 ሽህ ብር ካልከፈላችሁ ሬሣችሁን አንሰጥም” ሲላቸው በተዓምር ብትሰማ ኢትዮጵያ ውስጥ መሆንህ ይገለጥልሃል፤ ነጋዴውም የአንድ ሽህ ብሩን ዕቃ “20 ሽህ ብር ካልሸጥኩ ምኑን አተረፍኩ!” ብሎ ቡራ ከረዩ የሚለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው – የጉዶች ሀገር፡፡ የአብዛኛው የመንግሥትና የግል ድርጅት ተቀጣሪ ደሞዝ ደግሞ ግፋ ቢል ሁለትና ሦስት ሽህ ነው – ይህ ማለት ደግሞ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ዘመን አንድ ብርና ሁለት ብር፣ የደርግ ዘመን ሃያና 30 ብር እንደማለት ነው፡፡ በ1969ዓ.ም በወር ስድስት ብር የነበረው የበየቀኑአንድ ሊትር ግሩም የላም ወተት አሁን ጥራቱ የተጓደለ ዝንቅ ወተት በወር 2000 ብር ነው፡፡ ስድስት ብር ወደ 2000 ብር ማደጓን አስላና ሌላውንም ሁሉ በዚሁ ስሌት አስቡት – በ1957ዓ.ም በሰባትና በስምንት ብር ይገዛ የነበረው ሠንጋ በሬ አሁን ከ50 ሽህ ብር በታች አታገኘውም – በቅርቡ እኮ የደለበ በሬ በብር 250 ሽህ እንደተሰሸጠ ሰምተናል፡፡ የዐርባ ሣንቲም ምሥር ክክ 140 ብር መግባቷንም አትዘንጉ ታዲያ – የሃምሣ ሣንቲሙ የአፄው ዘመን የብሩንዶ ቁርጥ አሁን ከ1000 እስከ 1500 ብር መግባቱን ጭምር፡፡ አንድ ኪሎ ቡና ብር አምስት መቶን መታከኩንም አትርሱ፡፡ መብራት ኃይልም በበኩሉ ወብርቶ በወር ሃምሣና ስልሣ ብር እከፍል የነበርኩትን ሰውዬ አሁን ብር 2400 ገደማ ሰቅሎታል፡፡ ጉድ ነው ብቻ፡፡ የአምስት ብሩ አንድ ማዳበርያ ከሰል ብር 550 መሆኑን ደሞ ማንም እንዲያስታውሳችሁ አትጠብቁ፡፡ የአርባ ሣንቲሙ ቢራም በትንንሽ መሸታ ቤቶች ከ40 ብር በታች አታገኙትም፡፡ ይሄው ነው፡፡ ሰው እንዴት እየኖረ ነው ታዲያ ብለህ ብትጠይቀኝ መልስ የለኝም፤ ባጭሩ “በተዓምር እየኖርን ነው” ብልህ አታምነኝምና፡፡ ሲዖልም ገነትም ያሉት ሌላ ሥፍራ ሣይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ኦሮሙማዎችና ጥገኞቻቸው ግን በዊስኪ ሲራጩና ልጆቻቸውን በዓመት 2 ሚሊዮን ብር ገደማ በሚከፈልባቸው አይሲኤስን በመሳሰሉ ትምህርት ቤቶች እንደሚያስተምሩ አውቃለሁ፡፡ የምትገርም ሀገር ከሚገርም በቁሙ የሞተ ሕዝብ ጋር፡፡ በነገራችን ላይ አሁን ቤት የሚሠራው፣ መሬት የሚቀማውና የሚዘርፈው፣ ሕንጻ የሚገነባው ኦሮሞነቱን ካለሀፍረት እስከጥግ እየተጠቀመበት ያለው የኦሮሙማ ደቀ መዝሙር እንጂ ሌላው ልትወድቅ የደረሰች ዛኒጋባውን እንኳን ማደስ አይችልም፡፡ ሁሉም የሥራ ዘርፍ፣ ሁሉም የሥልጣን ቦታ፣ ሁሉም የጥቅም ሸጥና ሰርጥ… የኦሮሞና በኦሮሞ የተያዘ ነው፡፡ ወያኔ-ትግሬዎችን የሚያስመሰግን ዘመን መጣና አረፈው፡፡ የሚመጣ ግን አይመስለኝም ነበረ፡፡ ግሩም ነው፤ ዕድሜ ሰጥቶት መጨረሻውን ያዬ፡፡ አይቀርም – የቆዬ ያያል፤ የኦነግ/ኦህዲድ/ብአዴን መጨረሻ ከወያኔ መጨረሻም ይብሳል፡፡ ግልጽ እኮ ነው!! በቃኝ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  ለሴረኞች እየመሸ ይመስለኛል በኢትዮጵያ እየሆነ ያለው  ሁሉ ይገለጥ ዘንድ ነው - ሰርፀ ደስታ

3 Comments

  1. “በቀደምለት ወለጋ ላይ ከ3000 የማያንስ ዐማራ በኦነግ-ሸኔ ጦር ተከብቦ እንደዐይጥ ሲጨፈጨፍና ለዚያም ዕውቅና በመንፈግ የኅሊና ጸሎትም እንደብርቅ ተቆጥሮ ሲከለከል እያዩ “ዐቢይ ብቻውን ምን ያድርግ? ከሥሩ ያሉት እኮ ናቸው ሥራውን የሚያበላሹበት …” የሚሉ አሽቃባጭ-አሸርጋጆችን ማየት ከዐቢይ ሰይጣናዊ ዕኩይ ድርጊት ይበልጥ ያሳምመናል፡፡ ”

    An excellent way of putting it. Nice list. Great that you started with the “leg-holder” ANDM. ANDM is the one that figuratively holds the legs to facilitate the rape of the nation by TPLF and (OPDO/ OLF.)

    Although I don’t agree with all the criticism points against the church, I commend your audacity – for, if there was no problem with our Church, we will not be in such a mess in the first place. I personally have no problem with the Dogma of the EOTC. There, however, are a myriad other things that need fixing.

    The church has been targeted for attack or cooptation for a very long time as you mentioned. In fact, its resilience after all this attacks, including by successive Ethiopian governments, is amazing. The attacks by Yodit, Gragn and Mussolini were not the only major assaults on the EOTC. TPLF, while still a puppy with unopened eyes, trained some of its fighters as deacons to infiltrate the monasteries and the church hierarchy. This tells you who the real TPLF dispatchers are, as college drop outs like Meles could not have planned this 14 years before they came to power.
    It is the silence of the church (as a result of TPLF/EPRDF/PP’s corruptive influence) that allowed the escalation of the church burning and ethnic cleansing project of Abiy Ahmed unchallenged.

  2. One Shegitu Dadi, a very forward looking Oromo woman has the following to say on confederation. I’m copying and pastion her write-up without her authorization hoping that she’ll not mind.

    “Here is how to save Amharas, Oromos and the country.

    Once again in our recent history, Amharas have emerged as the holders of the MASTER key to solve Ethiopia’s multifaceted problems . How? By opting for confederation.

    Amharas have no choice but to move for confederation simply because federation in the Ethiopian context does not work.

    As a polirized multi-ethnic country, Ethiopia will not have a fair and free election without the opression of one or another ethnic group. Hence, democracy is an illusion that cannot be realized. The way Oromo rose to power and now control the entire country through proxy regional governments is the proof. Tigreans did it for the last thirty years and Oromos have stepped in Tigreans shoes to impose similar one ethnic group rule. With their number and size of their region, Oromo opressive rule will be much worse than Tigrean`s. Give another ten years to Oromo rule, Ethiopia will be the tail of the world by all standards of measure.

    So, it is time for Amharas to exercise their constitutional right to self-determnation and vote on confederation. If they adopt conederation, it will give them the opportunity to attract direct foreign investment since confederation will enable them to have economic diplomats and even have embasies abroad cutting the Oromo controlled foreign ministry diverting foreign investment to Oromia and other favoured regions. Amharas can also have a defense force which will protect them from foreign invaders including ethnic Oromo organizations.

    The Belgian model of confederation which appears to hep advance Amhara interests is something to explore.

    In any event, Ethiopia needs vast decentralization resembling confederation since the federalism the country has adopted is notheing other than unitarism in disguise. Controlled from the centre, it has miserably failed to develop the country let alone prosper and ensure safety and security of its citizens. The chaos we see in the country right now has much to do with lack of development (in all sectors) and security. Both have proven beyond the capacity of the federal government to provide.Change of government at federal level is not the answer for these problems.

    Tigreans have floated the idea of confederation, Amharas must follow. Tigreans know that they will not be fairly treated under Oromo rule; as a result, their choice of confederation appears just. Amharas must seize the opportunity to decide their destiny via self-determination as well without wasting another decade under incompetent Oromo rule. Despite all the atrocities they have committed, Tigreans are being heard and embraced by the Oromo rule since Oromos now feel tobe the savours of Ethiopia.

    Folks! Don’`t be fooled!. Oromos pretend to be “savours” only if they rule the entire country as one piece. Like any other ethnic group that aspire to oppress and dominate , they are after resources. If Amharas want to be heard and embraced as Tigreans, they have to go for confederation. If confederation does not work, they have to say good bye to the Ethiopian state.

    It is outdated for Amharas to hang on “mama ethiopia” cry since nobody in the country is interested in it any more. What Amharas got from this cry is atrocotoes, redicule and shame. All these on Amhara because they gave Oromos and other ethnic groups a country which they are not ready and willing to let go. If Amhara Insist on confederation, Oromos might call the army on it to protect the unity of the country! That will make them a laghing stock since they were in the forefront to weaken the unity of the country. Now they cannot be alllowed to reverse gear.

    Amhara! Wake up and smell the coffee. Tell Oromos that you want confederation – if not confederation then separation. Oromo crack down will soften even disappear as it did for Tigreans if Amara opt for confederation. But the idea is not to see Oromo softening on Amhara, it is to seek real confederation as a wayout from decades long quagmire. Oromo softeneing does not take Amharas anywhere.

    Try it! It will work and catapult Amhara development and growth to the sky and ensure their security. It will eventually liberate Oromos too from their bloody distructive path poised to takie everybody else down with them.

    For us, Oromos, conederation is also the answer. ”

    GREAT!

  3. ትንታኔው ጥሩና ታሪክን መሰረት ይደረገ ስለሆነ ጠቃሚ ነው፡፤ በፖለቲካ ውስጥ ግን አንድ ጠቃሚ ነገር መርሳት የለብንም፡፡ ዘላቂ ጠላትና ዘላቂ ወዳጅ የሚባል አስተሳሰብ ዘመኑ ያለፈበት ጎጅና ኋላቀር አስተሳሰብ ነው፡፡
    የአማራ ጠላቶች ተብለው በጽሁፉ ከተዘረዘሩት ውስጥ የአማራው ገዥ ፓርቲ ነኝ የሚለው የሆዳሞች ጥርቅም > ለአማራው ዘላቂ ህልውና ከሁሉም የባሰው አደገኛውና በቶሎ መወገድ ያለበት የአማራ ህዝብ ዋና ጠላት ነው፡፡
    በጠላትነት ከተዘረዘሩት ውስጥ ሻእቢያም አለበት፡፡ ሻእቢያ ወያኔን ፈጥሮና ኦነግን አጠናክሮ አገሪቱን ለዚህ ያበቃት ሀይል ነው፡፡
    ያ አለፈ፡፡ ኤርትራም አገር ሆነች፡፡ ሳሻእቢያም የኤርትራን መንግስት አቋቋመ፡፤
    አሁን ጊዜውም፣ ፖለቲካውም አሰላለፉም ተቀይሯል፡፡
    በአጭሩ አሁን አማራው ለህልውናው መቀጠል በአፋጣኝ ከውጭ ስትራቴጅክ ድጋፍ ማግኘት ግድ ይለዋል፡፡ ለዚህም ሁሉም ነገሮች ተደምረው አማራው ከኤርትራ ጋር የተጠና፣ጥንቃቄ የተመላበትና ጠቃሚ ግንኙነት፣ትብብርንና ወዳጅነትን መፍጠር ግድ ይለዋል፡፡ ጠቀሜታው ለአማራ ህዝብም ሆነ ለኤርትራ ህዝብ ዘላቂ እንዲሆንና የጋራ ጠላት የሆኑትን በጋራ መክቶ ለመምታት የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ትብብርን ያዘለ ስምምነትና አተገባበር በአስቸኳይ የግድ ያስፈልጋል፡፡
    አማራው አሁን ካለበት አደገኛ ሁኔታ በአሸናፊነት ከወጣ ለራሱም ሆነ ለሌሎች ወንድሞቹና ጎረቤቶቹ መከታና ደጋፊ ሊሆን የሚችልበት ሰፊና ተንካራ ህዝብ ስለሆነ ይህንን በራሱ ልጆች መከራ ውስጥ ገብቶ የሚዳክርበትን አስዛኝ ጊዜ በጥበብ ለማለፍ ሩቅ ማሰብና ብዙ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
    ስለሆነም የአማራን ችግር ሰፋ አድርጎ ለሚያየ ኡሉም የአማራ ሀይሎች በሙሉ አንድነትን መስርተው ቋሚ ወዳጅና ቋሚ ጠላት ሳይሆን ማሰብ የሚያስፈልጋቸው የህዝብና የአገር( የአማራው ብሎም የኢትዮጵያ ) ጥቅም ሊከበርበት የሚችልን ዘዴን ቀይሶና ከኤርትራዊያን ወንድሞቻችን ጋር በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ትብብርን መፍጠሩአስፈላጊነት ላይ ነው፡፡ የዚህ ትብብር መፈተር ለአማራው እጅግ በጣም ጠቃሚም በጣም አስፈላጊም ስለሆነ በቶሎ ሊታሰብበትና ወደተግባር ሊገባ ወቅቱ ግድ ይላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.