ዶክተር ቴድሮስ የአሸባሪው ሕወሃት ቡድንን እኩይ ተግባር በመደገፍ ኢትዮጵያ ላይ ሃሰተኛ መረጃ እያሰራጩ ነው

በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ ጽህፈት ቤት

የአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የአሸባሪ ሕወሃት ቡድንን እኩይ ተግባር በመደገፍ ኢትዮጵያ ላይ ሃሰተኛ መረጃ እያሰራጩ ነው ሲል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

ጽህፈት ቤቱ ዶክተር ቴድሮስ ኢትዮጵያን በተመለከተ እያሰራጩ የሚገኙትን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ አውግዟል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዶክተር ቴድሮስ ከድርጅቱ ስነ ምግባር ያፈነገጠ ድርጊትን በፍጥነት እንዲያስቆምም የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ ጽህፈት ቤት ጠይቋል።

የቡድኑ ቆንጮ አመራር የነበሩት ዶክተር ቴድሮስ አሁንም ከዋና ትእዛዝ ሰጪ አመራሮች መካከል አንዱ በመሆን ቡድኑን በማገልገል ላይ የሚገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ያነጣጠረ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ እያሰራጩ ይገኛሉ ብሏል ጽህፈት ቤቱ።

ዶክተር ቴዎድሮስ የአሸባሪውን እኩይ ተግባራት ይደግፋሉ ያለው ጽህፈት ቤቱ ፤ቡድኑ በአፋር እና አማራ ክልሎች ከፍተኛ ውድመት ሲያደርስ ተግባሩን አጋልጠው አያውቁም ብሏል።

ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት በቡድኑ ምክንያት የፈረሱትን የጤና ተቋማት ለመስራት ሲረባረቡ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ዝምታ መምረጣቸውን ነው የገለጸው ።

የሽብር ቡድኑ በአጎራባች ክልሎች ጦርነት በመክፈት በርካቶችን ሲጨፈጭፍ ፤ትምህርት ቤቶችን ፤የጤና ተቋማትን እና መሰረተ ልማቶችን ሲያወድም ምንም ያላሉት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር የሰብዓዊ እርዳታን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያን መንግስት ለማጥቃት ዘመቻ ከፍተዋል ብሏል።

የልዩ መልእክተኛው ጽህፈት ቤት ግለሰቡ የሚመሩትን ተቋም ኢትዮጵያን ለመጉዳት እየተጠቀሙበት መሆኑን ገልጾ ለዚህ ተግባሩ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግም ጠይቋል።

ኢዜአ

ተጨማሪ ያንብቡ:  " ሽርፍራፊ ስልጣን ለግለሰብ ኢጎ እና ጥቅማጥቅም እንደሆነ እንጂ ለህዝብ የተለየ አማራጭ ሃሳብ እንዲያገኝ አያደርግም ! " ተክሌ በቀለ

2 Comments

  1. ዶ/ር ቴዎድሮስ በእውነት ለትግራይ ህዝብ ቢያስብ ኑሮ ስለ ተራቡትና በየጥሻው ድርጅታቸው ወያኔ እየገፋ በላካቸው የትግራይ ልጆች ላይ የደረሰው ሞትና መቁሰል እንቅልፍ በነሳው ነበር። ግን ወያኔዎች ለራስ እንጂ ለህዝብ ቁመው አያውቁም። የወያኔን ክፋትና የባሩድ ሽታ ለመረዳት የትግራይ ክልልን የወያኔ የህዝብ መዝሙር መስመር በመስመር መመርመር ያስፈልጋል። አንድም ቦታ ላይ ስለ ሰላም ስለ አብሮ መኖር መዝሙሩ የሚለው የለም። በተቃራኒው እልፈተ ቢስ የሆነውን የጦርነት ጉሰማና ሲፈለግ የማይገኘውን የጀግንነት ታሪክ ያቅራራል እንጂ። ጀግንነት መለኪያው ወንድምና እህትን ገድሎ አሮጊቶችን ደፍሮ፤ ሊጥና እቃዎችን ዘርፎና አዘርፎ፤ በምኝታ ላይ ያሉ ወታደሮችን ገድሎ የሚተረክ ትረካ አይደለም። ለእብዶች የጀግንነት መለኪያው ያ ሊሆን ይችላል። ይህን አጥፍቶ ጠፊ ድርጅት ነው የትግራይ ልጆች የሚደግፉት። እጅግ ያሳዝናል። ወያኔ ከደርግ የባሰ አረመኔ ነው። ግን ጊዜውና የነጩ ሃይል እጎኑ ሆኖ በለው በላቸው እያስባለ ዛሬ ላለንበት እልቂትና ፍጅት ደርሰናል። ዶ/ር ቴዎድሮስ የዚህ የጨለማ ጊዜ ተባባሪ መሆኑ ምን ያህል የዘር ተሰላፊ እንደሆነ ያሳያል። የአሁኑ ይቅርና ያኔ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እያለ የሰራው ግፍ ሰማይ ጠቀስ ነው። ለመሆኑ ወያኔ ሆኖ በሃበሻው ምድር ግፍ ያልሰራ ይገኛል? በጭራሽ!
    አሁን የተመድ ስብሰባ እንደገና መቀመጥ፤ የአሜሪካ ልኡካን ወደ ኢትዮጵያ መላክ ሃገር የማፍረስ ቀቢጸ ተስፋቸውን ለማለምለም እንጂ ጦርነቱ እንዲቆም ቢፈልጉ ኑሮ መሳሪያ ወደ ትግራይ ባላጓጓዙም ነበር። የሚያሳዝነው አሜሪካ ለዲሞክራሲ ቁሜአለሁ እያለች የምትሰራው ሃገር የማፍረስ ሥራ ገዳቢ ማጣቱ ነው። ለምን በዪክሬን ጉዳይ ተመድ ለወያኔ ጭኽት የተሰበሰበውን ያህል አልተሰበሰቡም? አዎን የማይገፉት ሃይል ፊታቸው ላይ ስለተጋረጠ ነው። ድሃና ታዳጊ ሃገሮችን ማዋከብ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፓሊሲ ነው። የኤርትራ ጦር ከትግራይ ይውጣ ይሉናል። ለመሆኑ የኤርትራ ጦር ትግራይ አለን? ከሆነስ አሜሪካ ምን አገባት? እነርሱ በአፍጋኒስታን፤ በኢራቅ በሊቢያ በሶሪያ ለግብዣ ነው እንዴ የሄድት?
    ወያኔ ጦርነቱን በአማራና በአፋር ክልል ለ 3ኛ ጊዜ ከፍቶ አርሶ አድርና ታዳጊ ልጆችን እየገደለና እየዘረፈ በዚህ ዙሪያ ላይ የአሜሪካው ፓሊሲ አሁንም የማይድን እያየ የሚያሾፍ ነቀዝና ተንኮለኛ ነው። ለዚህ ማሳያው በየጊዜው የሚሰጠው መግለጫ በአመዛኙ የኢትዪጵያን መንግስት የሚኮንን ወያኔን የሚያግዝና አልፎ ተርፎም ሁለቱም ሃይሎች እንዲህ እና እንዲያ ቢያረጉ እያለ አፍጦ የተቀመጠ እውነትን አላይም ብሎ በውሸት ዓለም የሚዋልል ነው። የአሜሪካ ጉዳይ ሰው ቅነሳ ነው፡ እልፍ ሰው ቢሞት ግድ አይሰጣቸውም። ከሚሊዪን በላይ የራሱ ሰው በኮቪድ የረገፈበት አሜሪካ የዓለም ቁንጮ ከመሆን እየወረደ በውጭና በውስጥ አክራሪ ቡድኖች እየታመሰ በሚገኝበት በዚህ ሰአት ላይ ባህር ማዶ ባለ ጉዳይ እንዲህ እሮሮ ማሰማቱ ለምን ይሆን? ለትግራይ ህዝብ አዝኖ? በጭራሽ። መገዳደላችን ይፈልጉታል። እኛ ግን ሞኞች ነን ካለፈ ታሪክ የማንማር እሳትና ጭድ እያቀበሉ በሉ ሲሉን ምድራችን የምናቃጥል የእብድ ጥርቅሞች። ጦርነቱ እንዲቆም ከተፈለገ ወያኔ መጥፋት አለበት። ያለበለዚያ ልክ የትግራይን ሰንደቅ አንግበው እንደሚዘምሩት መዝሙር “ዝንተ ዓለም” መግደል መገዳደል ብቻ እጣችን ይሆናል።
    ያለ ቅጥ ያንቀላፋው የዶ/ር አብይ መንግስት ወያኔ ጦርነቱን ከራሱ ክልል አውጥቶ ለ 3ኛ ጊዜ አፋርና አማራን ሲያላትም ደጀን የሆነው የትግራይ ምድር ግን ሰላም ነው። ሁሌ መፈናቀል፤ ሁሌ መሞትና መዘረፍ በወያኔ ታጣቂዎች የሚፈጸምባቸው እነዚህ ክልሎች ራቸውን አዛምደውና አጣምረው ከመከላከል ወደ ማጥቃት እስካልተሻገሩ ድረስ ወያኔ ወንዙ ድረስ ሸኝቶ መመለሱ ለ 4 ጊዜ ወረራ ጊዜ እንዲገዛ መፍቀድ ነው። አዎን ይገባኛል አሜሪካ አውሮፓ እንዲህ እያለ ነው እንዴት ብለን ትግራይ እንግባ ትላላችሁ። ሥራ በልብ ነው። እሺ ተብሎም ሥራ ይሰራል ። እስቲ መቀሌ ግቡና የወያኔን አለቆች በካቴና እያሰራችሁ ለፍርድ አቅርቧቸውና አሜሪካና አውሮፓ የሚሉትን ስሙ። ጸጥ ረጭ ዝም ነው የሚሉት። አሁን ያው በዚህም በዚያም ተላላኪዎቻቸውና የጥቅም ሽርክናቸው በመሆናቸው ያለቅሳሉ እንጂ ድል ቢገኝ ምንም አይሉም። ድል ግን በትግራይ ህዝብ መነሳሳት የሚመጣና የሚደገፍ እንጂ በውጭ ሃይል ብቻ የሚሳካ አይሆንም። የትግራይ ህዝብ መሮታል። የወያኔ ካድሬና ፍርፋሪ ለቃሚዎች የሚያናፍሱትን የፈጠራ ወሬ መስማት አያሻም። ህዝቡ ሰላምን ይፈልጋል። ግን ታፍኗል። ሟቹና ቁስለኛው በበዛ ቁጥር ጥያቄው ከፍ እያለ ነው። የዶ/ር ቴዎድሮስ ምርጫ ወገንን ከእልቂት ለማትረፍ የሰላም ጥሪ ቢያደርግ በተመረጠ ነበር። ሰላም ለወያኔ ሰዎች አይሰራም። ስብዕናቸው የተቆራኘው በውሸትና ሽፍጥ ነውና። ባጭሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ የወያኔ ቃል አቀባይና እንባ ጠባቂ እንጂ የዓለም የጤና ድርጅት ዳሬክተር ሥራውን እየሰራ አይደለም። ግን ማን ይናገር ሁሉም ተለጉሟል። እልፍ ሃብት ለ 30 ዓመት የዘረፈው ወያኔ ሁሉን በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ሸምቷቸዋል። በቃኝ!

  2. ቴድሮስ አድሃኖም እዬዬ ብሎ ተንሰቅስቆ ሲያለቅስ አይቼ የትግሬ ጤነኛ የለም ብዬ ዘጋሁ እንዴት በሱ እድሜ ያለ ሰው እንዲህ ያለ ቀጣፊ አርቲስት ይሆናል ብዬ እራሴንም ጠየቅሁ እፍረት እነሱ አካባቢ ጓዙን ጥሎ ሸሸ ማለት ነው? ስብሃት ነጋ የያዝኩትን መርዝ እጠጣለሁ ሲል እንደማይሆን ሁኖ ተበላሽቶ ተያዘ ልጆቻቸው በየ ዩ ቲዩቡ ይተረተራሉ እንደው ምን ይሻላቸዋል? መጥኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published.