ለአቅመ አዳም ሳይደርስ የከሰመው የፕሮፌሱሩ የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር መድረክ ዲስኩር – ተዘራ አሰጉ

ሃገራዊ የድርድር መድረክ /National dialogues /  በአፍሪካ ፣ በደቡብ አሜሪካና በኤዝያ ባሉ እንደ ኮሎምቢያ ፣ ኢንዶኖዥያና ወዘተ ባሉ ሃገሮች ሰላምን ለማምጣት ታላቅ ሚና የተጫወተና በመጫወት  ያለ መድረክ ነው።

ለአቅም አዳም ሳይደርስ ወደመክሸፍ የደረሰው የኢትዮጵያ የምክክር መድረክ የኢትዮጵያ መንግስትንና የህወሃትን ሽብርተኛ ቡድን ችግራቸውና ግጭታቸውን በውይይት እንዲፈቱ ጥያቄ አቅርቧል “ሲሉ ሰምታ ምን አለች —” እንዲሉ  ፣ አንድ ስንዝር መራመድ የተሳነውና ለይስሙላ የተዋቀረው ተጠማኝ የድርድር መድረክ ተብየ “ውሃ ሽታ “ ሆኖ ስንብቶ ከላይ የጠቀሰውን ጋዜጣዊ መግለጫ ድስኩር ፣ ደስኩሯል ።

ይህ ከእንቅልፉ ተቆፍቁፎ የባነንው ፣ በደመ ነፍስ የሚኳትነውና ተቀላቢዊ ሃገራዊ የምክክር መድረክ  በሰጠው “የተኩስ አቁሙ”ና “የተደራደሩ” የሹፈትና የምፀት መግለጫው የሳተውና ያልተገነዘበው ቁም ነገር ምንድን ነው? የሚለውን ከዓለም አቀፍ የድርድር ማዕቀፎችና መሰረተ ፅንሰ ሃሳቦች አንፃር መሳ ለመሳ ገትረን እንገመግመዋለን።

ሃገር ወለድ ሃገራዊ የምክክር መድረክ ለሃገራት ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ትክክለኛውና አዋጭ አማራጭ እንደሆነ ልምዶች ያስገነዝባሉ።

ነገር ግን በተለይ እንደ አፍሪካ ባሉ ሃገሮች አብዛኞቹ የምክክር መድረኮች ከገዥው መደብ ጎን እየተለጠፉና እየታከኩ የመስራት ተጋላጭነት ስለሚያሳዮና ለይስሙላ ስለሚቋቋሙ ፋይዳቸው ኢምንት ነው።

በዚህም ምክንያት እንደ አፍሪካ ባሉ ሃገሮች የሚቋቋሙ ሃገራዊ የምክክር(የድርድር) መድረኮች ከጠቀሜታቸው ይልቅ የሚያመጡት ጠንቅ የሚያመዝን ፣  የሃገርን መዋለ ንዋይን የሚያባክኑ እንዲሁም ያለውጤት እራሳቸውን በራሳቸው በቅርቡ እንደተቋቋመው  የኢትዮጵያ የምክክር መድረክ እየከሰሙ እንደሚሄዱ ልምዶች ያሳያሉ።

ሃገራዊ የምክክር መድረክ የሚከወነው (ጥሪ የሚደረገው) ፓለቲካ ፓርቲዎችና መንግስት በሕዝብ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ጥያቄ ውስጥ እየገባ ሲመጣና በተለይ ሃገረ መንግስትን ተቃውሞው ነፍጥ ያነሱ ቡድኖች/ፓርቲዎች/ አቅማቸው ማሽቆልቆል ፣ ማሸነፍ ሲሳናቸውና አቅም ሲያጡ ወደ ሰላም የጠረጼዛ ዙሪያ ወይይት ለመግባት ያላቸው ፍላጎት እየናረ ስለሚመጣ በዚህ ወቅት ሃገራዊ የድርድር መድረክ ማከናወኑ አዋጭና ውጤታማም ሊሆን እንደሚችል ተሞክሮዎች ያሳያሉ።

“The scope of the dialogue must be clearly defined so that it is realistic, achievable, and manageable by the body responsible for the dialogue in the time allocated for the deliberation.”

ከላይ በዘርፉ የተመራመሩ  ባለሙያዎች እንዳሰፈሩት ሃገራዊ የውይይት መድረክ ከመከወኑ በፊት የምክክሩ ነጥቦች፣ አጀንዳዎች በግልፅ መስፈራቸውን ፣ የግጭቶችን ተጨባጭ ትክክለኛ ምክንያቶች ፣ መነሻዎች መገንዘብና የግራ ጎኑን ፍላጎቶች ነቅሰው ሊያወጡ የግድ ይላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጉራጌ ህዝባዊ ንቅናቄ(ጉህን) በዛሬው እለት መግለጫ አውጥቷል

ከዚህም በተጨማሪ የማህበረሰቡንና የሕዝቡን ሃገራዊ አመለካከት ፣ ስሜትና ፍላጎት ከግምት ውስጥ አስገብቶና መሰረት አድርጎ በቅድሚያ መመለስ ያለባቸው ጉዳዮች ካሉ በዝርዝር ሊታወቅና ሊቀመጡ ይገባል።

ሃገራዊ የምክክር መድረኩም ለሚከተሉት መሠረታዊ ጥያቄዎች በአግባቡ መላሽ ሰጥቶ ወደ ስራ መግባት ያለበት   ይሆናል። እነሱም፣

  • ሃገራዊ የምክክር መድረኩ በሚነሱትአጀንዳዎች ላይ  ዕልባት የመስጥት ችሎታና ተሞክሮ አለው ወይ?

 

  • ችግሮችለመፍታት በቂ ቁመና ፣ አቅምና አቋም ላይ ነው ወይ?

የሚሉት መሰረታዊ ጥያቄዎች ከምክክሩ በፊት ሊጤኑና ምላሽ ሊያገኝ ይገባል።

ከላይ የተዘረዘረውን ዓለም አቀፋዊ ፅንሰ ሃሳቦችና ጥያቄዎች መሰረት አድርገን የኢትዮጵያ የምክክር መድረክ አሁን ባላው ቁመና ፣ አቅምና ብቃት አንፃር ስንገመግመው የተወሳሰበውን የኢትዮጵያ የብልፅግ መንግስትና የሕወሃትን መነሻ ችግሮችና ግጭቶችን አንጥሮ በማውጣት ለመፍታት የሚቻለው አይሆንም።

ለምን ቢሉ የሕወሃት ተፋላሚ ቡድንና ግብረ አበሮችን በሚፋለሙበት ነፃ ግዛታቸው ወይም አማራጭ በሆኑ ቦታዎች እንደ ገዥው  የብልፅግና ፓርቲ እንደልቡ አግኝቶ ለማነጋገር ይሳነዋል።

በዚህም የተነሳ የምክክሩን ቅድመ ሁኔታወች ለማመቻቸት ፣ ተፋላሚ ቡድኖችን በየፊናቸውና ቦታቸው አግኝቶ ማነጋገርና ፍላጎታቸውንና የሚሽቱን ነገር ማሰባሰብ ስለማይችል ባለው አሁናዊ ቁመና ፣ ብቃትና አቅም ይህን ድርድር ለማከናወን ሁኔታዎች አይፈቅዱለትም፣ አይቻለውምም።

“The actors that should take part, and those included or excluded in the dialogue must be carefully defined and managed.”

በውይይቱ መካተትና መካተት የሌለባቸው ተፋላሚ ቡድኖች ተለይተው ተቀምጠዋል ወይ? ለሚለው ጥያቄ የኢትዮጵያ ምክክር መድረክ ይሄን አላከናወነም።

ለምሳሌ ያህል በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚታዮት ግጭቶች በሕወሃት ብቻ ሳይሆን የሕውሃት መራሹ ቡድን በፈለፈላቸው በአራቱ የአገሪቱ ማዕዘናት ታጠቀው ሕዝብና መንግስትን እያዋከቡ ያሉት ቡድኖች ማለትም ኦነግ -ሸኔ ፣ ኦነግ ፣ የቤንሻንጉል፣ የጋምቤላና የቅማንት የሕወሃት ቅጥረኞች አጀንዳቸው ተመሳሳይ በመሆኑ በአንድ ጎራና ረድፍ ሁነው በመቅረብ  ጉዳያቸው በምክክር መድረኩ ሊታይ የሚገባ ይሆናል።

ከዚህ በተቃርኖ እነዚህን ቅጥረኛ ቡድኖች ለሃገር ሰላምና አንድነት ሲባል የሚፋለሟቸው የአማራ ፋኖ ፣ የአማራ ሚኒሻ ፣ የአፋር ነፃነት ግንባርና ግጭቶች በሚከወኑበትና ፍልሚያ በበረቱባቸው አካባቢዎች ያሉትን ክልሎችን ይወክላሉ የሚባሉ የመንግስት መዋቅሮች ፍላጎታቸው በግልፅ ታትቶ መቅረብ  ያለበትን ችግሩ ዘላቂ ዕልባት ያገኝ ዘንድ በምክክር መድረኩ የመለከታቸዋል የተባሉ ቡድኖች በሙሉ ተሳታፊ መሆን የግድ ይላቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ማስገንዘቢያ ለዘ-ሐበሻ ወዳጆች

ከላይ የተዘረዘረውን ቅድመ ዝግጅቶችና ፅንሰ ሃሳቦችን ተመርኩዞ የብልፅግና ፓርቲንና ተፋላሚ ቡድኖችን በዕውቀት ፣ በሎጂስቲክ ፣ በነፃነትና ያለማንም ጣልቃ ገብነት    የኢትዮጵያ የምክክር መድረክ አቅርቦ ለማወያየት   ከአለው ተጨባጭ ሁኔታ እንፃር ይሄን ግዙፍ ስራ ለማከናወን አቅም ይኖረዋል ለማለት “ሰማይን እንደመጨበጥ” ነው የሚሆንበት እንላለን።

ስለዚህ  በወሬ ዲስኩር ጊዜውን እያጠፋ ያለው የኢትዮጵያ የምክክር መድረክ ጉዳዮ ከአቅሙ በላይ መሆኑን ተገንዝቦ ” አውቆ የተኛን ቢቀሱቅሱት አይሰማም” እንዲሉ እንቅልፉን እየለሸለሸ ባለበት ሁኔታ የተዛነፈና ለሃገር የማይበጅ መልእክት አልሁ ለማለት ብቻ ማስተላለፍ የለበትም።

  • ከዚህ ባሻገር የብልፅግና ፓርቲና ተፋላሚቡድኖች ለምክክሩ ተግባራዊነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተፋላሚዎቹ በንግግር ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አንጥሮ ወይም ወስኖ አላስቀመጠም።

 

  • “The process leading to the organization of a national dialogue must be democratic – namely, broadened to include all key stakeholders in society, such as civil society organizations, professional associations, religious leaders, political parties, and armed or unarmed resistance movements/oppositions”

 

  • የኢትዮጵያ ሃገራዊየምክክር መድረኩ ዲሞክራቲክ በሆነ መንገድ ማለትም ያለአንዳች ተፅህኖ ፣ በነፃነትና የተዋያዮችን መብትና ግዴታን ግንዛቤ ባስገባ መልኩ ስራውን ሊከወን የግድ የሚለው ይሆናል።

 

 

  • ሁሉምበምክክር መድረኩ ሊካተቱና ሊሳተፉ የሚገባቸው የጋራ ተጠቃሚ ክፍሎች /stake holders/ ማለትም የሙያ ማህበራት ፣ ማህበራዊ ተቋማት ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች ፣ ነፍጥ ያነሱና ያላነሱ ተፋላሚዎች ፣ ተፃራሪ ቡድኖችና ንቅናቄዎች በውይይት መድረኩ መሳተፍ የሚገባቸው ይሆናል።

 

  • ከዚህ በተጨማሪ በተለይ ሃገረ ኢትዮጵያን እየመራያለው የብልፅግና ፓርቲ ካልሆነ በስተቀር የመንግስት ተፃራሪ ቡድኖች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ነፍጣቸውን ማውረድ ያለባቸው ሲሆን ትግላቸውን ግን ፓለቲካዊ በሆነ ስምምነትና መንገድ ያከናውኑ ዘንድ አግባብ ያለው አካሄድ ሊመቻችላቸው የግድ ይላል ።

 

  • ከዚህ ሌላ ሃገር የሚመራ መንግስት  ሃሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀ ተቀናቃኝ ወይም ጦር ካነገበ ቡድን ጋር ለመደራደር ፍላጎት ላይኖረው ይችላል ፣ በሕገ አግባብም ቢሆን ከአሸባሪ ቡድን ጋር ለመደራደር ላይገደድ ይችላል።

 

 

  • “Often few incentives for governments to shift strategies away from warfare, especially when their enemies have been designated as terrorist.”
ተጨማሪ ያንብቡ:  የሕብር ሬዲዮ ፕሮግራም - ድብቁ የእነ ዶ/ር አብይ ጦርነት በምዕራብ ኦሮሚያ

ሃገራዊ የምክክር መድረክ ውጤታማ እንዲሆን ተቃዋሚ ቡድኖች ከጣልቃ ገብ ሃገራት  ከሚደረግላቸው የወታደራዊ ፣ የፋይናስና ቁሳቁስ ድጋፎች ራሳቸውን ሊያቅቡ ይገባል።

ይህ ተሞክሮ በተለይ በኮሎምቢያ መንግስትና በተቀናቃኝ ቡድኖች የነበረውን ግጭቶች ለመፍታት የተሄደበትን ርቀት እንደ ምሳሌ ብንወስድ ተቀናቃኞቹ  ከኮሎሚቢያ መንግስት ጋር ሲደራደር ከአሜሪካ መንግስት ይደረግላቸው የነበረውን ድጋፍ ሙለ በሙሉ እንዲቆም በማድረግና ሃገሪቱን በጋራ ለመምራት ቃል ገብተው ግጭታቸውን ለመፍታት በቅተዋል።

ይህን መሰረት በማድረግ አሸባሪው የሕውሃት መራሹ ቡድን ከግብፅ ፣ ከሱዳን ፣ ከአሜሪካ ወዘተ የሚያገኘውን የመሳሪያ ፣ የገንዘብ ፣ የቁሳቁስ፣ የሎጂስቲክ ወዘተ ድጋፍ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ማቆም ይገባዋል።

ከዚህ ባሻገር ሃገርን እየመራ ያለን መንግስትና ተቃዋሚ ፣ ተፋላሚ ቡድን/ኖች የጋራ  የተኩስ አቁም እዲያደርጉ አደራዳሪዎች /ሃገራዊ የምክክር መድረኩ/ ግፊት ወይም ማስገደድ አይኖርባቸውም ፣ አይገባምም።

ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት ይልቅኑ የሕዝብና የሃገር ስላም እዳይታወክ ሃገር እየመራ ያለው የብልፅግና መንግስት  የሚፋለማቸውን የአሸባሪ የሕውሃት ቡድንና ጭፍራዎቹን አቅም ለመንሳት ፣ መሪዎቹ እጃቸውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እዲሰጡ ፣ ማሳሪያ እንዲያወርድ፣ ቅጥ ያጣውና የተለጠጠ ፍላጎታቸው እንዲቀንሱና “ጦርነት በቃን ፣ አልቻልነም ድርድሩን ያለምንም ቅድመ ሀኔታ ተቅብለናል እንዲሉ የብልፅግና መንግስት ጦርነቱን በመቀጠል ወይም በመግፋት ነፍጥ ያነሳውን ቡድን ወደሰላም እንዲመጣ ማስገደድ እንዳለበት በየሃገራቱ የተከናወኑ የምክክር/ የድርድር መድረኮች ያሳያሉ።

ነገር ግን “ የእርጎ ዝንቡ” የሆነው የኢትዮጵያ የምክክር መድረክ የኢትዮጵያ መንግስት ጦርነት እንዲያቆም አማራጭ ካቀረበ የተቋቋመብትን ዓላማና አለምዓቀፋዊ የምክክር መድረክ ፅንሰ ሃሳብን ሊረዳ የግድ ይለዋል።

“In Colombia, the  decision not to have a bilateral ceasefire ahead of the Havana  negotiations in 2012 was intended to keep military pressure  on the armed group, but also ensure the military still felt  in control and empowered. It was also a way for the early  talks not to be derailed by ceasefire violations.”

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የምክክር መድረክ ያለምንም ስራ ተወዝፎ የሃገር መዋለ ንዋይ ከማጥፋትና መንግስትን ከማዘናጋት ተቆጥቦ በጊዜ ራሱን እንዲያከስም በማድረግ መንግስት ያለውን ኃይልና እቅም አሟጦ በመጠቀም በሃገረ ኢትዮጵያ ሰላም እንዲያወርድ አማራጭ መንገዶችን እንዲወስድ እንመክራለን።

 

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.