መቻልህ ፣ ማለፍህ ፤ ካሥጠቃህ ፤ ምን ትጠብቃለህ ?! ( አባታጠቅ   ምንዳሁንኝ )

” There is no avoiding war,it can only be postponed   to the advantage of your  enemy .  Niccolo machiaveli

ሠላምን በጦርነት ድል ነስተህ አልያም በድርድር ታገኛለህ ። ሠላምን ለማይሻ ጠላትህ ግን ለሰከንድ እንኳን ጊዜ አፎይታ አትስጠው ።  ጊዜ ከሰጠኸው ጠላትህ ተጠቃሚ አንተ ተጎጂ መሆናችሁ አይቀርም ።

“ከእንግዲህ   አይሆንም ነገር ማለሣለሥ

እነሱም አያርፉም እኔም አልመለሥ ። “

  ፩ ለሠላም ረጅም ርቀት የምትጓዘው ጭላንጭል የሠላም ሃሳብ ያለው ጠላት ሲያጋጥምህ ብቻ ነው ።

የሰው  ቁጥርህ ከጠላትህ የሰው ቁጥር እየበለጠ ፤  የነፍስ ወከፍ መሣሪያህ ከጠላትህ አሥር እጅ ሆኖ ፤ የዘመነ   የምድር እና የአየር ኃይል እያለህ ፤ ወዘተ ። ለምን ሚጢጢው ጠላትህ ዳግም ጡንቻውን አፈርጥሞ   እንዲወጋህ  ጊዜ ትሰጠዋለህ  ? ሌላ የጥፋት ዕድል ለምን ትለግሰዋለህ ?

ከላይ በርዕሱ ሥር የተጠቀሰው የኒኮሎ ማኪቬሌ  ብዙ እውነታዎችን ያዘለ ገመዜ የማይሽረውን ሃሳብ አለሸተመለከትክምን ? ጦርነትን  እንዳይፈጠር ባይቻልም ፤ ማሥቀረት ባይቻልም ፣ ማራዘም ግን ይቻላል ። ይሁን እንጂ ጥቅሙ ” ለሚጢጢው ጠላትህ ብቻ ነው ። “ ነው ፤ እኮ    የሚልህ ። ታላቁ የፖለቲካ ሊሂቅ ኒኮላማኬቬሌ ።

ኢትዮጵያ  በምሥራቅ አፍሪካ ፣ ተወዳዳሪ የሌለው የመከላከያ ሠራዊት እንደገነባች እና ጦሯም በማርሻል ደረጃ እንደሚመራ አወጀህ ስታበቃ  ፣ በምሥራቅ አፍሪካ ውሥጥ እጅግ የታወቀ እና የሚፈራ የመከላከያ ሠራዊት አገር እንዳላት እርግጥ ሆኖ  ፣ አገርህን በየአቅጣጫው በሤራ እና በገንዘቡ ኃይል ተጠቅሞ ሌት ና ቀን እያቆሰለ በድህነት እንድትማቅቅ ያደረጋትን አንድ ሚጢጢ የውሥጥ መዥገር ፤ በጀግናው መከላከያ ሠራዊት  ደፍጥጠህ መገላገል እንዴት መቻል አቃተህ ?

እንዴት  ይህንን የማፍያ ቡድን  አንገቱን ይዘህ ለፍርድ  በማቅረብ የትግራይ ህዝብን ጨምሮ መላው ጦቢያን ማሠሰደሰት አቃተህ ?  ተመሥገን  ብለሸ ፣ ያለሥጋት ይኽቺን አጭር ህይወቱን አጣፍጦ እንዲኖር ማሥቻል እንዴት ተሳነህ ?  እርቅን ፈፅሞ ለመቀበል የማይፈልገውን ጥቂት የአውሬ ህሊና ያለውን መዥገር ቡድን ፣ በእርቅ ወደ ሰውኛ አሥተሣሠብ ይመለሳል በማለት ተሥፋ አድርገህ ነውን ? ለተከታታይ 2 ዓመታት  ሥለ ሰላም  ሥትል የኢትዮጵያ ህዝብ ማስዋት እንዲከፍል አላደረክምን ?  ለዚች ወድ ፣ ውብ እና እንቁ እናት አገሩ  ብሎ  ከአንድም ሦሥት ጊዜ ፣ ይኽ ወጣት ትውልድ ህይወቱን አልገበረመሰ እንዴ ? መሰዋትነቱስ እንደ ቀላልል የሚታይ ነው እንዴ ?

ጠላትህ አሥሬ እያንሰራራ አገርህን ሲያጠፋ  ፣ እየተመለከትክስ እንዴት ለዚህ መሠሪና መዥገር ጠላትህ  ለአሰቃቂው የአራተኛ ጊዜ የጭካኔ ተግባሩ እንዲሰናዳ ጊዜ ትሰጠዋለህ ?

ወያኔ እኮ አንድበአገራችን የሚገኝ የኢትዮጵያም ሆነ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው ። ጠላትነቱንም ትግራይን ዪለህዝቡ ይሁንታ ፤ ያለ ግልፅ ፣ ነፃ ፣ ተአማኒ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ፤  በጠመንጃ ዘላለሜን ልግዛ ፤  በኢትዮጵያ መንግሥትም ውሥጥ ቁልፍ ቦታ ይሰጠኝ ባይ ነው ።

ይህ መዥገር እና እሥሥት ቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ እድገትና ብልፅግና የማይፈልግ  ፀረ ልማት ሆኖ ሣለ ፤ በለመደው ውሸት ሥለ ሠላም በቀባጠረ ቁጥር ፣ ለምን  አገርን ለመጉዳት የሚያሥችል ኃይል እሥከሚገነባ ድረስ የእፎይታ ጊዜ ይሰጠዋል ። አገርህን ለሦሥተኛ ጊዜ እያደማት ያለው ፣  ንፁሐንን በግፍ እየገደለ እና መሠረተ ልማቶችን እና የህዝብ መገልገያዎችን  እያወደመ ያለው እኮ ትላንት መዥገሩ ትህነግ ተጨፍልቆ ግብዓተ መሬቱ ባለመፈፀሙ ነው ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአቶ ተኮላ ጽሁፍ ትችት ወይንስ ሽሙጥ ከሳᎀኤል ሽፈራው/ዳላስ

ይህ እንደ እባብ አፈር ልሶ የተነሳው ጥቂት ቡድን ትላንት ” ንፋስ ላይ የተበተነ ዱቄት ነው ። ” ያልከው ነው ። ይኽ ቡድን ትላንት ሸዋ ሮቢት ደርሶ ፣ የሸዋ ልጆች ህይወታቸውን ገብረው በመሰዋትነት ድል ያደረጉት ቡድን ነው ። ይኽ ቡድንን ወደ መቀሌ ያባረሩት ለአገራቸው ለመሞት የወሰኑ ፣ የመከላከያ ሠራዊቶች ፣ የአማራ ፋኖዎች ፣ ከመላው ኢትዮጵያ በክተት ጥሪው ጦርነቱን የተቀላቀሉ ኢትዮጵያውያን  ጀግኖች  አሰንደሆኑ አትዘንጋ  !

ከነዚህ ውድ ኢትዮጵያውያን  መሰዋትነት በኋላ ግን ጦርነቱ ሳይቋጭ ፣ ጦርነቱ ይቁም  ተባለ ። ከአሸባሪው ወያኔ / ትህነግ ጥቂት ቡድን ጋር መንግሥት እደራደራለሁ አለ ። ” ለትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥቅም ሥል ። ምክንያቱም ጦርነት ያቀጭጨናል እንጂ አያሳድገንምና ! ”

እውነት ነው ። የመንግሥት ሃሳብን ንፁህ ህሊና ያለው አይቃወመውም ። ግን ፣ ግን ወያኔ /ትህነግ ለሠላም ዝግጁነት እንደሌለው እየታወቀ ፣ ለሠላም አላሥፈላጊ እርቀት መጎዝ  አሥፈላጊነቱ አይታየኝም  ።

      ፪ ሠላምን በጠረጴዛ ዙሪያ ለማግኘት የማይፈልግ በጦር ሜዳ እንዲያገኛት ይገደዳል ።

ወያኔ ለሠላም ደንታ እንደሌለው ያሥመሰከረው  እኮ ጥቅምት   24/2013 ዓ/ም ነው ። በዛን ቀን የትግራይ ህዝብን እና ኢትዮጵያን ከጠላት የሚጠብቀውን የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት ፣ በትግራይ ልዩ ኃይልና በሚሊሻው እንዲሁም ሆድ እንጂ ማሰቢያ አእምሮ በሌላቸው  በሠራዊቱ ባልደረቦች ( ቋንቋና ዘርን በሚያመልኩ ) በተቀናጀ ሤራ ድንገት የጦር ከምፑ ተወሮ  የተፈፀመበትን አረመኔያዊ ድርጊት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ለዘላለም አይረሳውም ።

ይሁን እንጂ ፣ ይኽንን ወራዳ ታሪክ ይቅር የማይለው በጭካኔ እና በግፍ የተሞላ ተግባር ፈፅመው ፣ መንግሥት በአሸባሪነት ፈርጇቸው ሲያበቃ ፤ ” ለአገሬ እና ለህዝብ ከበጀ ለይቅርታ እጄን እዘረጋለሁ ። ” በማለት ለሠላም ሲል ያልተገባ እርምጃ ቢወስድም ከሠላም ይልቀሰ በጦርነት የሚያተርፉ ኢምንት የወያኔ መሪዎች ፣መንግሥትን እንደ ጅል የኢትዮጵያን ህዝብ ደግሞ ፣ እንደፈሪ በመቁጠር  ይኸው ለሁለተኛ ጊዜ በአማራ ክልል እና በአፋር ላይ ጦር መዘው እየወጉት  ነው ።

የትግራይን ህዝብ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ምሽጋቸው ነው የሚቆጥሩት ። እናም ይህ አገርን የሚወጋ ሠራዊታቸው የእነሱ ምሽግ ነው ። በእርሱ ሞት እንጂ በእርሱ በሠላም መኖር የእነሱ ነፍስ ቀጣይነት አይኖራትም ። ይኽንን አሣምረው ሥለሚያውቁ ጠቅላላ የትግራይ ወጣት ለእነሱ ህይወት መቀጠል አላስፈላጋ መሰዋትነት ቢከፍል ቅንጣት ያህል ሐዘኔታ አይሰማቸውም ።

ወዳጆቼ ሆይ እነዚህ ኢምንት ሰው ያልሆኑ ሰዎች እኮ በትግራይ ኃይማኖት እንዲጠፋና ጥቂት የማይባል   ቄስ  ካድሬ እንዲሆን  ያደረገ ፀረ ኃይማኖቶች ናቸው ። የእግዚአብሔር  መሪነት ተወግዶ የነደብረፅዮን መሪነት በየቤተክርስቲያኑ ነግሷል ። በንፁህ ልብ አምልኮ ቀርቷል ። በአጭሩ ወያኔ በሚያሳዝን መልኩ  የትግሬ እግዛብሔርን ፈጥራለች  ። ወዳጄ ፈጣሪያችን  እግዛብሔር  አንድ ነው ።  ፈጣሪ በፍጡሩ የማይመዘን ችሎታ እንዳለው ተረዳ ። መድሃኒዓለም በሸክላው ፍጡሩ ሊመዘን ፣ ሊገለፅና ማብራሪያ ሊሰጥበት አይችልም ። እና የፈጣሪ አገልጋይ የሆኑት ቄሶች ፣ በሰማይ ዙፋኑ በምድር መረገጫው ኃያል ዓምላከሰ እንመራለን የሚሉት ቄሶች  ለምን የወያኔን ጠመንጃ ፈርተው የወያኔ አገልጋይ በመሆን በፀረ _ ሰው ድርጊት ሥጋውያን ሆነው ተሠለፉ ? ? ” መጀመሪያ ሰማይና ምድርን የፈጠረው እግዛብሔር ነው  ። ምድርም ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም ። ” የዘፍጥረት ጅማሬው ይኽ ነው ። ኦሪት ዘፍጥረትን አንብብ ።

እናም እነዚህ መዥገሮች ሰውን በጭካኔ ቆራርጠው ለመግደል ምን ያህል ርቀት ለሠጓዝ እንደሚችሉ ፣ ከእምነተ ቢሥነታቸው ተረዳ ።  ለነዚህ ፀረ_ እምነቶች ርህራሄ ፈፅሞ ማሳየት የዋህነት ነው ። እነሱ ቢያገኙህ አይንህ እያየ ሰውነትህን በቁሙ እየቆራረጡ ለአውሬ የሚሰጡ ጨካኞች ናቸው ። ይኽንን ድርጊት እኮ ከትግራይ እናት መሐፀን  በወጡ በብዙ ሃቀኛ ኢትዮጵያውያን ያውም በትግራይ ልጆች ላይ ያለርህራሄ ፈፅመውታል ። ለነሱ የሰው አካልን እንደ እንስሳ መበለት እና የሰው አንገት መቅላት ብርቅ አይደለም ።

ከነዚህ በሰው አምሳል ከተፈጠሩ የሰው ጭራቆች ጋራ መደራደር ከቶም አያሥፈልግም ።እነዚህን ሰው በላ ጠሸቂት የወያኔ አመራሮች  በመከላከያ ሠራዊታችን የሚመራው የኢትዮጵያ ጥምር ጀግና የጦር ሠራዊት ተገቢውን ቅጣት ሊሰጣቸው ይገባል ። በነሱ መቃብር ላይ ፣ የተግራይ ክልል ነዋሪ  የራሱን መሪ በነፃ ምርጫ በምርጫ ቦርድ አማካኝነት መርጦ ወደ ትክክለኛ  ፍትህ ፣ ዴሞክራሲ ፣ እኩልነት ፣ ሠላምና ዕድገትና ብልፅግና መሸጋገር ይገባዋል ። ከእንግዲህ ወደፊት እንጂ ወደኋላ የለም ። ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከጠላቶቿ ጋር ለተማማሉ  መሠሪ የወያኔ አውራዎች ጋዜ መሥጠት ለዳግም ወረራና ውድመት  እንዲዘጋጁ ከማድረግ በሥተቀር ለትግራይ ክልልም ሆነ ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም የለውም  ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.